1) LCD screen ዎት ከተፋቀ በላጲስ ጠረግ ጠረግ ማድረግ ፍቀቱን ያጠፋዋል

2) ወረቀት እጅዎትን ወይም ሌላ የሰውነት ክፍሎትን ከቆረጦት chap stick(ቻፕስቲክ) ቀባ ቀባ ካደረጉት ይሽልዎታል

3) Crayons (የከለር እርሳስ) የሆነ እቃ ላይ እንዳይወድቅ እቁመው ቢለኩሱት ልክ እንደሻማ ለሰአታት ያብራል(ማስጠንቀቂያ:- አዋቂ በሌለበት አይሞክሩት)

4) ውሃ የገባበት ስልክ ካልዎት ቀጭን ፌስታል ውስጥ በቂ ሩዝ አድርገው ስልክዎትን ሩዙ ውስጥ አድርገው ፌስታሉን ቋጥረው አስረው(ቢቻል zip lock bag ውስጥ ሎክ አድርገው) ለ 24 ሰአት ያስቀምጡት። ሩዙ ውሃውን ይመጠዋል።

5) የስልክ ሙዚቃዎትን ወይም የስልክ አላርሞትን ድምጽ ለማጉላት ስልኮትን ብርጭቆ ውስጥ ያድርጉት

6) ፌስታል ለማሸግ ጫፍና  ጫፉን በ aluminum foil (አሉሚንዩም ፎይል) አንዴ ጠቅለል አድርገው በካውያ ተኩሱት እና አሉሚንየሙን ፍቱት።


1) አይጥ ከግመል በላይ ያለውሃ መኖር ይችላል

2) ሆዳችን በየ 2 ሳምንቱ አዲስ ምርግ mucus(ንፍጥ) እራሱን እንዲሸፍን ካላመረተ እራሱን ይፈጫል

3) ሽንኩርት ሲከትፉ ማስቲካ ማኘክ አይንን ከማልቀስ ያስጥላል

4) Charlie Chaplin(ቻርሊ ቻፕሊን) እራሱ የሆነ ጊዜ የቻርሊ ቻፕሊንን(እራሱን) የመምሰል ውድድር ላይ ሶስተኛ ወጥቶ ነበር።

5) አምሮአቸው ብሩህ የሆኑ ሰዎች ከሌሎች ሰዎች የበለጠ ጸጉራቸው zink እና copper አዘል ነው።

6) 111,111,111 × 111,111,111 = 12,345,678,987,654,321


1) Robert Lee Brock የሚባል በአሜሪካ ሀገር የቨርጂኒያ ነዋሪ በወንጀል ከታሰረ በኋላ እስር ቤት እያለ እራሱን ከሶ እራሱ እራሱን 5 ሚሊዮን ዶላር እንዲከፍል ከሷል። ግን እሱ እስር ቤት ስለሆነ መንግስት በራሱ ፋንታ ለራሱ 5 ሚሊዮን ዶላር እንዲከፍል ከሶ በፍርድ ቤት ተከራክሯል።
 ዝርዝሩን እዚህ ያግኙ 

2) Chile ሀገር ውስጥ Atacama በረሃ እስከ አሁን ድረስ ዝናብ ሲጥል በሰውም ሆነ በሳተላይት ታይቶ አይታወቅም።
 ዝርዝሩን እዚህ ያግኙ 

3) Michael Faraday የሚባል ታላቅ የአለማችን ሳይንቲስት ከመሰረተ ትምህርት ውጪ ሌላ አልተማረም። ሳይንቲስት የሆነውም በራሱ እየተመራመረና እያነበበ ነው።
 ዝርዝሩን እዚህ ያግኙ 

4) በጎች የሌሎች በጎችን ፊት ለይተው ማወቅ ይችላሉ።
 ዝርዝሩን እዚህ ያግኙ 

5) ዱባይ ሃገር ውስጥ ከሚኖሩ ሰዎች 80% የዛ ሃገር ሰዎች አይደሉም
 ዝርዝሩን እዚህ ያግኙ 


1) እኛ ሰዎች አእምሮአችን ውስጥ እባብ ብቻ ስናይ ስራቸውን የሚጀምሩ neurons አሉን
 ዝርዝሩን እዚህ ይመልከቱ 

2) ጥናቶች እንደሚያሳዩት ከሆነ አንድ ሰው ሃብቱ ሲጨምር በአብዛኛው ጊዜ አንድን ነገር ለማሸነፍ ሃብታም ካልሆነበት ጊዜ የበለጠ ማታለልና መዋሸት ይጀምራል።
 ዝርዝሩን እዚህ ይመልከቱ 

3) ህንድ ውስጥ Shani Shingnapur የሚባል ቀበኬ የሁሉም ሰዎች ቤት በር የለውም። የትኛውም ንብረታቸውንም አይደብቁም። እንደዛም ሆኖ እስከ ፈረንጆች አቆጣጠር 2010 ድረስ አንድም ስርቆት ተመዝግቦ አያውቅም።
 ዝርዝሩን እዚህ ይመልከቱ 

4) Hiroo Onoda የሚባል ጃፓናዊ ወታደር ሁለተኛው የአለም ጦርነት(እሱ እንዲዋጋ ግዳጅ የተጣለበት ጦርነት) ጦርነቱ ካቆመ በኋላ ጦርነቱ እንዳቆመ ባለማወቁ ለ 29 አመት ሲዋጋ ነበር
 ዝርዝሩን እዚህ ይመልከቱ 

5) በፈረንጆች አቆጣጠር በ1914 ወደ 40 ሚሊዮን ህዝብ ባለቀበት በ አንደኛ ጦርነት መካከል ገና በዓል ላይ በጠላቶች መካከል የገና ተኩስ አቁም ነበር። በዚህ ተኩስ አቁም ጠላቶች ከጠላቶቻቸው ጋር እጅ ተጨባብጠው፣ ስጦታ ተለዋውጠው እና የገና መዝሙር አብረው ዘምረው ውዲያው ወደ ጦርነቱ ተመልሰው ተገዳድለዋል።
 ዝርዝሩን እዚህ ይመልከቱ 


1) አውስትራሊያ ሃገር ውስጥ በየ 10 ደቂቃ አንድ ሰው እራሱን ለመግደል ይሞክራል
 ዝርዝሩን እዚህ 

2) Palau የሚባል ሃገር ማንም ሰው በ 0(ዜሮ) አመቱ አዎ በ 0(ዜሮ) አመቱ በህጋዊ መንገድ ሊያገባ ይችላል።
 ዝርዝሩን እዚህ 

3) Nebraska የሚባል የአሜሪካ ክፍለሃገር ውስጥ አንድ ሰው ብቻ ያለበት የሆነ መንደር አለ። እሷም ሴት ናት። የመንደሩ ከንቲባ እሷው ስትሆን ለራሷም ግብር ትከፍላለች።
 ዝርዝሩን እዚህ 

4) የድመት ዘሮች(ድመት፣ አንበሳ፣ ነብር፣ አነር እና አቦሸማኔ የመሳሰሉት) ጣፋጭ ነገር መቅመስ አይችሉም። ጣፋጭ ነገር ቢበሉ ጣፋጭነቱን አያቁትም።
 ዝርዝሩን እዚህ 

5) በተፈጥሮአቸው ለውሃ አለርጂክ የሆኑ ሰዎች አሉ።
 ዝርዝሩን እዚህ 

6) አርጀንቲና ውስጥ Rosario የሚባል ታዋቂው እግር ኳስ ተጫዋቹ Lionel Messi የተወለደበት ከተማ ውስጥ ብዙ ሰዎች ልጆቻቸውን Messi እያሉ ስለሰየሙ አዳዲስ የተወለዱ ልጆችን Messi ብሎ መሰየም አይፈቀድም።
 ዝርዝሩን እዚህ 


በአለማችን አደገኛና ጠንካራ የውሻ ዝርያዎች

9) The Husky:- 

እኚህ የውሻ ዝርያዎች የተደቀሉት ለአንድ ዋና ጉዳይ ነው። እሱም በበረዶአማ አካባቢ ሰዎች ሰውንም ሆነ እቃን ለማመላለስ እንደጋሪ የሚጠቀሙበትን sled እንደፈረስ እየጎተቱ እንዲሮጡ ነው። ስለዚህ አደቃቀላቸው እራሱ ጠንካራ ትከሻ፣ አንገትና እግር እንዲኖራቸውና ያን ሁሉ ክብደት እየጎተቱ እንዲሮጡ ነው።


The Husky




8) The German Shepherd:- 

ይህ German Shepherd የሚባለው የውሻ ዝርያ እንደ ፖሊስነት፣ ሽብር ተከላካይ ቡድን፣ አደንዛዥ ዕጽ ተከላካይ ቡድን እና ሌሎች ስራዎች ላይ ከሌሎች የውሻ ዝርያዎች ሁሉ በአብዛኛው ሰው  የሚጠቀመው እሄንን የውሻ ዝርያ ነው። ይሄም ሊሆን የቻለበት ምክንያት ደግሞ ጥንካሬውና የአምሮ ብቃቱ ስለሚፈለግ ነው።


German Shepherd



7) The English Bulldog:-

ይህ English bulldog የሚባለው የውሻ ዝርያ እንደስሙም አደቃቀሉ በሬዎችን ለማገድ ወይም ለመጣል ነው። ይህ የውሻ ዝርያ በተፈጥሮ አጭር ቢሆንም ሰውነቱ እንዳለ በጡንቻ የበለጸገ ጡንቸኛ እና ጉልበተኛ ያለው የውሻ ዝርያ ነው።

The English Bulldog



6) Pit Bull:- 

ይህ Pit Bull የሚባለው የውሻ ዝርያ ያው የ bulldog ዝርያ ሲሆን ግን እነዚህ ደግሞ አደቃቀላቸው ምህረት የለሽ ተደባዳቢ እንዲሆኑ ነው። ስለዚህ እኚህ ውሻዎች በተፈጥሮአቸው እጅግ እልኸኛ ተደባዳቢና ሲደባደቡም እስከ ሞት ድረስ በእልህ እንደሚደባደቡ ይታወቃሉ። ሌላ ደግሞ እኚህ Pit Bull የውሻ ዝርያዎች ልክ እንደ English Bulldog ሰውነቱ እንዳለ በጡንቻ የበለጸገ ከመሆኑ በላይ Pit Bull በሃይል የዘለለበት ሰው ልክ በመሳሪያ እንደተመታ በሃይል እንደሚጎዳ ይታወቃል። ከዚህም በላይ ደግሞ Pit Bull ትንሽ መኪና እስከ 20 ሜትር ድረስ ሊጎትት ይችላል። 

ይህ Pit Bull የሚባለው የውሻ ዝርያ ከሁሉም የውሻ ዝርያዎች የበለጠ አደገኛ እና ገዳይ ነው ተብሎ ይታወቃል። በአለም ላይ በውሻ ከሚሞቱ ሰዎች ግማሽ የሚሆኑት ያህል የሚሞቱት በ Pit Bull ነው።

ከሌሎች የውሻ ዝርያዎች ጋርም ሆነ ከምንም ጋር ድብድብ ቢጋጠም Pit Bull እልኸኛ ስለሆነ በጉልበት ቢበለጥ እንኳን እስከሞት ድረስ ይጋደላል እንጂ እጅ አይሰጥም።

Pit Bull



5) Dogo Argentino:- 

ይህ የውሻ ዝርያ አደቃቀሉ Cordoba Fighting dog ከሚባል እስከሞት ድረስ መደባደብ ከሚወድ ውሻ ነው። ስለዚህ ይህ የውሻ ዝርያ እጅግ ታዋቂ ዝርያ ባይሆንም ድሮ ከነበረው Cordoba Fighting dog ከሚባለው ታዋቂ ተደባዳቢ የውሻ ዝርያ ስለተደቀለ ጡንቸኛ፣ ጠንካራ፣ በድብድብ ጊዜ ህመም የሚችል የውሻ ዝርያ ነው። እሄም የውሻ ዝርያ አሁን የጫካ አሳማዎች ለማደን ሰዎች የሚጠቀሙበት የውሻ ዝርያ ነው።

Dogo Argentino



4) Rottweiler:-

ይህ rottweiler የውሻ ዝርያ አደቃቀሉ ብዙ ከብት ለመጠበቅ ነው። እሱም ከብቶችን በስነስርአት ለማገድ በቂ ጥንካሬ አለው። ይህ የውሻ ዝርያ ጥንካሬ ብቻም ሳይሆን በቶሎ ተናዳጅነቱም ይታወቃል።


Rottweiler



3) The Carpathian Shepherd:-

ይህ the carpathian shepherd የሚባለው የውሻ ዝርያ በአብዛኛው በ Slovakia, Ukraine, Romania እና Serbia አካባቢ የሚገኝ ሲሆን በነዚሁም አካባቢ በጎች ለመጠበቅ ነው የተደቀለው። ከላይ በተጠቀሱት አካባቢዎች እረኞችን ተኩላ፣ የተራራ አንበሳ እና ድብ የመሳሰሉት እንስሳቶች በጎችን ስለሚይስስቸግሩ እሄ ጠንካራ የውሻ ዝርያ ተደቀለ።

The Carpathian Shepherd



2) The St. Bernard:- 

ይህ የውሻ ዝርያ የ Swiss ውሻ ነው። ይህ የውሻ ዝርያ በዋናነት የጠፉ የሃገር ጎብኚዎችን ፈልጎ ማግኘት ነው ስራው። እንደሚነገረው ከሆነ በረዶ የተናደባቸው ጎብኚዎችን ልብሳቸውን በአፉ ይዞ ምንም ከባድ ቢሆኑ ጎትቶ እንደሚያወጣቸው ይነገርለታል። ይህም ደግሞ ጥንካሬውን ያሳያል።

The St. Bernard



1) Kangal:-

ይህ የውሻ ዝርያ kangal የጥንት ዝርያ ሲሆን በመጀመሪያ የ ቱርክ ሃገር ውሻ ቢሆንም አሁን ወደ ኢስያ፣ አፍሪካ እና አውሮፓ ተሰራጭቷል። ይህ ውሻ ሰዎች ለዘበኝነት የሚጠቀሙት ውሻ ሲሆን እንዲሁ ውሻው የሀገራችንን አህያ ያክላል። ይህ ውሻ እጅግ በጣም ጠንካራ እና ንክሻውም ከሁሉ ውሻዎች በላይ ሃይል አለው። ይህ ውሻ በጣም ግዙፍ፣ ሃይለኛ እና ህመም ቻይ ከመሆኑ የተነሳ በወሬ ደረጃ ቢሆንም እንኳን ድቦችን፣ አንበሳዎችን፣ ነብሮችን ታግሎ አሸንፏል ተብሎ የተወራባቸው ጊዜያቶ አሉ። እንዲየውም አሁን እራሱ በ ኢንተርኔት እነዚህን አውሬዎች ታግሎ ሲገድል ቪዲዮ አለን የሚሉ ዌብሳይቶች አሉ። ስለዚህ ከሁሉም የውሻ ዝርያዎች እሄኛው Kangal የሚባለው ዝርያ በጥንካሬው እና በአደገኛነቱ ይበልጣል።

Kangal

1) ሶስተኛው የአሜሪካ ፕሬዚደንት Thomas Jefferson የግሉን አተረጓጎም የያዘ መጽሃፍ ቅዱስ ነበረው። እሱም ከመጽሃፍ ቅዱስ ምክንያታዊ ያልሆኑ ነገሮችን አስወግዶ ምክንያታዊ የሆኑትንና ጥሩ ስነምግባርን የሚያስተምሩ ነገሮችን የያዘ ነው።  መጽሃፍ ቅዱሱ በአብዛኛው የ ኢየሱስ ክርስቶስ መልካም ስመምግባርን የሚያስተምሩትን ቦታዎች በብዛት የያዘና በነሱ ያተኮረ ነው።  ዝርዝሩን እዚህ ያንብቡ 

2) በአሜሪካ ሀገር ቋንቋው እንግሊዝኛ ቢሆንም የምልክት ቋንቋ የጥቁሮችና የነጮች ይለያያል።
 ዝርዝሩን እዚህ ያንብቡ 

3) የማሌዥያ ሀገር መታወቂያ እንደ መታወቂያ ብቻ ሳይሆን እንደ መንጃ ፈቃድ፣ እንደ ATM Card፣ እንደ electronic purse እና እንደ public key ያገለግላል። ከዛም አልፎ እንደ ሌሎች ብዙ ነገሮች ያገለግላል።
 ዝርዝሩን እዚህ ያንብቡ 

4) ከ ሌኒን በኋላ የተተካው የሩሲያ ታላቁ መሪ ጆሴፍ ስታሊን Joseph Stalin የባንክ ዘራፊ ነበር።
 ዝርዝሩን እዚህ ያምብቡ 

5) አንዳንድ ባክቴሪያዎች radio wave ሊያመነጩና በ radio wave(ሬዲዮ ዌቭ) ም ደግሞ እርስ በእርስ ሊነጋገሩ ይችላሉ።
 ዝርዝሩን እዚህ ያንብቡ 


የአኗኗር ዘይቤዎ ምን ያህል የሰውነትዎት የመከላከያ አቅም ከበሽታ ሊከላከልዎት እንደሚችል ይወስናል።

ለጤንነት መጥፎ የሆኑ የአኗኗር ዘይቤዎችን ጥሩ በሆኑት በመተካት የመከላከያ አቅምዎትን ጤነኛና ጠንካራ አድርገው ሊያቆዩት ይችላሉ።

የትኞቹ ዘይቤዎች ለ ሰውነት የበሽታ መከላከያ አቅም ጥሩ እንደሆኑና የትኞቹ ደግሞ መጥፎ እንደሆኑ እንይ።

1) በቂ እንቅልፍ መተኛት:-

በቂ እንቅልፍ መተኛት ለሰውነት መከላከያ አቅማችን እጅግ አስፈላጊ ነገር ነው። ጥናቶች እንደሚያመለክቱት ከሆነ በቂ እንቅልፍ የሚያገኙ ሰዎች ከማያገኙት ይልቅ በበሽታዎች(እንደጉንፋን አይነት ቀላል በሽታዎችም ቢሆን) የሚያዙበት ጊዜ ያነሰ ነው።

ተመራማሪዎች በትክክል እሄ የሚባል እንቅልፍንና የሰውነት የመከላከል አቅምን የሚያገናኝን ነገር ገና ባያውቁም በእርግጥ የሚታወቀው ነገር በቂ እንቅልፍ መተኛት ለሰውነት መከላከያ አቅም በጣም ጠቃሚ እንደሆነ እና በቂ እንቅልፍ አለመተኛት የጭንቀት hormones በጣም ሰውነታችን ውስጥ እንዲለቀቁ እንደሚያደርግ እና የጭንቀት hormones ደግሞ ለሰውነት መከላከያ አቅም ጎጂ እንደሆኑ ነው።

2) ስፖርት መስራት:-

ስፖርት መስራት ለ በሽታ መከላከያ አቅም ብቻ ሳይሆን ለብዙ ነገር ይጠቅማል። ስፖርት መስራት ደግሞ እንቅልፍም በደንብ እንድንተኛ ይረዳል። በቀን ውስጥ 30 ደቂቃ ብቻ እራሱ መራመድ ትልቅ የጤና ጥቅም አለው።

3) የአመጋገብ ዘይቤ:-

ስኳር የበዛበት ምግብ መብላት ወይም ስኳር የበዛበት መጠጥ መጠጣት ባክቴሪያን የሚዋጉ የሰውነት ተከላካይ ሴሎችን ከተጠጣ በኋላ ለትንሽ ሰአታት ይቀንሳል። ስለዚህ ስኳር የበዛበት ነገር መብላት ብዙም አይመከርም።

ምግባችን አትክልትና ፍራፍሬ በርከት ያለበት፣ በ ቫይታሚን C ፣ በ ቫይታሚን E በ beta caroten እና zink የበለጸጉ ምግቦችን መብላት የሰውነታችንን  immune system ወይም መከላከያ አቅም ያዳብራል።

4) ጭንቀት:-

ብዙ መጨነቅ ሰውነታችን cortisol የሚባሉትን የጭንቀት hormomes ከልክ በላይ እንዲለቅ ያደርጋል። እኚህ hormones ደግሞ ለ immune system ወይም የመከላከያ አቅማችን መጥፎ ናቸው።

5) ከሰዎች ጋር ቅርርብነት:-

ለሰው መድሃኒቱ ሰው ነው ሲባል ሰምተን ልናውቅ እንችላለን። እውነትም ጥናቶች እንደሚደግፉት ከሆነ ሌሎች ነገሮችም አብረው ሚና ቢጫወቱም ከሰዎች መቀራረብ እና ማህራዊ ኑሮ ማዳበር የበሽታ ተጋላጭነትን ሊቀንስ ይችላል።

