ብዙ ባለሙያዎች እንደሚናገሩት ከሆነ 20% የሚሆኑ ወንዶች የሚመለጡት እድሜአቸው ከ 20 - 30 ዓመት ሲሆን ነው።

የራስ በረሃነትን ሊያመጡ የሚችሉ ብዙ ነገሮች ቢኖሩም ዘር ዋነኛው መንስዔ ነው ተብሎ ቢታወቅም ባለቤቱም እንዳይከሰት የተወሰኑ ውጤት ሊኖራቸው የሚችሉ ሙከራዎችን ሊያደርግ ይችላል።

ስለዚህ አሁን ራሰ በረሃነትን ሊከላከሉ የሚችሉ የምግብ ዓይነቶችን እንይ።

1) በOmega 3 fatty acids የበለጸጉ ምግቦች:-

Omega 3 fatty acids ፀጉርንና ፀጉር የሚበቅልበትን የራስ ቆዳን ለጤነታቸው በሚጠቅሙ ንጥረ ነገሮች ይመግባሉ። ፀጉራችንም ደግሞ እንዳይበጣጠስና እንዳይነቃቀል ይረዳሉ።

በ omega 3 fatty acids የበለፀጉ ምግቦች  ለውዝ(ከተቻለ wallnuts)፣ tuna(ቱና የአሳ ዘርያ)፣ salmon፣ kale፣ የአሳ ዘይት፣ ቆስጣ ከዋና ዋናዎቹ አንዳንዶቹ ናቸው።

2) በ zink የበለጸጉ ምግቦች:-

Zink ፀጉራችን የሚበቅልበት የራስ ቆዳ ሴሎች በስርአቱ renewed እንዲሆኑ ወይም እንዲተካኩ አስተዋጽኦ ያደርጋል። ፀጉርም እንዲያድግ የሚያደርጉ ሆርሞኖች ሰውነታችን በበቂ ሁኔታ እንዲያመርት ያግዛል።

በ zink የበለጸጉ ምግቦች ሽምብራ፣ ስንዴ፣ የበሬ ስጋ(ቀይ)፣ የበግ ስጋ(ቀይ)፣ እንደ ቆስጣ አይነት ጥቁር ቅጠል ያላቸው አታክልቶች፣ የዱባ ፍሬ፣ ለውዝ፣ ቾኮሌት ከዋና ዋናዎቹ አንዳንዶቹ ናቸው።

3) በፕሮቲን የበለጸጉ ምግቦች:-

ጸጉራችን በአብዛኛውኑ ከ ፕሮቲን የተሰራ እንደሆነ ባለሙያዎች ይነግሩናል። ስለዚህ በቂ ፕሮቲን መብላት ራሰ በረሃነት እንዳይከሰት ሊረዳ ይችል ይሆናል ተብሎ ይታሰባል።

በፕሮቲን የበለጸጉ ምግቦች እንቁላል፣ የትኛውም ስጋ(ቀይ)፣ ባቄላ፣ ምስር፣ አተር፣ አሳ፣ እርጎ፣ ዶሮ ከዋና ዋናዎቹ አንዳንዶቹ ናቸው።

4) በ Iron(ብረት) የበለጸጉ ምግቦች:-

Iron(ብረት) ደማችን በደንብ እና በበቂ ሁኔታ ወደ ሁሉ የሰውነታችን ክፍሎች እንዲደርስ ያደርጋል። ስለዚህ ደምና በደም ውስጥ ያሉ ለፀጉር ዕድገት አስፈላጊ ንጥረ ነገሮች ፀጉራችን ወደሚበቅልበት የራስ ቆዳ ለማድረስ አስፈላጊ ከሆኑ ነገሮች የአንበሳ ድርሻውን ይጫወታል።

