አስገራሚ የሆኑ የሳይኮሎጂ(psychology) ግኝቶችና እና እውነታዎች



እስከቅርብ ጊዜ ድረስ ሳይኮሎጂ እና ፍልስፍና እንደ አንድ ጥናት ነበር የሚታዩት። እንዲየውም የሳይኮሎጂ ጥናት ከፍልስፍና ተለይቶና እራሱን ችሎ የወጣው በፈረንጆቹ ከ 1870 ዎቹ በኋላ ነው። ከዛ በኋላ በሳይኮሎጂ ጥናት ብዙ ግኝቶችና መሻሻሎች ቢኖሩም አሁንም ገና ያልተነካ ፊልድ እንደሆነ ባለሙያዎቹ ይናገራሉ።

ለማንኛውም በሳይኮሎጂ ጥናት የተኙትን እነዚህን የሚያስገርሙ ግኝቶችን እንመልከት።

1) እቅድዎትንና አላማዎትን ለሌሎች ከነገሩ ያንን እቅድ የማሳካትዎ እድል ይቀንሳል:-

በፈረንጆች አቆጣጠር ከ 1933 ዓ/ም ጀምሮ በተደረገው ጥናት መሰረት አንድ ሰው እቅዱን ለሌላ ሰው ከነገረ እቅዱን ስለነገረ የሚሰማው እርካታ ባይነግር ኖሮ የሚኖረውን ግፊት እና እልህ ይቀንስበታል ብሎ ጥናቱ ያሳያል። ስለዚህም እቅዱን የማሳካቱ እድልም የበለጠ ይቀንሳል።

2) ብዙ ሰዎች የሆነ ዘፈንን በጣም የሚወዱት ዘፈኑ የሆነ ያሳለፉትን ስሜታዊ ጊዜ ስለሚያስታውሳቸው ነው:-

ዘፈን ስሜት ላይ ተጽእኖ እንደሚያደርግ የታወቀ ነገር ነው። ግን አሁን ጥናቶች እንደሚያመለክቱት ከሆነ ተቃራኒውም እውነት ነው። ያ ማለት ስሜት ዘፈንን እንድንወደው ወይም እንዳንወደው ተጽእኖ ያደርጋል።

3) ዘፈን ስለ ማንኛውም ነገር ያለን አመለካከታችን ላይ ተጽእኖ ያደርጋል:-

በ Groningen University በተካሄደው ጥናት መሰረት ዘፈን አመለካከታችን ላይ ትልቅ አስተዋጽኦ ያደርጋል። በተለይ አሳዛኝ ዘፈን እና ይደስታ ዘፈን ስንሰማ ስለአለም ያለን አመለካከታችን ላይ በዛው መሰረት ተጽእኖ ያደርጋል።

4) ጥናቶች እንደሚያሳዩት ከሆነ ገንዘብን ለሌሎች ማዋል በራስ ከማዋል የበለጠ ደስታን ይሰጣል:-

በ Harvard buisness school በተደረገው ጥናት መሰረት ሰዎች ለሌሎች ሰዎች ገንዘብ ሲሰጡ ከማይሰጡ ይልቅ የበለጠ ደስተኞች ናቸው።

5) በጥናቶች መሰረት ገንዘብን ንብረት ማካበት ላይ ከማዋል ይልቅ በ experience(በተግባር ነገሮችን ማየት) ላይ ማጥፋት የበለጠ ደስተኛ ያደርጋል:-

6) ብዙ የዛሬ ልጆች(በተለይ ምዕራባዊያን) በ ፈረንጆች አቆጣጠር በ 1950 ዎቹ ከነበሩት የአእምሮ በሽተኞች ተመሳሳይ መጠን ያለው ጭንቀት አለባቸው:-

ጥናቶች እንደሚያመለክቱት ከሆነ የዛሬ ሰው ከድሮው ሰው እጅግ በበለጠ ሁኔታ ጭንቀት አለበት። ለዚህ ምክንያት ከሆኑት አንዳንዶቹ ሱሰኛ መሆን፣ ከህብረተሰቡ ጋር ብዙ ተቀራራቢነት አለመኖር፣ ስራ መቀያየር፣ የኑሮ ቦታ መቀያየር አንዳንዶቹ ናቸው።

7) አንዳንድ እንደፀሎት እና ቤተ ክርስቲያን መከታተል አይነት ሃይማኖታዊ ልምዶች የአእምሮን ጭንቀት ይቀንሳሉ:-

“The American Psychiatric Publishing Textbook of Mood Disorders” ባጠናው ጥናት መሰረት ሃይማኖታዊ ልማድን የሚያዘወትሩ ሰዎች ከማያዘወትሩት ሰዎች በጭንቀትና በሌሎች የአእምሮ ችግሮች ለመሰቃየት ያላቸው እድል በጣም ያነሰ ነው።

8) ገንዘብ ደስታን ሊገዛ ቢችልም ከተወሰነ የገንዘብ መጠን ካለን በኋላ ግን መጨመሩ ደስታችን ላይ ብዙም ለውጥ አያመጣም

9) በደስተኞች ሰዎች እራሳችንን መክበብ ወይም ከደስተኞች ጋር ብዙ ጊዜ አብሮ መሆን እራሳእንንም ደስተኛ እንድንሆን ያደርገናል:-

በ Psychoneuroendocrinology journal ላይ የታየ አዲስ ጥናት መሰረት ደስታም ሆነ ጭንቀት ተላላፊነት ባህሪይ አለው። እና ከየትኛውም አይነት ሰዎች ጋር መሆን የኛ ስሜት ላይ በዛው መሰረት ተጽዕኖ ያደርጋል።

10) ከ 18 እስከ 33 አመት ዕድሜ ያላቸው ሰዎች ከየትኛውም ዕድሜ ክልል ካሉ ሰዎች የበለጠ ጭንቀት አለባቸው። ከ 33 አመት በኋላ የጭንቀት መጠን እየቀነሰ ይሄዳል።

11) እራስን በቂ ተኝቻለሁ ብሎ ማሳመን በቂ ባይተኛ እራሱ ካለማሳመኑ ይልቅ በዕለት ተግባራችን ላይ የተሻለ ንቃት እንዲኖረን ያደርጋል:-

በ Journal of Experimental Psychology በታተመው ጥናት መሰረት ጥናት የተደረገባቸው ሰዎች በቂ ሳይተኙም ከበቂ በላይ ተኝታችኋል ተብለው ሲነገሩ ካልተነገሩት ይልቅ እጅግ የተሻለ ንቃትና የንቃት ተግባር አሳይተዋል።

12) አእምሮአቸው ብሩህ የሆኑ ሰዎች ስለራቸው ዝቅ አድርገው ነው የሚያስቡት። ብሩህ ያልሆኑና ብዙም የማያውቁ ሰዎች ግን በተጋነነ መልኩ ስለራሳቸው ከፍ ያለ ስሜት አላቸው።

13) ከአሁን በፊት የተደረገ ክስተትን ስናስታውስ በሚያስገርም ሁኔታ ድርጊቱን ሳይሆን የምናስታውሰው አሁን ካስታወስነው በፊት ስለሱ ያስታወስንበትን ጊዜ ነው።

14) አፍ ከፈቱበት ቋንቋ ውጪ ሌላ ቋንቋ ከቻሉ ውሳኔዎችን በሌላኛው ቋንቋ መወሰን ውሳኔው የበለጠ ምክንያታዊ እንዲሆን አስተዋጽኦ ያደርጋል።



Posted via Blogaway


0 comments:

Post a Comment