6) መሳቅ:-

መሳቅ ለሰውነታችንም ሆነ ለ ሰውነታችን immune system(የመከላከያ አቅም) ጥሩ ነው። መሳቅ የተወሰኑ የነጭ የደም ሴል አይነቶች በይበልጥ እንዲመረቱም ሊያደርግ ይችላል። ነጭ ደም ሴሎች ደግሞ በሽታን የሚዋጉልን ሰውነታችን ውስጥ ያሉ ወታደሮች ናቸው።


ከመጠን በላይ መብላት ምግብ ቶሎ እንዳይፈጭ በማድረግ ለሆድ መነፋፋትና ለቁንጣን ይዳርጋል። ይህ ደግሞ ምቾታችንን በማባረር ለጊዜውም ቢሆን እንድንጨናነቅ ያደርጋል። ይህ ጭንቀት በጊዜው ቢለቅም ለጊዜውም ቢሆን በጣም ሊያጨናንቀን ስለሚችል ቶሎ እንዲለቀን ለመሞከር የምንጠቀምባቸው ዘዴዎች ሊኖሩ ይችላሉ።

መጠቀም የምንችላቸውን ዘዴዎችን እንመልከት

1) ሆድ ላይ የሆነ ሙቅ ነገር ማስቀመጥ:-

ሆድ ላይ እንደ hot water bottle አይነት ነገር በሙቅ ውሃ ሞልተን ወይም የትኛውንም ሞቅ ያለ ነገር ሆዳችን ላይ ማስቀመጥ ለዚህ ችግር ጥሩ ረዳት ነው። በአብዛኛው ጊዜ ይሄ ዘዴ ከ ሃያ ደቂቃ በኋላ ሆዳችን ለቀቅ እንዲል ያደርጋል

2) ለ 30 ደቂቃ ያህል ጋደም ብሎ እረፍት መውሰድ:-

በእንደዚህ አይነት ጊዜ የሆዶቻችሁ ጡንቻዎች ምግብን በደንብ እንዲያዘዋውሩ ጊዜ እና እረፍት መስጠት አስፈላጊ ነው። ከዛም በኋላ ደግሞ በደንብ ወደውስጥ በመተንፈስ የተጨናነቁ የሆድ ጡንቻዎችን ማፍታታትም አስፈላጊ ነው።

3) ቀላል walk መውሰድ:-

ቀለል ያለ walk መውሰድ አንዳንዴ ምግብ ቶሎ እንዲፈጭ ይረዳል

4) ቶኒክ መጠጣት:-

በተለይ እንደ ስጋ አይነት ነገር በልተን ቁንጣን ከያዘን ቶኒክ ቶሎ እንዲፈጭልን ያግዛል።

5) ጭንቀቱ ከ 5 ሰአት በላይ ከቆየ ያለ ሃኪም ትእዛዝ የሚፈቀዱ antacid እና antigas መውሰድ

6) ጠንከር ያለ ዊስኪ ወይም አረቄ በትንሹ መጠጣት:-

ይሄ እራሱ በተለይ ስጋ ከልክ በላይ ከተበላ ጥሩ መፍትሄ ሊሆን ይችላል።


በ Newcastle University ሳይንቲስቶች በተገኘው የምርምር ውጤት መሰረት ላሞችን ስም ሰይሞ በስማቸው መጥራት፣ እንዳይፈሩና እንዳይደነግጡ ማድረግ እና እንደግለሰብ ማየት የወተት ውጤትን በ 3.5% ይጨምራል።

የላሞችን ጠቅላላ ፍርሃታቸውን መቀነስ ዘር አተካካቸውን፣ እድገታቸውን እና የበሽታ መከላከል አቅማቸውን ያሻሽላል። ይህ ብቻ ሳይሆን ላሞቹ ሰው ካልፈሩ እና ከሰው ጋር ከተላመዱ ሊታለቡ ሲሉ ወተታቸውን አይከለክሉም ይላል በ Anthrozoos journal የተዘገበው ጥናታዊ ዘገባ።

ጥናቱ እንደሚያሳየው ከሆነ ላሞችን በስም የሚጠሩ  እና የማይጠሩ በሁለት ተመድበው ተመሳሳይ የላም ዘር ኖርዋቸው እራሱ በስም የሚጠሯቸው ከማይጠሯቸው እጅግ የበለጠ የወተት ውጤት እንደሚያገኙ ጥናቱ አይቷል።