በ Iron(ብረት) የበለጸጉ ምግቦች እንደ ቆስጣ ያሉ ጥቁር ቅጠል ያላቸው አታክልቶች፣ እህላ እህሎች፣ ቀይ ስጋ፣ የበሬ ጉበት፣ የዶሮ ጉበት፣ ሳርዲንስ(በቆርቆሮ የታሸገ)፣ tuna(ቱና)፣ እንጀራ ከዋና ዋናዎቹ አንዳንዶቹ ናቸው።

5) በ ቫይታሚን A እና C የበለጸጉ ምግቦች፡-

ሁለቱም ቫይታሚኖች A እና C sebum የሚባል ንጥረ ነገር ሰውነታችን እንዲያመርት ይረዳሉ። እሱም ደግሞ ፅጉራችን እንዳይቀነጣጠስንስ እንዳይነቃቀል ይረዳል። ግን በተለይ ቫይታሚን A በተለይ በኪኒን መልኩ ከተወሰደ ከልክ(500 IU በቀን) ማለፍ የለበትም። አለበለዚያ ከሚፈለገው ውጤት(የፀጉር) ተቃራኒ ውጤት ሊያመጣብን ይችላል።

በ ቫይታሚን A የበለጸጉ ምግቦች ካሮት፣ ቆስጣ፣ ስኳር ድንች፣ ዱባ፣ ሰላጣ፣ melon፣ tuna፣ ማንጎ፣ ከዋና ዋናዎቹ አንዳንዶቹ ሲሆኑ

በቫይታሚን C የበለጸጉ ምግቦች ደግሞ ብርቱካን፣ ሎሚ፣ በተፈጥሮ ኮምጠጥ ያሉ ፈራ ፍሬዎች፣ የቃሪያ ዘሮች፣ ዘይቱን፣ እንደ ቆስጣ ያሉ ጥቁር ቅጠል ያላቸው አታክልቶች፣ ቲማቲም ከዋና ዋናዎቹ አንዳንዶቹ ናቸው።

6) በ magnesium የበለጸጉ ምግቦች:-

Magnesium ለሰውነታችን አስፈላጊ ለሆኑ 300 bio chemical reaction ኦች ወሳኝ እገዛ የሚያደርግ ንጥረ ነገር ነው። ከነዛም አንዱ የጸጉር እድገትን የሚያግዝ biochemical reaction ነው።

በ magnesium የበለጸጉ ምግቦች ለውዝ፣ ቆስጣ፣ ምስር፣ ሙዝ፣ አኩሪ አተር፣ የዱባ ፍሬ ከዋና ዋናዎቹ አንዳንዶቹ ናቸው።

7) በ selenium የበለጸጉ ምግቦች:-

Selenium ፀጉር በደንብ እንዲያድግ stimulation ይፈጥራል ብለው ባለሙያዎች ይናገሩለታል።

በ selenium የበለጸጉ ምግቦች ለውዝ፣ tuna፣ አሳ፣ የአሳማ ስጋ፣  የስንዴ ዳቦ፣ የበሬ/የበግ ስጋ(ቀይ)፣ የዶሮ ስጋ(እግር)፣ እንጉዳይ ከዋና ዋናዎቹ አንዳንዶቹ ናቸው።



Posted via Blogaway


የተሻለ የአመጋገብ ዘይቤ በመከተል ሰው በዕድሜው ላይ ዓመታት ሊጨምር ይችላልን?

መልሱ አዎ ነው።

ከእግዚአብሔር ጋር ሆንው ሰው ስንት ዓመት እንደሚኖርና በስንት ዓመቱ እርጅና ላይ እንደሚወድቅ ሊወስኑ የሚችሉ ብዙ ነገሮች አሉ። ግን በቂ እንቅስቃሴ ማድረግ፣ ጥሩ የአኗኗር ዘይቤ መከተልና የተሻለ የአመጋገብ ዘይቤ መከተል እርጅና ቶሎ እንዳይመጣና ከዕድሜ ጋር አብረው የሚመጡ በሽታዎችን ለመከላከል ይረዳሉ።

