ድካምን ሊፈጥሩ የሚችሉ ነገሮች እና መፍትሄዎቻቸው

የዕለት ተግባሮቻችንን ስንፈፅም ወይም ልንፈፅም ስናስብ ድካም ትልቅ መሰናክል ሊሆንብን ይችላል።

ግን ችግር የለውም። አይጨነቁ። ለአብዛኞቹ የድካም መንስኤዎች መፍትሄ አላቸው።

ስለዚህ አሁን የድካም መንስኤዎችንና መፍትሄዎቻቸውን እንመልከት

1) በሽታ:-

ለድካሞት አንደኛው መንስኤ በሽታ ሊሆን ይችላል። የሆነ በሽታ ይዞዎት ወይም ሊይዞት እየሞከረ ሊሆን ይችላል።
ድካሞት ብርቱ ከሆነ ሀኪም ቤት ሄደው ይመርመሩ።

2) እንቅልፍ:-

ለድካሞት ሌላው መንስኤ ሌሊት በቂ እንቅልፍ ሳያገኙ ቀርተውም ሊሆን ይችላል። የእንቅልፍ እጦት ድካም ብቻ ሳይሆን የምንሰራቸውን ሥራዎች ሁሉ በስነስርዓት እንዳንሰራ ይከለክላል።
ሌሊት እንቅልፍዎትን በስነስርአት ካልተኙ አደጋ ካላቸው ስራዎች በተለይ እንደ መንዳትና ኮንስትራክሽን ይቆጠቡ።
ለእቅልፍ መፍትሄው ያው መተኛት ነው።
እንቅልፍ ሁሌ የሚያስቸግርዎት ከሆነ ሀኪም ያማክሩ።

3)dehidration(የሰውነት ውሃ መጠን ማነስ):-

የሰውነታችን የውሃ መጠን ሊሆን ከሚገባው 1.5% እንኳን ከጎደለ የድካም ስሜት፣ የስሜት መቀያየር፣ ጉልበት ማጣት  ይሰማናል። በዛው እየቀነሰ ከሄደ እስከሞት ድረስ ሊዳርገን ይችላል።
በቀን ውስጥ በሞላ ጎደል ከ 1.6 እስከ 2 ሊትር ውሃ ለሰውነታችን ያስፈልጋል።
ስራችን ከባድ ከሆነ ወይም ከባድ ሥራ ከሰራን፣ ተቅማጥ ከያዘን፣ ብዙ ጨው ያለበት መግብ ከበላን እና ውሃ በየትኛውም መንገድ በላብም ሆነ በሌላ በፍጥነት የሚወጣን ከሆነ ከዛ በላይ መጠጣት ይኖርብናል።
ስለዚህ በዚህ መሰረት ውሃችንን በየቀኑ መጠጣት ያስፈልገናል።

4) Alcohol(የሚያሰክሩ መጠጦች):-

እሄ ቀልድ ሊመስልዎት ይችላል ግን የሚያሰክሩ መጠጦች የእንቅልፍዎትን ጥራት እንደሚቀንስብዎት የተረጋገጠ ነገር ነው።

5) አንዳንድ መድሃኒቶች:-

አንዳንድ መድሃኒቶች ድካም ሊለቁብን ይችላሉ። የድካም ስሜትዎት በሚወስዱት መድሃኒት ነው ብለው የሚጠረጥሩ ከሆነ እና ደግሞ ድካሙ ከባድ ከሆነብዎት ሃኪምዎትን ያማክሩ

6) የሰውነት የብረት መጠን መቀነስ:-

ብረት ደማችን አኦክስጅን ወደ መላ ሰውነታችን እንዲደርስ የሚረዳ ንጥረ ነገር ነው። ሰውነታችን በቂ ብረት ካጣ ደግሞ አኦክስጅን ለሰውነታችን በብቁ ሁኔታ አይደርስም ማለት ነው። ይህ ደግሞ አእምሮእችንን ያካትታል። በዚህ ምክንያት ድካም እና የማዞር ስሜት ሊሰማን ይችላል።
እንደ እንጀራ፣ ቅጠላቅጠሎች እና እህሎች ብረት የያዙ ምግቦች ናቸው።
እነሱን እየበሉም የብረት መጠን ማነስ በራስዎት ላይ ከጠረጠሩ ሃኪምዎትን ያማክሩ።

7) ቡና:-

ቡና ልክ ሲጠጣ ያነቃቃል። ግን ከሰውነታችን ባለቀ ጊዜ ድካም ሊያሰማ ይችላል።
በተለይ ሱስ ካለብን በተለመደው ሰዓት ከባድ ድካም ሊሰማን ይችላል።

8) በቂ እንቅስቃሴ አለማድረግ:-

በቂ እንቅስቃሴ አለማድረግ ለድካም አንዱ መንስኤ  ነው። ጥናቶች እንደሚያመለክቱት ከሆነ በሳምንት ሶስቴ ለሃያ ደቂቃ ስፖርት የሚሰሩ ሰዎች ምንም ስፖርት ከማይሰሩ ሰዎች የላቀ የሃይል መጠን ያላቸውና ድካማቸውም ስፖርት ከማይሰሩት ሰዎች ያነሰ እንደሆነ ታይቷል።

9) ከመጠን በላይ መሥራት:-

ሁሉም ነገር ሲበዛ ወይም ሲይስንስ ጥሩ አይደለም። ሥራ ጥሩ ቢሆንም ከመጠን በላይ መሥራት በተለይ የጉልበት ሥራ ከመጠን በላይ መሥራት ሰውነታችን "cortisol" የሚባል የጭንቀት ሆርሞንን በጣም እንደሚለቅና በዛም ምክንያት እንቅልፍ መተኛት  እንኳን በጣም እንደሚከብድ ጥናቶች ያመለክታሉ።
ስለዚህ ሁሉንም ነገር ስናደርግ በመጠኑ እናድርግ።


0 comments:

Post a Comment