ይሄ በሳይንሳዊ መረጃ እንዴት ሊደገፍ ይችላል ቢባል ብዙም የማይጨነቁ እና ፈታ ብለው የሚያድጉ ላሞች cortisol የሚባለውን የጭንቀት hormone ብዙም አያመነጩም። Cortisol ሰውም ሆነ እንስሳ ብዙ ሲጨነቅ ሰውነት እራሱ የሚያመነጨው hormone ነው። Cortisol የሚባለው የጭንቀት hormone ደግሞ በሰውም ሆነ በእንስሳ በሰውነት የሚካሄደውን የወተት ምርትን እንደሚቀንስ ብዙ ሳይንሳዊ ጥናቶች ያረጋግጣሉ።






ጥንጥዬ ድብ የሚመስለው wolverine(ዉልቨሪን) በልኩና በመልኩ እንዲየውም የበለጠ የሚመስለው ከ አይጥ ትንሽ የሚበልጠውን እና ድመት የሚያክለውን weasel(ዊዝል) ነው። Wolverine(ዉልቨሪን) እራሱ የዊዝል ቤተሰብ ነው ይባላል። Wolverine(ዉልቨሪን) የሚያክለውም መካከለኛ ውሻን ነው።

እሄ ትንሽ እንስሳ ርዝመቱ(እስከነጭራው) 110 ሴንቲ ሜትር አካባቢ ሲሆን ክብደቱ ደግሞ ከ 9 - 25 ኪሎ ግራም አካባቢ ነው። ሪኮርዱ 33  ኪሎግራም ነው።

ዉልቨሪን የመብላት አቅሙ እጅግ በጣም ከፍተኛ ከመሆኑም በላይ ምህረት የለሽና እንደሚታየው ከሆነ የሚፈራው ነገር የለም ተብሎ ይታወቃል። ይህ ትንሽ ገዳይ እንስሳ ያለው ጉልበት ከአንዳንድ ትልልቅ ገዳይ እንስሳዎች እራሱ የሚስተካከልና ከአንዳንዱም ደግሞ የበለጠ ነው። እንዲየውም ድብን ከሚያክል አንበሳን እንኳን ሊያሸንፍ ከሚችል እንስሳ ግድያ ሊነጥቅ ቢያንስ አንዴ ሲተናነቅ  እንደታየ ይነገርለታል። እንደ ተኩላ አይነት እንስሳቶችማ ግድያቸውን ለመንጠቅ መተናነቁ ዘውትሮ ይታያል። እንደ ቀበሮ አይነት እራሳቸው አዳኝ የሆንትን እንስሳዎች ደግሞ በቀላሉ ገድሏቸው ይበላል። ደግነቱ ይሄ እንስሳ ብዙ ሰው አካባቢ የሚኖር ሳይሆን የአለማችን ሰሜናዊው ጫፍ በረዶአማ አካባቢ የሚባለው Arctic circle አካባቢ ነው የሚኖረው።

ይሄ እንስሳ Wolverine(ዉልቨሪን) እንደጅብ የአገጩ ጉልበት ሃይለኛ ከመሆኑ አንጻር የገደላቸውን እንስሳቶች አጥንትና ጥርስ ሳይቀር ቁርጭምጭም አድርጎ እንደሚበላ ይታወቃል። እሄ ብቻ ሳይሆን እሄ ከ 9 - 25 ኪሎግራም አካባቢ የሚመዝነው Wolverine(ዉልቨሪን) ብቻዎን ከ 200 ኪሎግራም በላይ የሚመዝኑትን አጋዘኖችና ከ 300 - 400 ኪሎግራም እንዲየውም ከዚያም በላይ የሚመዝኑትን elk (ኤልኮች) ገድሎ ይበላል።

እነዚህ ትንንሽ ገዳዬች በረዶ ላይ እንዲሮጡ የሚረዳ መሬት ሲረግጡ በራሱ ጊዜ እጥፍ ሆኖ የሚሰፋ እግሮች አሏቸው። ጥፍሮቻቸው ደግሞ ረዘም ያሉና እጅግ ሹል ናቸው። እሄም ደግሞ የሚገድሉትን እንስሳ ሲነክሱ ጥፍሮቻቸውን ሰክተውበት እንዲይዙት ያግዛቸዋል።

