አስገራሚ የጨው ጥቅሞች

የሰው ልጅ ጨውን ለብዙ መቶ እንዲየውም ሺህ ዓመታት ተጠቅምዋል። በዛም ጊዜ ውስጥ ደግሞ ጨውን ለብዙ ጥቅሞች ማዋል ችልዋል። ሰው በአብዛኛው ጊዜ ጨውን ለምግብ ማጣፈጫነት ቢሆንም የሚጠቀመው ለሌሎች ነገሮችም ማዋል ችልዋል። እነዚህን አንዳንድ ነገሮች ደግሞ ብዙ ሰው ልብ ብሎአቸው አያውቃቸውም።

ስለዚህ እነሱን እንመልከት

1) መሬት ላይ ወድቆ የተሰበረና መሬቱን ያበላሸ እንቁላል ካለ መሬቱን ለማጽዳት። እንቁላል ተሰብሮ መሬቱን ካበላሸ ጨው እንቁላሉ የፈሰሰበት ቦታ ላይ ነስንሰው ለሃያ ጠብቁ። ከሃያ ደቂቃ በህዋላ እጅግ በቀላሉ እንቁላሉን አጽድቶ መሬቱን ልክ እንደነበረ ማድረግ ይቻላል።

2) ንብ ከነደፍዎት:- ንብ ከነደፍዎት የተነደፉበትን ቦታ አርጥቡትና ከዛ ጨው እላዩ ላይ አደርገው በጨው ይሸፍኑ።

3) ዘይት ላይ የሚፈጠር እሳትን ለማጥፋት:-
እንደድንገት ዘይት ላይ እሳት ቢፈጠር መቼም ቢሆን በውሃ አያጥፉት። ግን ጨው እላዩ ላይ በብዛት መበተን አንድ ጥሩ መፍትሄ ነው።

4) ቀለማቸው የሚለቅ ልብሶችን ቀለማቸው እንዳይለቅ ማድረግ:-
ቀለማቸው የሚለቅ ለልብሶች ካልዎት ቀለማቸው እንዳይለቅ ወደ 2 ሊትር የሚጠጋጋ ውሃ ግማሽ ኩባያ ቪኒጋር እና ግማሽ ኩባያ ጨው አድርገው በሆነ ዕቃ አደባልቁ። ከዛ ልብሱን ለ1 ሰዓት እዛ ውስጥ ዘፍዝፉ። ከአንድ ሰዓት በህዋላ ልብሱን ቀለሙ ሳይለቅ ማጠብ ይችላሉ። ይህ ዘዴ በመጀመሪያ ዙር ካልሰራ ይድገሙት።
ይህ ዘዴ ወጥ ቀለም ላላቸው ልብሶች ብቻ ነው።

5) የተበላሸ እንቁላል ልመለየት:-
በአንድ ኩባያ ውሃ ውስጥ ሁለት የሻይ ማንኪያ ጨው ጨምረው በጥብጡ። ከዛ እንቁላሎቹን ብጥብጡ ውስጥ እየጨመሩ መፈተሽ ይችላሉ።
ያልተበላሹ እንቁላሎች ይሰምጣሉ የተበላሹት ግን ይንሳፈፋሉ።

6) በኮብል ስቶኖች መካከል የሚበቅሉ ሳሮችን ለማጥፋት:-
በኮብል ስቶኖች መካከል እንዲጠፋ የሚፈልጉት ሳሮች ካሉ ጨው እላዩ ላይ ይነስንሱና ከ12 ሰዓት በኋላ ትንሽ ውሃ ያድርጉበት።

7) አርቴፊሻል አበባዎችን ለማፅዳት:-
በሆነ ትልቅ ፌስታል ጨው በብዛት አድርጉና አርቴፊሻል አበባውን ውስጡ አድርጉ። እሰሩትና በደንብ ነቅንቁት። ውጤቱን የጨውን ቀለም በማየት ይገንዘቡ።

8) ሲኒዎችን ከቡና ወይ ከሻይ ከተፈጠረ አልለቅ ካለ ጠቋራ ምፅዳት:-
የጠቆረበትን ቦታ በጨው በደንብ ፈግፍገው ያቆዩና ከዛ ይጠቡ።



Posted via Blogaway


1 comment: