ምናልባት የማያውቁት በሎሚ ማድረግ የሚችሉት አስገራሚ ነገሮች

መቼም እራሱን አውቆ ሎሚ የማያውቅ ሰው አለ ማለት በጣም ይከብዳል።
ሎሚ በልማድ በሀገራችን ለብዙ ነገሮች እንጠቀምበታለን።
ግን ሎሚ እኛ በልማድ ከምንጠቀምበት መንገዶች በተጨማሪ ሌሎች በተለምዶ የማናውቀው በጣም ጠቃሚ አገልግሎቶች አሉት። እነሱም  የሚከተሉት ናቸው።

1) ረዘም ላለ ጊዜ ማስቀመጥ:-

ሎሚን ዝምብሎ አንድ ጥግ ከማስቀመጥ አንድ መክደኛ ያለው ዕቃ ውስጥ ውሃ ሞልተው፣ ሎሚውን ውሃው ውስጥ አድርገው፣ ከድነውት ፍሪጅ ውስጥ ቢያኖሩት በተለምዶው በጤንነቱና በትኩስነቱ ከሚስነብትልዎት ጊዜ በጣም አብልጦ ይሰነብትልዎታል።

2) የእጅዎትን ወይም የእግርዎትን የጣቶች ጥፍር ንጣት ለመጨመር ይጠቅማል

ሎሚን ከቤኪንግ ሶዳ ጋር በወፍራሙ በማደባለቅ ከዛ ድብልቁን ጥፍርዎትን ቀባ አድርገው ቀስ ብለው ለትንሽ ጊዜ አሸት አሸት ማድረግ ጥፍርዎትን ንጹህ እና ነጭ ያደርግልዎታል።

3) ጉንዳን ለማባረር

ሎሚ ጉንዳኖችን ባይገድልም የምልክት አቀባበላቸውን እና አሰጣጣቸውን ስለሚረብሽ እናንተ አካባቢ ያሉትን ጉንዳኖች ሌሎች የቡድኖቻቸው አባላቶች እንዳይከተልዋቸው እና እንዳይመጡ ይረዳል።

4) ቆዳዎትን ቀላ ለማድረግና ከቆዳዎት ቀለም ጋር አብረው የማይሄዱትን ጥቆዋቁር ነጥቦችን ለማጥፋት

ሎሚን ከማር ጋር በማደባለቅና ፊትን በመቀባት እና ከትንሽ ደቂቃዎች በህዋላ በመታጥብ ፊትዎትን ቀላ ማድረግናእና እላስፈላጊ ነጠብጣቦችን ማጥፋት ይቻላል።

5) ሰውነታችንን ለማጽዳት
ሎሚ በተለይ ጠዋት ጠዋት በመጠጣት ሰውነታችን ውስጥ ያሉትን toxins ወይም ቆሻሻ ነገሮች ማጥራት ይቻላል።

6) መክተፊያዎትን ለምጽዳት
መክተፊያዎትን ለማጽዳት ጨው በመክተፊያዎት ላይ ነስንሰው ሎሚዎትን ለሁለት ቁረጡና በሎሚዎት ፍትግ ያድርጉት።

7) ልብስ ላይ አልለቅም ያለ ዕድፍ ለማስለቀቅ
ልብስዎት ላይ አልለቅም ያለ ዕድፍ ካለ ንጹህ የሎሚ ጭማቂ አና ጨው በማደባለቅ ዕድፉ ላይ ለትንሽ ጊዜ ማሸት። ከዛ ሳያጥቡት ለ24 ሰዐት ማስቀመጥ። ከ24 ሰዐት በህዋላ ማጠብ።


0 comments:

Post a Comment