ከአመጋገብ አንጻር ስናየው በ antioxidents የበለጸጉ ምግቦች ቶሎ እንዳናረጅ እና ከዕድሜ ጋር የሚመጡ በሽታዎችን ለመከላከል ጥሩ አስተዋጽኦ ያደርጋሉ።

እነዚህ ምግቦች እነማን እንደሆኑ በሚከተለው እንይ።

1) የወይራ ዘይት:-

የወይራ ዘይት polyphenols በተባሉ antioxidents የበለጸገ በመሆኑ ከእርጅና ጋር አብረው ከሚመጡ በሽታዎች ለመከላከል ይረዳል ተብሎ በባለሙያዎች ይታመናል።

2) እርጎ:-

እርጎ ቶሎ እንዳናረጅ እንዴት በቀጥታ እንደሚረዳ ይህ ነው የተባለ መረጃ እስከአሁን ባይኖርም እርጎ በ ካልሲየም የበለጸገ፣ osteoporosis የተባለ ከእርጅና ጋር በተጓዳኝ የሚመጣ የአጥንት በሽታን እንደሚከላከል፣ በጠቃሚ ባክቴሪያዎች የበለጸገ መሆኑና ጠቅላላ የአንጀት ጤንነትን ለመጠበቅ ከፍተኛ አስተዋጽኦ እንደሚያደርግ ይታወቃል።

3) አሳ፡-

አሳ በ omega 3 fats የበለጸገ፣ artery ላይ  colesterol እንዳይመረግ የሚረዳና ልብ ትክክለኛ የምት rythem እንዲኖረው እንደሚረዳ ይታወቃል።

አሳ በብዛት የሚበላባቸው አካባቢ የሚኖሩ ሰዎች የማይበላባቸው አካባቢ ከሚኖሩ ሰዎች ጋር በአንፃራዊነት ሲታዩ በአስገራሚ ሁኔታ የትኛውም አይነት የልብ በሽታ ተጠቂ የሆኑት እጅግ ጥቂት መሆናቸው በጥናቶች ታይቷል።

4) ቾኮሌት:-

የቾኮሌት ዱቄት (cocoa) flavanols በሚባሉ ንጥረ ነገሮች የበለፀገ ስለሆነ የደም ትቦዎቻችን በስነስርዓት ስራቸውን እንዲሰሩ ይረዳል።

ስለዚህ በደም ግፊት፣ በ type 2 የስኳር በሽታ፣ በኩላሊት በሽታና dementia በተባለ በሽታ እንዳንያዝ ይረዳል።

እዚህ ላይ ማወቅ ያለብን ነገር የቾኮሌት ዱቄት ስኳር ያልተጨመረበት ወይም ያልበዛበት መሆን አለበት። አለበለዚያ ግን ለሌሎች የጤንነት ችግሮች ሊዳርግ ይችላል።

5) የለውዝ(ኦቾሎኒ) ዘሮች (nuts):-

Nuts በ unsaturated fats የበለጸጉ ሲሆኑ የወይራ ዘይት ከሚሰጣቸው ጥቅሞች ተመሳሳይ ጥቅሞች ይሰጣሉ።

ከዛም በተረፈ በ ቫይታሚኖች፣ ሚኒራሎች እና antioxidents የበለጸጉ ናቸው።

6) ወይን(የአልኮሆል መጠጥ):-

አልኮሆል በመጠኑ ከተጠጣ ከልብ በሽታ፣ የስኳር በሽታና ከእድሜ ጋር በተያታዥነት ከሚመጣ memory loss ለመከላከል እንደሚረዳ በባለሙያዎች ይነገርለታል።

ወይን(የአልኮሆል መጠጡ) resveratrol የሚባል ንጥረ ነገር ይገኝበታል። እሱም ደግሞ ሴሎቻችን ቶሎ እንዳያረጁ የሚረዱ ጂኖችን activate ያደርጋል ተብሎ በባለሙያዎች ይታመናል።

7) blueberries ካልተቻለ የወይን ዘለላ:-

Blueberries በ antioxidents የበለጸጉ፣ ከእድሜ ጋር በተያያዥነት ከሚመጡ በሽታዎች ለመከላከል እንደሚረዱና ሴሎቻችን ቶሎ እንዳያረጁ የመርዳት አቅም እንዳላቸውም ይታመናል።



Posted via Blogaway


ለስላሳ ቆዳ እንዲኖሮት ይፈልጋሉ? ፊትዎት እንደ ህፃን ልጅ ቆዳ  ልስልስ ያለ እንዲሆንና እንዳይጨራመት ይፈልጋሉ?

