ጉንፋንዎት ቶሎ እንዲለቅ አለበለዛም ብዙ ሳይጎዳዎት እንዲለቅ ምን ማድረግ አለብዎት?

ጉንፋን በነገራችን ላይ እስከአሁን ድረስ መድሃኒት ያልተገኘለት በሽታ ነው።  immune system ወይም የሰውነታችን የመከላከያ አቅም ትክክል እና በቂ ከሆነ በራሱ ጊዜ የሚሄድ በሽታ ነው።

በአብዛኛው ጊዜ ለጤነኛ ሰው ጉንፋን ከ3 እስከ 7 ባሉት ቀናት ውስጥ እራሱ ይድናል። አንዳንድ ጊዜ ግን ከዛም በላይ ሊቆይ  ይችላል።

የሚከትሉት ነጥቦች ጉንፋን ከተቻለ ቶሎ እንዲለቅዎትና ብዙ ሳይጎዳዎት እንዲለቅ ይጠቅማሉ ተብሎ ይታሰባል።

1) የማርና የሎሚ ሻይ መጠጣት:-

1 1/2 የሾርባ ማንኪያ የሎሚ ጭማቂ ከ 2 የሻይ ማንኪያ ማር ጋር በአንድ ኩባያ የተቀዳ የፈላ ውሃ ውስጥ ጨምረው ይጠጡ

2) ፈሳሽ በደንብ መጠጣት:-

ማንኛውንም አይነት ፈሳሽ በደንብ መጠጣት። በተለይ ትኩስ ነገሮችን በደንብ በተደጋጋሚ መጠጣት

3) አዘውትረው እረፍት ከሚወስዱት በላይ እረፍት መውሰድ

4) ጨውና ለብ ያለ ውሃ በጥብጠው ጉሮሮዎትን በደንብ ይግሞጥሞጡበት

5) የሀኪም ትዕዛዝ ከማያስፈልጋቸው(over the counter) መድሃኒቶች አንዱን መውሰድ

6) ሲጋራ አለማጨስ ወይም ሲጋራ የሚጨስበት አካባቢ አለመሆን

7) የዶሮ ሾርባ መጠጣት:-

የዶሮ ሾርባ አንዳንድ የጉንፋንን ስሜት እንዲሰማን የሚያደርጉትን የነጭ ደም ሴል አይነቶች እንቅስቃሴያቸው እንዲቀንስ እምደሚያደርግ አንዳንድ የሳይንስ ጥናቶች ያሳያሉ። ስለዚህ የህመም ስሜቱ እንዲቀንስ ይረዳል።

የዶሮ ሾርባ ሲጠጡ የሚያቃጥል ነገር ጣል ቢያደርጉበት ይመረጣል።

8) በ zink የበለፀጉ ምግቦችን ወይም የ zink እንክብል መውሰድ:-

ጥናቶች እንደሚያመለክቱት ከሆነ የ zink እንክብል መውሰድ ጉንፋኑ እንክብሉ ሳይወሰድ ከሚድንበት አንድ ቀን አስቀድሞ እንደሚያድንና በታመሙበትም ጊዜ የህመም ስሜቱ አነስተኛ እንዲሆን እንደሚረዳ ነው።

9) ነጭ ሽንኩርት መብላት:-

ነጭ ሽንኩርት anti oxidents ስልስሉት የሰውነት የመከላከል ዓቅማችንን ከፍ ያደርጋል።

10) ጥሬ ማር መብላት:-

ጥሬ ማር ልክ እንደ ነጭ ሽንኩርት የሰውነት የመከላከያ አቅማችንን ይጨምራል። ከዛም በላይ ደግሞ ጉሮሮእችንን ከሚበላን ስሜት ነፃ ለማድረግ ይረዳል።

11) ቫይታሚን ሲ በደንብ ያላቸውን ምግቦች መብላት ወይም የቫይታሚን ሲ እንክብል መውሰድ:-

ቫይታሚን ሲ ያላቸው ምግቦች እንደ ብርቱካን፣ ሎሚ፣ ስትሮቤሪ የመሳሰሉት ናቸው።

አብዛኞቹ ፍራፍሬዎች ቫይታሚን ሲ አላቸው ግን ሎሚ፣ ብርቱካን እና ስትሮቤሪ የመሳሰሉት በተፈጥሮአቸው ኮምጠጥ የሚሉ ፍራፍሬዎች ከሌሎች በላቀ ሁኔታ ቫይታሚን ሲ ይገኝባቸዋል


0 comments:

Post a Comment