1) ሽንኩርት ሲከትፉ አይኖት እንዳያነባ

- የሽንኩቱን ጫፎች ቆርጠው ጣሉት
- ከዛ ሽንኩርቱን ለ 30 ሰኮንድ ያህል ቀዝቃዛ ውሃ ውስጥ ይዘፍዝፉት
- ሽንኩርቱን ሲከትፉ አይኖት አያነባም

2) የአፍዎትን ጠረን ማወቅ ከፈለጉ

- ከመዳፍዎት ዝቅ ብለው እጅዎትን ይላሱ
- ለ አስር ሰኮንድ ጠብቁ
- የላሱበትን ቦታ አሽትቱት
- የአፍዎት ጠረን እንደዛ ነው

3) እንቁላል ቀቅለው ሲልጡ እንዲቀልሎት ከፈለጉ እንቁላሉን ሲቀቅሉት 1 የሻይ ማንኪያ ቤኪንግ ሶዳ አብረው ውሃ ውስጥ ይጨምሩ

4) ስልኮትን ቶሎ ቻርጅ ማድረግ ከፈለጉ ቻርጅ ሲያደርጉት Airplane Mode ወይም በአንዳንድ ስልኮች Flight Mode ላይ አድርጉት


1) Parkinson በሽታን ሰው ላይ ማሽተት የምትችል ሴት ነበረች። እሷም ከ 12 ሰዎች 11 በትክክል አሽትታ በሽታው አለባቸው ብላለች። የተሳሳተችው 12ኛውም ከ 8 ወር በኋላ በሽታው ተገኝቶበታል።
 ለበለጠ መረጃ እዚህ ይጫኑ 

2) የድመቶች ኩላሊት በጣም efficient ነው። የሰውነታቸውን ውሃ መጠን ስጋ ብቻ በመብላት ያለ ውሃ መቆጣጠር ይችላል። እሱም ብቻ ሳይሆን የባህር ውሃ እራሱ ጠጥተው የሰውነታቸውን ውሃ ፍላጎት ሊቋጭላቸው ይችላል።
ለበለጠ መረጃ እዚህ ይጫኑ 

3) በቂጣቸው የሚተነፍሱ ኤሊዎች አሉት
 ለበለጠ መረጃ እዚህ ይጫኑ 

4) ሳይንቲስቶች የተቀቀለ እንቁላል መልሶ ጥሬ ማድረግ ችለዋል
 ለበለጠ መረጃ እዚህ ይጫኑ 

5) ሩሲያ ሀገር ውስጥ ጆን የሚባል ዝንጀሮ የሲጋራና የመጠጥ ሱሰኛ ሆኖ የሱስ ማገገሚያ ተቋም ገብቶ ነበር።
 ለበለጠ መረጃ እዚህ ይጫኑ 

6) ጄኔራል ዌስሊ ክላርክ የሚባሉ የአሜሪካ ታዋቂ  ጄኔራል መካከለኛው ምስራቅ አሜሪካ ጦርነት ከመጀመሯ ብዙ አመት በፊት በዛው መካከለኛ ምስራቅ አሜሪካ ለጦርነት ያወጣችውን እቅድ አጋልጠዋል።
 ለበለጠ መረጃ እዚህ ይጫኑ 


1) LCD screen ዎት ከተፋቀ በላጲስ ጠረግ ጠረግ ማድረግ ፍቀቱን ያጠፋዋል

2) ወረቀት እጅዎትን ወይም ሌላ የሰውነት ክፍሎትን ከቆረጦት chap stick(ቻፕስቲክ) ቀባ ቀባ ካደረጉት ይሽልዎታል

3) Crayons (የከለር እርሳስ) የሆነ እቃ ላይ እንዳይወድቅ እቁመው ቢለኩሱት ልክ እንደሻማ ለሰአታት ያብራል(ማስጠንቀቂያ:- አዋቂ በሌለበት አይሞክሩት)

4) ውሃ የገባበት ስልክ ካልዎት ቀጭን ፌስታል ውስጥ በቂ ሩዝ አድርገው ስልክዎትን ሩዙ ውስጥ አድርገው ፌስታሉን ቋጥረው አስረው(ቢቻል zip lock bag ውስጥ ሎክ አድርገው) ለ 24 ሰአት ያስቀምጡት። ሩዙ ውሃውን ይመጠዋል።

5) የስልክ ሙዚቃዎትን ወይም የስልክ አላርሞትን ድምጽ ለማጉላት ስልኮትን ብርጭቆ ውስጥ ያድርጉት

6) ፌስታል ለማሸግ ጫፍና  ጫፉን በ aluminum foil (አሉሚንዩም ፎይል) አንዴ ጠቅለል አድርገው በካውያ ተኩሱት እና አሉሚንየሙን ፍቱት።


1) አይጥ ከግመል በላይ ያለውሃ መኖር ይችላል

2) ሆዳችን በየ 2 ሳምንቱ አዲስ ምርግ mucus(ንፍጥ) እራሱን እንዲሸፍን ካላመረተ እራሱን ይፈጫል

3) ሽንኩርት ሲከትፉ ማስቲካ ማኘክ አይንን ከማልቀስ ያስጥላል

4) Charlie Chaplin(ቻርሊ ቻፕሊን) እራሱ የሆነ ጊዜ የቻርሊ ቻፕሊንን(እራሱን) የመምሰል ውድድር ላይ ሶስተኛ ወጥቶ ነበር።

