ልብሶት ቀለሙን እንዳይለቅ መጠቀም የሚችሏቸው ዘዴዎች

አብዛኛውን ሰው ቀለም ያለው ልብስ ይወዳል። ግን ልብሱ ቀለሙን ሲለቅ ደስ የማይል መልክ ሊያመጣና የማንፈልገው አይነት ልብስ ሊሆንብን ይችላል።

ስለዚህ ልብሶት ቀለሙን እንዳይለቅብዎት አንዳንድ መጠቀም የሚችሏቸው ዘዴዎች አሉ። እነሱም የሚከተሉት ናቸው።

1) ልብሱ ላይ ያለውን label በደንብ ማንበብ:-

Label ልብሱ የት እንደተሰራ፣ ከምን እንደተሰራ፣ እንዴት መታጠብ እንዳለበትና እንዴት መጨመቅ እንዳለበት ይነግረናል።

2) ልብስዎትን ሲያጥቡ በቀለም መለያየት:-

አንድ አይነት ቀለም ያላቸው ልብሶች አንድ ላይ ቢታጠቡ ተመራጭ ነው።

3) ልብስዎትን ሲያጥቡ መጀመሪያ ይገልብጡት:-

ልብስዎት ሲታጠብም ሆነ ሲሰጣ ተገልብጦ ቢሆን የልብስ ቀለም እንዳይለቅ ይረዳል። በተለይ ፀሃይ የልብስ ቀለምን ሊያደበዝዝ ስለሚችል ተገልብጦ ቢሰጣ ተመራጭ ነው።

4) ቀለም ያላቸውን ልብሶች በቀዝቃዛ ውሃ ማጠብ:-

ቀለም ያላቸው ልብሶች በሙቅ ውሃ ከሚታጠቡ ይልቅ በቀዝቃዛ ቢታጠቡ ቀለማቸውን ይጠብቃሉ።

5) vinigar(አቼቶ) በማጠቢያው ውሃ ውስጥ መደባለቅ:-

ልብስዎትን ሲያጥቡ በመጀመሪያ አንድ ኩባያ vinigar(አቼቶ) አድርገው ቢያደባልቁ አቼቶው የልብሱ ቀለም እንዳይለቅ ትልቅ አስተዋጽኦ ያደርጋል። የአቼቶውም ሽታ ልብሱ ከታጠበ በኋላ ይለቃል።

6) ጨው መጠቀም:-

አቼቶ የማይጠቀሙ ከሆነ ልብሶትን የሚያጥቡበት ውሃ ውስጥ ትንሽ ጨው በመካከለኛ ቁንጥጫ ጨምረው አሟምተው ልብሶትን ቢያጥቡ ጨዉ የልብስዎት ቀለም እንዳይለቅ ትልቅ አስተዋጽኦ ያደርጋል።


0 comments:

Post a Comment