CD/DVD ዲስክ ስክራች የማከሚያ ዘዴ

CD/DVD ዲስክ ስክራች ከሆነ ወይም በጣም በእጅ ከተነካካ የምንወደውን ዘፈን እየሰማን ወይም የምንወደውን ፊልም እያየን ቀጥ ሊልብን ወይም ሊዘልብን ይችላል።

አንዳንድ ጊዜ የዲስክ ስክራች ሊታከም ከሚችልበት ገደብ አልፎ መታከም ወይም መስተካከል ባይችልም እንደዚሁ አንዳንድ ጊዜ ደግሞ ቤት ውስጥ እራሱ በራስዎት እጅ ሊታከም ይችል ይሆናል።

ስለዚህ የዲስክ ስክራችን እራሳችን እንዴት ማከም እንደምንችል አነሆ።

1) ዲስኩን ማፅዳት:-

አንዳንድ ጊዜ ዲስኩ ባይፋቅ እንኳን አቧራ፣ የእጅ አሻራ፣ ቅባት፣ እድፍ የመሳሰሉ ነገሮች ዲስኩ በአግባቡ እንዳይጫወት ሊያሰናክሉ ይችላሉ።

ስለዚህ ዲስኩን(የውስጡን በኩል) ማፅዳት መቼም ቢሆን የመጀመሪያ አማራጭ መሆን አለበት።

ዲስኩን ሲያፀዱ

- ትንሽ ለብ ያለ ውሃ ዲስኩ ላይ አፍስሱ

-  እድፍ ያለበት ቦታ ካለ ለብ ያለ ውሃ ላይ ፈሳሽ ሳሙና አደባልቀው በጣትዎት ያቺን ቦታ አሸት አሸት ያድርጉና ለብ ባለ ውሃ ለቅለቅ አድርጉት

- ዲስኩ እንዲደርቅ ውሃውን በደንብ ያራግፉና አየር እንዲያደርቀው ጠብቁ

- ከደረቀ በኋላ ዲስኩን ከተው ሞክሩት።

- ሌላ ዲስክ የማፅዳት ዘዴ አልኮሆል ውስጥ ጥጥ ነከር አድርገው ዲስኩን(የውስጡን በኩል) ጠረግ ጠረግ ማድረግ ነው።

ዲስክ ሲጠርጉ ሁሌም ከመሃል ጀምረው ወደጫፍ (ከ ውስጥ ወድ ውጭ) በሆነ አቅጣጫ መሆን አለበት። በመሃሉ ዙሪያ እጅዎትን እያሽከረከሩ ካፀዱ(circular motion) ከሆነ ዲስኩ የበለጠ ሊበላሽ ይችላል።

2) CD/DVD ዲስኩን በሌላ ዲስክ መገልበጥ:-

አንዳንድ ጊዜ ዲስኩን በሌላ ዲስክ መገልበጥ ጥሩ የማከሚያ ዘዴ ሆኖ ሊገኝ ይችላል።

ዲስክ ለመገልበጥ Nero ተመራጭ software ነው።

3) የሚከተለውን ዘዴ ከተጠቀሙ ዲስኩ የበለጠ ሊበላሽ የሚችልበት አጋጣሚ ለፈጠር እንደሚችል መጀመሪያ ይገንዘቡ።

- የጥርስ ሳሙና (tooth paste) (paste እንጂ jell እንዳይሆን ተጠንቀቁ)። ( jell ከእቃው ሲጨመቅ እንደ ፀጉር ጄል አይነት መልክ ያለው ነው)

- ትንሽ ዲስኩ(የውስጡ በኩል) ላይ ጨመቅ አድርገው ያኑሩ።

-የመነፅር መጥረጊያ ጨርቅ ያዘጋጁና የጥርስ ሳሙናውን ከመሃል ወደጫፍ(ከውስጥ ወደ ውጭ) በሆነ መስመር ይሹት። (በመሃሉ ዙሪያ በ circle motion ካሹ ዲስኩ የበለጠ ሊበላሽ ይችላል)

- ከ 10 - 12 ጊዜ እንደዚህ በተደጋጋሚ እሹ

- ዲስኩን በጣም ጫን እንዳይሉት ተጠንቀቁ

- ሲጨርሱ ዲስኩን ትንሽ ለብ ባለ ውሃ አለቅልቁና ዲስኩ በአየር እስኪደርቅ ጠብቀው ከደረቀ በኋላ ከተው ይሞክሩት።

- እንደዚህም ሆኖ ካልሰራ እንደገና በጥንቃቄ በ tooth paste ለ 15 ደቂቃ በተመሳስስይ መንገድ አሽተው በተመሳሳይ መንገድ አለቅልቀውና አድርቀው ይሞክሩ

4) የሚከተለው ዘዴ ጊዜአዊ መፍትሄ ነው። ይህ ዘዴ ከሰራልዎት ወድያው በሌላ ዲስክ ይገልብጡት ወይም copy ያድርጉት

- ዲስኩን(የውስጡን በኩል) ቫዝሊን ወይም chap-stick በቀጭኑ ቀቡት

- ደረቅ ሲል ቫዝሊኑን ወይም chap-stick በንፁህ ጨርቅ ጠረግ ጠረግ አድርጉት

- ከዛ ዲስኩን ከተው ይሞክሩት

- ይህ ዘዴ ከሰራልዎት ይህ ዘዴ ጊዜያዊ መፍትሄ ስለሆነ ወዲያው በሌላ ዲስክ copy አድርጉት።


0 comments:

Post a Comment