ውበት በአብዛኛው ጊዜ ከጠቅላላ የሰውነት ጤንነት ጋር ተያያዥነት እንዳለው አይርሱ።
በአብዛኛው ጊዜ ደግሞ ለጤንነት ተፈጥሮአዊ ነገሮች ተመራጭ ናቸው።

አሁንም ደግሞ በተፈጥሮአዊ መንገድ ቆዳዎት ልስልስ እንዲሆን በአመጋገብዎት እርምጃዎትን ይጀምሩ።

የአመጋገብ እርምጃዎቹም የሚከተሉት ይሁኑ።

1) የለውዝ ዘሮችን(nuts)(ከተቻለ wallnuts ወይም almonds) መብላት:-

የለውዝ ዘሮች በተለይ almonds እና wallnuts በ vitamin B complex የበለፀጉ ሲሆኑ የቆዳ restoration(መልሶ እራሱን መተካት) በሥነስርዓቱና በጊዜው እንዲሆን ጥሩ አስተዋፅኦ ያደርጋሉ። ከዛም አልፎ ቆዳችን ደረቅ እንዳይሆን ይረዳሉ። ቆዳችን የወጣትን texture እንዲይዝም ይረዳሉ።

ስለዚህ ለውዝ ከተቻለ almonds ወይም walnuts እንደመክሰስ በልኩ ማዘውተር ጥሩ እርምጃ ነው።

2) cheese(አይብ) ከተቻለ swiss cheese ወይም cheddar cheese መብላት:-

3) የወይን ዘለላ መብላት:-

ወይን  በተፈጥሮ anti aging(እርጅናን የሚዋጋ) ነጥረ ነገር ካላቸው ምግቦች ዋነኛው ነው ተብሎ ይታወቃል።  ስለዚህ ቆዳችን እንዳይጨረማመትና ያረጀን እንዳንመስል አስተዋጽኦ ያደርጋል።

4) አቮካዶ መብላት:-

አቮካዶ በ fatty acid የበለጸገ ምግብ ነው። እናም ቆዳችን እንዳይደርቅና ለስላሳ እንዲሆን ይረዳል።

5) Tuna ወይም Salmon የተባሉትን የአሳ ዝርያዎች መብላት:-

Salmon በሀገራችን ላይ እጅጉን የሚገኝ ባይሆንም Tuna ግን በተለይ በቆርቆሮ ታሽጎ እንደ ልብ ይገኛል።

Tuna እና Salmon የሚባሉት የአሳ ዝርያዎች በ omega 3 fatty acids እና በ vitamin D የበለጸጉ ምግቦች ናቸው።

Vitamin D ቆዳ fresh እንዲሆንና በአጠቃላይ ጤናማ መልክ እንዲኖረው ይረዳል።

6) አረንጓዴ አታክልቶችን መብላት:-

አረንጓዴ አትክልቶች በተለይ spinach(ቆስጣ), brochilli እና asparagus የመሳሰሉት በ vitamin E የበለጸጉ ምግቦች ሲሆኑ vitamin E የቆዳ elasticity (ተለጣጭነት) ጠንካራ እንዲሆን ይረዳል። ስለዚህ ቆዳችን እንዳይላላ፣ እንዳይጨራመት እና ጠንካራ ሆኖ እንዲቆይ አስተዋጽኦ ያደርጋል። Vitamin E የቆዳ ሴሎች እራሳቸውን እንዲተኩም ጥሩ አስተዋጽኦ ያደርጋል።