Wolverine(ዉልቨሪን) አይኖቻቸው ትንንሽ ቢሆንም ሩቅ እና በረዶ ውስጥ እራሱ በጥልቀት የተቀበረ ነገር ማሽተት የሚችል አፍንጫ አላቸው። Wolverine(ዉልቨሪን) የሚኖሩት ከ 4 - 7 አመት ያህል ቢሆንም እስከ 13 አመት ድረስም ሊኖሩ ይችላሉ።

Wolverine(ዉልቨሪን) እንደተኩላ በቡድን ሳይሆን ብቻውን የሚዞርና ብቻውን የሚያድን እንስሳ ነው። እሱም ስጋና የ አደን ምግብ ብቻ ሳይሆን እራሱ ያልገደለውን ጥምብ እና ከ ፍራፍሬ የሚመደበውንም berries ይበላል። የሚተኛው ከ 3 - 4 ሰአታት ያክል ሲሆን አንድ ወንድ Wolverine(ዉልቨሪን) ስኬታማ ከሆነ ከ 3 - 4 ሴቶች ይኖሩታል። ከነዚህም ሴቶች ጋር የህይወት ሙሉ አጋር ይሆናል። ወንድ Wolverine(ዉልቨሪን) ከሴት Wolverine(ዉልቨሪን) በርዝመትም ሆነ በክብደት 30% ያህል እንዲየውም ከዚያም በላይ ሊበልጥ ይችላል። እንደሚነገርላቸው ከሆነ ደግሞ ውይልቨሪኖች ጥሩ አባቶች ናቸው። ልጆቻቸው ሙሉ በሙሉ ጎልማሳ እስኪሆኑ ደግሞ ከሌኮች ዉልቨሪኖች ጋር አብረው ባያድኑም እራሱ ከልጆቻቸው ጋር አብረው ሊያድኑ ይችላሉ።



Posted via Blogaway




በአለማችን የመጀመሪያው እርጅናን የሚዋጋ መድሃኒት በአውሮፓዊያን ካላንደር መጪ አመት በሰዎች ላይ ሙከራ መደረጉን ይጀምራል። የዚህም ሙከራ ውጤት ደግሞ ሰዎች ከፈለጉ በጥሩ ጤንነት እስከ 120 አመት ድረስ እንዲኖሩ ሊያደርግ የሚችል ሊሆን ይችላል ይላል "The New Zealand Herald" ጋዜጣ።

ሳይንቲስቶች አሁን ሰዎች ቶሎ እንዳያርጁ መከላከል እንደሚቻልና Alzheimer's እና Parkinson's የሚባሉ በሽታዎችን ደግሞ ታሪክ ማድረግ እንደሚቻል ያምናሉ።

አሁን ባለንበት ጊዜ እውነት መስሎ ላይታይ ቢችልም ተመራማሪዎች metformin የሚባለው የስኳር በሽታ መድሃኒት የእንስሳቶችን እድሜ እንደሚያራዝም በማስረጃ አረጋግጠዋል። ስለዚህም የአሜሪካ ምግብ እና መድሃኒት ተቆጣጣሪ አካል "food and drug administration" ይህ መድሃኒት ሰው ላይም ተመሳሳይ ውጤት ያሳይ እንደሆን እንዲመረመር ሙከራው መጪ አመት እንዲጀምር ፈቃድ ሰጥቷል።

ይህ ውጤታማ ከሆነ የ 70 አመት ሰው በጤንነት እና በሰውነት ወጣትነት ከአሁኑ ከ50 አመት ሰው ጋር ተመሳሳይ ይሆናል ማለት ነው።

ሳይንቲስቶች እንደሚሉት ከሆነ ማርጀት ማምለጥ የማንችለው የህይወት ዱብዳ አይደለም። እንዲየውም አንዳንድ የባህር እንስሳቶች እንደማያረጁና በእድሜ ምክንያት ጭራሽ የሰውነት ድክመት እንደማያሳዩ ይገልጻሉ።

ይህ ሙከራ ውጤታማ ከሆነ እርጅናን ብቻ ሳይሆን ከእርጅና ጋር ተያይዘው የሚመጡ በሽታዎችንም አብሮ ይከላከላል ተብሎ ይገመታል። ስለዚህ አንድ ህጻን ልጅ አሁን ሲወለድ ይኖራል ተብሎ የሚጠበቀውን እድሜ 50 በመቶ ይጨምራል ተብሎ ይታመናል።



Posted via Blogaway