ፎሮፎርን ማጥፊያ ዘዴዎች

ፎሮፎር እንደምናውቀው አሳፋሪና ነዝናዥ ነገር ሊሆን የሚችል ነገር ነው። አንደኛ በጣም ያሳክካል ሁለተኛ በሰው ፊት ነጭ ሆኖ ሊያጋልጠንና ሊያሳፍረን ይችላል።

ፎሮፎር ላለባችሁ ሰዎች ጥሩ ዜናው አንዳንድ ሊያጠፉላችሁ የሚችሉ ዘዴዎች አሉ።

ከነሱም አንዳንዶቹ የሚከተሉት ናቸው

1) ለፎሮፎር ተብለው የተሰሩ ሻምፑዎችን መጠቀም:-

እነሱም

- zinc pyrithione shampoo

- coal tar base የሚል ያለበት ሻምፑ

- selenium sulfide ያለበት ሻምፑ

- salisylic acid ያለበት ሻምፑ

- ketoconazole ያለበት ሻምፑ

አንዳንዶቹ ናቸው

የየሰዉ የቆዳ አይነት የተለያየ ስለሆነ አንዱ የሻምፑ አይነት ካልሰራ ሌላ በመቀየር መሞከር ጠቃሚ ነው።

2) coconut oil ወይም baby oil ራስን መቀባት:-

Coconut oil ወይም baby oil ራስዎትን ከተቀቡ በኋላ የተወሰነ ያህል ጊዜ ቆይተው ይታጠቡት። ይህንን በሳምንት እስከ ሶስቴ ያድርጉ።

3) ራስዎትን እርጎ መቀባት:-

እርጎ ራስዎትን ተቀብተው ከ 10 - 15 ደቂቃ ይቆዩ። ከዛ በኋላ በትንሽ ሻምፑ ይታጠቡ።

4) ራስዎትን የሎሚ ጭማቂ መቀባት:-

የሎሚ ጭማቂ ራስዎትን ተቀብተው ለትንሽ ጊዜ ያህል ቆይተው ራስዎትን በደንብ ይታጠቡ

5) ራስዎትን vinegar/አቼቶ መቀባት:-

ሁለት የሾርባ ማንኪያ አቼቶ ራስዎትን ተቀብተው ትንሽ ጊዜ ይቆዩና በደንብ ይታጠቡት

6) ራስዎት በቂ የጸሃይ ብርሃን በየቀኑ እንዲያገኝ ማድረግ።(እንዳያበዙት ይጠንቀቁ)

7) በ zinc እና በ vitamin b የበለጸጉ ምግቦችን መብላት:-

በ zinc ከበለጸጉ ምግቦች ከዋናዎቹ

ቀይ ስጋ፣ ዶሮ፣ እንቁላል፣ የአሳማ ስጋ፣ የወተት ውጤቶች አንዳንዶቹ ናቸው።

በ vitamin b ከበለጸጉ ምግቦች ከዋናዎቹ

አሳ፣ ጉበት፣ ቀይ ስጋ፣ cheese(አይብ ከተቻለ የፈረንጅ) እና እንቁላል አንዳንዶቹ ናቸው።

8) እንደ ጄል እና ጸጉር ላይ የሙነፉ ስፕሬይዎች የመሳሰሉትን ኬሚካል ያላቸው ነገሮች መጠቀም መቀነስ

9) ጭንቀት መቀነስ

10) በሃኪም ታይቶ ጠንከር ያሉ ፎሮፎርን የሚያጠፉ ሻምፑዎችና ቅባቶች እንዲታዘዝሎት ማድረግና መጠቀም

11) steroid lotion መጠቀም:-

Steroid lotion የሚባሉት በአብዛኛው corticosteroid የሚባል ንጥረ ነገር ያለባቸው ቅባቶች ናቸው።


0 comments:

Post a Comment