7) ነጭ ምግቦች መብላትን መቀነስ:-

እንደ ነጭ ስኳር እና ፊኖ ዱቄት የመሳሰሉት ነጭ ምግቦች ነጭ ባልሆኑት መተካት። ለምሳሌ ነጭ ሩዝን በ brown ሩዝ፣ ነጭ ድንችን በስኳር ድንች፣ ነጭ ስኳርን በ brown ስኳር፣ ፊኖ ዱቄትን በ ሙሉ ስንዴ ዱቄት ብዙውን ጊዜ መተካት ለቆዳችን ልስላሴ ጥሩ እርምጃ ነው።

8) ውሃ በደንብ መጠጣት:-

ውሃ እና ተፈጥሮአዊ ጁሶች ወይም ጭማቂዎች (ፋብሪካ ያልገቡ እና ስኳር እና ኬሚካል ያልገባባቸው) ለቆዳ ልስላሴ ጥሩ አስተዋጽኦ አላቸው።

9) Processed foods(ፋብሪካ ገብተው የተቀያየሩ ምግቦች) አለብላት ወይ መጠቀም መቀነስ

10) ለስላሳ መጠጦች (እንደ ኮካ ፔፕሲ...) መጠቀምን መቀነስ።



Posted via Blogaway


CD/DVD ዲስክ ስክራች ከሆነ ወይም በጣም በእጅ ከተነካካ የምንወደውን ዘፈን እየሰማን ወይም የምንወደውን ፊልም እያየን ቀጥ ሊልብን ወይም ሊዘልብን ይችላል።

አንዳንድ ጊዜ የዲስክ ስክራች ሊታከም ከሚችልበት ገደብ አልፎ መታከም ወይም መስተካከል ባይችልም እንደዚሁ አንዳንድ ጊዜ ደግሞ ቤት ውስጥ እራሱ በራስዎት እጅ ሊታከም ይችል ይሆናል።

ስለዚህ የዲስክ ስክራችን እራሳችን እንዴት ማከም እንደምንችል አነሆ።

1) ዲስኩን ማፅዳት:-

አንዳንድ ጊዜ ዲስኩ ባይፋቅ እንኳን አቧራ፣ የእጅ አሻራ፣ ቅባት፣ እድፍ የመሳሰሉ ነገሮች ዲስኩ በአግባቡ እንዳይጫወት ሊያሰናክሉ ይችላሉ።

ስለዚህ ዲስኩን(የውስጡን በኩል) ማፅዳት መቼም ቢሆን የመጀመሪያ አማራጭ መሆን አለበት።

ዲስኩን ሲያፀዱ

- ትንሽ ለብ ያለ ውሃ ዲስኩ ላይ አፍስሱ

-  እድፍ ያለበት ቦታ ካለ ለብ ያለ ውሃ ላይ ፈሳሽ ሳሙና አደባልቀው በጣትዎት ያቺን ቦታ አሸት አሸት ያድርጉና ለብ ባለ ውሃ ለቅለቅ አድርጉት

- ዲስኩ እንዲደርቅ ውሃውን በደንብ ያራግፉና አየር እንዲያደርቀው ጠብቁ

- ከደረቀ በኋላ ዲስኩን ከተው ሞክሩት።

- ሌላ ዲስክ የማፅዳት ዘዴ አልኮሆል ውስጥ ጥጥ ነከር አድርገው ዲስኩን(የውስጡን በኩል) ጠረግ ጠረግ ማድረግ ነው።

ዲስክ ሲጠርጉ ሁሌም ከመሃል ጀምረው ወደጫፍ (ከ ውስጥ ወድ ውጭ) በሆነ አቅጣጫ መሆን አለበት። በመሃሉ ዙሪያ እጅዎትን እያሽከረከሩ ካፀዱ(circular motion) ከሆነ ዲስኩ የበለጠ ሊበላሽ ይችላል።

