ስቅታ ሲነሳ እንዴት ማቆም ይቻላል?

ስቅታን ለማቆም ብዙ አሉታዊ ዘዴዎች አሉ። አንዳንዶቹ ከሳይንሱ ጋር ጭራሽ ባይሄዱም አንዳንዶቹ ደግሞ በአስገራሚ ሁኔታ ከሳይንሱ ጋር የሚሄዲና በተግባር ልክ ሲደረጉ የሚያቆሙ ናቸው።
ስቅታን ለማቆም 100% ይሰራል የሚባልለት ዘዴ ባይኖርም እዚህ ከሚዘረዘሩት አብዛኞቹ ዘዴዎች ስቅታዎን ያቆማሉ ተብለው ይታመናሉ።
እንደድንገት አንዱ ዘዴ ባይሰራ እንኳን ከነዚህ ዘዴዎች አንዱ ይሰራልዎታል ተብሎ ይታመናል።

1) ትንፋሽዎትን ወደሳንባዎ ማስገባት እስከሚችሉ ድረስ አስገብተው ትንፋሽዎትን እስከአንድ ደቂቃ ድረስ ሳያስወጡት ወጥሮ መያዝ። ስቅታው ካላቆመ ሳንባዎትን በደንብ ወጥረውት ላይሆን ስለሚችል አቅምዎት እስከሚፈቅድ ድረስ ትንፋሽዎትን ሳንባዎት ውስጥ አስገብተው እንደገና ትንፋሽዎትን ሳያስወጡ በመያዝ ለአንድ ድቂቃ ያህል መሞከር።

2) በየሴኮንዱ ስቅታው እስቂያቆም ድረስ ውሃ እየተጎንጩ መዋጥ

3) አፍንጫዎትን ቆንጥጠው ይዘው ሶስት ጊዜ አፍንጫዎትን ሳይለቁ ምራቅዎትን መዋጥ። እሄንን ማድረግ ከባድ ቢሆንም ከተደረገ በኋላ ግን ስቅታውን ያቆመዋል።

4) ተዘቅዝቆ ውሃ መጠጣት

5) በመሃል ሳይተነፍሱ 6 ወይ ሰባት ጊዜ ውሃ እየተጎነጩ መዋጥ

6) በአንድ ብርጭቆ ውሃ ሞልተው ስትሮ (straw) አዘጋጁና ጆሮዎትን ድፍን አድርገው በመያዝ ውሃውን በስትሮው ጠጡ።
ይህ ዘዴ ከጀርባው ሳይንሱ ባይታወቅም ይሰራል የሚባል ዘዴ ነው።

7) ስኳር ወይም በጣም ጣፋጭ ነገር መቃም ወይም መብላት

8) ሎሚ መምጠጥ

9) ሳንባዎትን ሙሉ ትንፋሽዎትን ያስገቡና ትንፋሽዎትን ከማስወጣትዎ በፊት ውሃ ተጎንጭተው ይዋጡት


0 comments:

Post a Comment