5) አምሮአቸው ብሩህ የሆኑ ሰዎች ከሌሎች ሰዎች የበለጠ ጸጉራቸው zink እና copper አዘል ነው።

6) 111,111,111 × 111,111,111 = 12,345,678,987,654,321


1) Robert Lee Brock የሚባል በአሜሪካ ሀገር የቨርጂኒያ ነዋሪ በወንጀል ከታሰረ በኋላ እስር ቤት እያለ እራሱን ከሶ እራሱ እራሱን 5 ሚሊዮን ዶላር እንዲከፍል ከሷል። ግን እሱ እስር ቤት ስለሆነ መንግስት በራሱ ፋንታ ለራሱ 5 ሚሊዮን ዶላር እንዲከፍል ከሶ በፍርድ ቤት ተከራክሯል።
 ዝርዝሩን እዚህ ያግኙ 

2) Chile ሀገር ውስጥ Atacama በረሃ እስከ አሁን ድረስ ዝናብ ሲጥል በሰውም ሆነ በሳተላይት ታይቶ አይታወቅም።
 ዝርዝሩን እዚህ ያግኙ 

3) Michael Faraday የሚባል ታላቅ የአለማችን ሳይንቲስት ከመሰረተ ትምህርት ውጪ ሌላ አልተማረም። ሳይንቲስት የሆነውም በራሱ እየተመራመረና እያነበበ ነው።
 ዝርዝሩን እዚህ ያግኙ 

4) በጎች የሌሎች በጎችን ፊት ለይተው ማወቅ ይችላሉ።
 ዝርዝሩን እዚህ ያግኙ 

5) ዱባይ ሃገር ውስጥ ከሚኖሩ ሰዎች 80% የዛ ሃገር ሰዎች አይደሉም
 ዝርዝሩን እዚህ ያግኙ 


1) እኛ ሰዎች አእምሮአችን ውስጥ እባብ ብቻ ስናይ ስራቸውን የሚጀምሩ neurons አሉን
 ዝርዝሩን እዚህ ይመልከቱ 

2) ጥናቶች እንደሚያሳዩት ከሆነ አንድ ሰው ሃብቱ ሲጨምር በአብዛኛው ጊዜ አንድን ነገር ለማሸነፍ ሃብታም ካልሆነበት ጊዜ የበለጠ ማታለልና መዋሸት ይጀምራል።
 ዝርዝሩን እዚህ ይመልከቱ 

3) ህንድ ውስጥ Shani Shingnapur የሚባል ቀበኬ የሁሉም ሰዎች ቤት በር የለውም። የትኛውም ንብረታቸውንም አይደብቁም። እንደዛም ሆኖ እስከ ፈረንጆች አቆጣጠር 2010 ድረስ አንድም ስርቆት ተመዝግቦ አያውቅም።
 ዝርዝሩን እዚህ ይመልከቱ 

4) Hiroo Onoda የሚባል ጃፓናዊ ወታደር ሁለተኛው የአለም ጦርነት(እሱ እንዲዋጋ ግዳጅ የተጣለበት ጦርነት) ጦርነቱ ካቆመ በኋላ ጦርነቱ እንዳቆመ ባለማወቁ ለ 29 አመት ሲዋጋ ነበር
 ዝርዝሩን እዚህ ይመልከቱ 

5) በፈረንጆች አቆጣጠር በ1914 ወደ 40 ሚሊዮን ህዝብ ባለቀበት በ አንደኛ ጦርነት መካከል ገና በዓል ላይ በጠላቶች መካከል የገና ተኩስ አቁም ነበር። በዚህ ተኩስ አቁም ጠላቶች ከጠላቶቻቸው ጋር እጅ ተጨባብጠው፣ ስጦታ ተለዋውጠው እና የገና መዝሙር አብረው ዘምረው ውዲያው ወደ ጦርነቱ ተመልሰው ተገዳድለዋል።
 ዝርዝሩን እዚህ ይመልከቱ 


1) አውስትራሊያ ሃገር ውስጥ በየ 10 ደቂቃ አንድ ሰው እራሱን ለመግደል ይሞክራል
 ዝርዝሩን እዚህ 

2) Palau የሚባል ሃገር ማንም ሰው በ 0(ዜሮ) አመቱ አዎ በ 0(ዜሮ) አመቱ በህጋዊ መንገድ ሊያገባ ይችላል።
 ዝርዝሩን እዚህ 

3) Nebraska የሚባል የአሜሪካ ክፍለሃገር ውስጥ አንድ ሰው ብቻ ያለበት የሆነ መንደር አለ። እሷም ሴት ናት። የመንደሩ ከንቲባ እሷው ስትሆን ለራሷም ግብር ትከፍላለች።
 ዝርዝሩን እዚህ 

4) የድመት ዘሮች(ድመት፣ አንበሳ፣ ነብር፣ አነር እና አቦሸማኔ የመሳሰሉት) ጣፋጭ ነገር መቅመስ አይችሉም። ጣፋጭ ነገር ቢበሉ ጣፋጭነቱን አያቁትም።
 ዝርዝሩን እዚህ 

5) በተፈጥሮአቸው ለውሃ አለርጂክ የሆኑ ሰዎች አሉ።
 ዝርዝሩን እዚህ 

6) አርጀንቲና ውስጥ Rosario የሚባል ታዋቂው እግር ኳስ ተጫዋቹ Lionel Messi የተወለደበት ከተማ ውስጥ ብዙ ሰዎች ልጆቻቸውን Messi እያሉ ስለሰየሙ አዳዲስ የተወለዱ ልጆችን Messi ብሎ መሰየም አይፈቀድም።
 ዝርዝሩን እዚህ