2) CD/DVD ዲስኩን በሌላ ዲስክ መገልበጥ:-

አንዳንድ ጊዜ ዲስኩን በሌላ ዲስክ መገልበጥ ጥሩ የማከሚያ ዘዴ ሆኖ ሊገኝ ይችላል።

ዲስክ ለመገልበጥ Nero ተመራጭ software ነው።

3) የሚከተለውን ዘዴ ከተጠቀሙ ዲስኩ የበለጠ ሊበላሽ የሚችልበት አጋጣሚ ለፈጠር እንደሚችል መጀመሪያ ይገንዘቡ።

- የጥርስ ሳሙና (tooth paste) (paste እንጂ jell እንዳይሆን ተጠንቀቁ)። ( jell ከእቃው ሲጨመቅ እንደ ፀጉር ጄል አይነት መልክ ያለው ነው)

- ትንሽ ዲስኩ(የውስጡ በኩል) ላይ ጨመቅ አድርገው ያኑሩ።

-የመነፅር መጥረጊያ ጨርቅ ያዘጋጁና የጥርስ ሳሙናውን ከመሃል ወደጫፍ(ከውስጥ ወደ ውጭ) በሆነ መስመር ይሹት። (በመሃሉ ዙሪያ በ circle motion ካሹ ዲስኩ የበለጠ ሊበላሽ ይችላል)

- ከ 10 - 12 ጊዜ እንደዚህ በተደጋጋሚ እሹ

- ዲስኩን በጣም ጫን እንዳይሉት ተጠንቀቁ

- ሲጨርሱ ዲስኩን ትንሽ ለብ ባለ ውሃ አለቅልቁና ዲስኩ በአየር እስኪደርቅ ጠብቀው ከደረቀ በኋላ ከተው ይሞክሩት።

- እንደዚህም ሆኖ ካልሰራ እንደገና በጥንቃቄ በ tooth paste ለ 15 ደቂቃ በተመሳስስይ መንገድ አሽተው በተመሳሳይ መንገድ አለቅልቀውና አድርቀው ይሞክሩ

4) የሚከተለው ዘዴ ጊዜአዊ መፍትሄ ነው። ይህ ዘዴ ከሰራልዎት ወድያው በሌላ ዲስክ ይገልብጡት ወይም copy ያድርጉት

- ዲስኩን(የውስጡን በኩል) ቫዝሊን ወይም chap-stick በቀጭኑ ቀቡት

- ደረቅ ሲል ቫዝሊኑን ወይም chap-stick በንፁህ ጨርቅ ጠረግ ጠረግ አድርጉት

- ከዛ ዲስኩን ከተው ይሞክሩት

- ይህ ዘዴ ከሰራልዎት ይህ ዘዴ ጊዜያዊ መፍትሄ ስለሆነ ወዲያው በሌላ ዲስክ copy አድርጉት።


ካንሰር አደገኛና እስከሞት ድረስ ሊያደርስ የሚችል በሽታ እንደሆነ ይታወቃል።

ካንሰር በተለያዩ አይነት ምክንያቶች ሊነሳ ይችላል። ካንሰር እንዳይነሳብን እድሉን ለማጥበብ ማድረግ የምንችላቸው ነገሮች ቢኖሩም እንደማይዘን 100% የሚያረጋግጥልን መፍትሄ የለም።

ለማንኛውም በካንሰር የመያዝ ዕድልን ለመቀነስ አብዛኞቹ ባለሙያዎች የሚስማሙበት የአኗኗር ዘይቤን ማስተካከል ነው በሚል ነው።

ስለዚህ በካንሰር የመያዝ ዕድላችንን ለመቀነስ እነዚህ ልንከተላቸው የሚገባቸው ቀላል የአኗኗር ዘይቤዎች ምን ይመስላሉ።

1) ከትንባሆ መራቅ:-

ይህ አለማጨስ፣ ትንባሆ አለማኘክ ወይም ደግሞ የሚጨስበት አካባቢ አለመሆንን ያካትታል።

ማጨስ ከብዙ አይነት የካንሰር አይነቶች ጋር ግንኙነት እንዳለው መረጃዎች ያሳያሉ። ከነዚህ ውስጥ በገዳይነቱ በጣም የሚታወቀው የሳምባ ካንሰር ነው።

