ቤኪንግ ሶዳ፣ ቪኒጋር ወይም የሎሚ ጭማቂ እና ውሃ እንድ ላይ ፀረ እሳት ናቸው

ቤትዎት ውስጥ እግዚአብሄር አይበለውና እሳት ቢነሳ ውሃ በመርጨር ወይም በጨርቃጨርቅ በማፈን እሳቱን ማጥፋት የታወቁ ዘዴዎች ናቸው።

ግን ቤኪንግ ሶዳ እና ቪኒጋር ወይም የሎሚ ጭማቂ ከትንሽ ውሃ ጋር ፍቱን ፀረ እሳት መሆኑን ያውቁ ኖርዋል?

ከነዚህ ነገሮች እሳት አጥፊ ነገር ለመቀመም ብዙ ጣጣ አያስፈልገውም።

ለድንገተኛው በአስቸኩዋይ ይሄንን ቅማሚ ለመጠቀም እንደሚከተለው አድርጉ

1) ትልቅ ሃይላንድ እስከነክዳኑ አቅርቡና ክዳኑ ላይ ቀጭን እርሳስ እንደምንም የምታሳልፍ ቀዳዳ አብጁ።

2) ሃይላንዱን ግማሽ ያህል በቪኒጋር ወይም በሎሚ ጭማቂ ሙሉት

3) 1/3ኛ የሚያክለውን ቦታ ደግሞ በውሃ ሙሉት

3) ሶፍት ያቅርቡና ሶፍቱ ላይ ሁለት ወይም ሶስት የሾርባ ማንኪያ ቤኪንግ ሶዳ ያድርጉ

4) ሃይላንዱን ክደኑትና ቤኪንግ ሶዳ ያለበትን ሶፍት ጠቅለል አድርገው የሃይላንዱ ክዳን ላይ ባበጁት ቀዳዳ ውስጥ ገባ አድርገው ግማሽ ድረስ አድርሱት(ቤኪንግ ሶዳ ያለበት ሶፍት ሃይላንዱ ውስጥ መግባት የለበትም ግን ለዝግጁነት ግማሽ ከክዳኑ በታች ግማሽ ከክዳኑ በላይ ይሁን)

5) ሃይላንዱ በደንብ እንደተክደነ ያረጋግጡና ስው የማይነካካበት ቦታ አስቀምጡት።

6) እንደድንገት እሳት ከተፈጠረ ሶፍቱን በቀዳዳው ገፋ በማድረግ ቪኒጋርና ውሃ ብጥብጡ ውስጥ በመጨመር በደንብ ነቅንቆ በመበጥበጥ ወዲያው ይጠቀሙ።

ቤኪንግ ሶዳው ብጥብጡ ውስጥ ገብቶ ከቆየ የሚፈለገውን ውጤት ላያሳይ ስለሚችል ቤኪንግ ሶዳው ከገባ ይህን ፍቱን ቅምር ወዲያው ይጠቀሙ።



Posted via Blogaway


0 comments:

Post a Comment