ትንባሆ ማኘክም እንደዚሁ በተለይ ለአፍ ካንሰር እንደሚዳርግ መረጃዎች ያሳያሉ።

ሲጋራ የሚጨስበት አካባቢ መሆንም በሳንባና በሌሎች አይነት ካንሰሮችም የመያዝ እድልን ይጨምራል ተብሎ ይታሰባል

2) ጤነኛ የአመጋገብ ዘይቤን መከተል:-

ጤነኛ የአመጋገብ ዘይቤን መከተል በጠቅላላው በካንሰር እንዳንያዝ አስተዋጽኦ አለው ተብሎ ይታመናል።

ጥሩ የአመጋገብ ዘይቤ

- ጠቅላላ አመጋገብን በአትክልት፣ ፍራፍሬ፣ ጥራጥሬ እና እህላ እህሎች የተመሰረተ ማድረግ(ለውዝ ሳይበዛ ጥሩ ነው)

- ከመጠን በላይ አለመወፈር ወይም የሚያወፍሩ ምግቦችን አለማዘውተር

- አልኮሆል(የሚያሰክሩ መጠጦች) የሚጠቀሙ ከሆን በልኩ መጠቀምን ያካትታል።

3) ዘወትር እንቅስቃሴ ማድረግ:-

እንቅስቃሴ ማድረግ ጤነኛ የክብደት መጠን እንዲኖረን ከሚያደርገው አስተዋጽኦ አልፎ እሱ እራሱ እንደ ጡት ካንሰር እና ሌሎች አንዳንድ የካንሰር አይነቶች እንዳይነሱ አስተዋጽኦ ያደርጋል ተብሎ ይታመናል።

4) እንደ hepatitis B እና HPV ላሉ በሽታዎች ከተቻለ ክትባት መውሰድ:-

Hepetitis B የጉበት ካንሰር እንዲነሳብን እስተዋጽኦ ያደርጋል ተብሎ ይታመናል። HPV ደግሞ የብልት ካንሰርና ኪንታሮት እንዲነሳ አስተዋጽኦ ያደርጋል ተብሎ ይታመናል። ስለዚህ ከተቻለ በተለይ አኗኗሮ ለነዚህ በሽታዎች ተጋላጭ የሚያደርግ አይነት ከሆነ አስቀድሞ ክትባት መውሰድ ካንሰርን ከመከላከያ መፍትሄዎች አንዱ ነው ተብሎ ይታሰባል።

5) ከአንዳንድ አደገኛ ባህሪይዎች መቆጠብ፡-

ለምሳሌ የግብረስጋ ግንኙነት ሲያደርጉ ወይ መቆጠብ ወይ መጠቀም። ምክንያቱም እንደ HIV እና HPV አይነት ጥንቃቄ ከጎደለው የግብረስጋ ግንኙነት ሊከሰቱ የሚችሉ በሽታዎች ለ ብልት፣ ጉበት፣ ሳንባ ካንሰርና ለኪንታሮት ተጋጭለታችንን ያሰፋሉ ተብሎ ይታመናል።

ሌላም ደግሞ መርፌን አለመጋራት ከጥንቃቄዎቹ አንዱ ነው።

6) regular checkup (ተለምዶአዊ የጤነት ክትትል) ማድረግ:-

በዓመት ወይ በሁለት ዓመት አንዴ ጠቅላላ የጤነት ምርመራ(ካንሰርንም ሊያጋልጥ የሚችል) ቢደረግ አንዳንድ እንደጡት ካንሰር አይነት የካንሰር አይነቶች በእንጭጭነታቸው ከታወቁ ሙሉ በሙሉ የመዳን ወይም ሳይከሰቱም የመክሸፍ እድላቸው እጅግ ከፍተኛ ስለሆነ regular checkup ካንሰር እንዳይከሰት ወይም ሳይሰራጭ እንዲቀጭና እንዲድን እጅግ ከፍተኛ ጠቀሜታ ያለው መፍትሄ ነው።



Posted via Blogaway




የዘወትር ድካም ችግር ካለብዎት በአብዛኛው ጊዜ በዋናነት የአኗኗር ዘይቤን መቀየር ፍቱን መፍትሄ ነው።

እንቅስቃሴ ማድረግ፣ መውሰድ የሌሉብን ነገሮች አለመውሰድ፣ በቂ እረፍት መውሰድ እና ለጤነት ተስማሚ ምግብ መብላት ከአኗኗር ዘይቤ መቀየር ዋና ዋናዎቹ ናቸው።

በተፈጥሮአቸው ደግሞ የድካም ስሜትን ሊዋጉልን የሚችሉ የምግብ አይነቶችም አሉ።

እነሱን እንመልከት

1) በ magnesium የበለፀጉ ምግቦች:-

ከነሱም

- ሙዝ

- አሳ

- ለውዝ

- የደረቁ ፍራፍሬዎች

- አቮካዶ

- ቆስጣ እና ጥቁር ጎመን

- የዱባ ፍሬ

- እህላ እህሎች

ይገኙበታል

2) በ  vitamin b 12 የበለፀጉ ምግቦች

ከነሱም

- የበሬ ጉበት

- አሳ

- አኩሪ አተር

- ቀይ የበሬ ስጋ

- አይብ(ከተቻለ የፈረንጅ ከተቻለም ደግሞ
swiss cheese)
- እንቁላል

- ወተትና እርጎ

ይገኙበታል

3) ድካሞት በ iron(ብረት) እጦት ሊሆን ስለሚችል በ iron(ብረት) የበለፀጉ ምግቦች

ከነሱም

- የዱባ ፍሬ

- የዶሮ/የበሬ ጉበት

- ለውዝ

- ቀይ የበሬ ወይም የበግ ስጋ

- ባቄላ ወይም ምስር

- እህላ እህሎች

- ቆስጣና ጥቁር ጎመን

- ጥቁር ቾኮሌት

- አኩሪ አተር

- ኮኮነት

ይገኙበታል

4) በ omega 3 fatty acids የበለፀጉ ምግቦች

ከነሱም

- የዓሳ ዘይት

- ዓሳ(ቢቻል ሳልሞን)

- ለውዝ

- ኦራጊኖ ቅመም

- ቆስጣ

- የወይራ ዘይት

- አኩሪ አተር

- ማዮኔዝ

- የአሳማ ስጋ

- ዶሮ(እግር)

- እንቁላል፣ ወተት፣ ቅቤ

- በሬ(ጎድን)

ይገኙበታል



Posted via Blogaway




ለጤንነታችን መጥፎ ወይም ጎጂ የሆኑ ነገሮችን በአብዛኛው ጊዜ እናውቃለን ብለን ልንገምት እንችላለን። ግን አንዳንዴ ያልጠበቅናቸው ነገሮች ለኛ መጥፎ ሆነው ሊገኙ ይችላሉ።

እናም ከነዚህ ውስጥ አንዳንዶቹን በሚከተለው እንመለከታለን።

1) ርካሽ የፀሓይ መነፅሮች:-

አንዳንድ ophthalmologists እንደሚያስረዱት ከሆነ ከ UVA እና ከ UVB ጨረሮች የመከላከል አቅም የሌለው የፀሓይ መነፅር ከሚያደርጉ ጭራሽ ባያደርጉት ይሻላል ነው የሚሉት ባለሙያዎቹ።

ባለሙያዎቹ ሲያስረዱ ለዚህ ምክንያቱ ሃይለኛ ብርሃን ወዳለው ነገር ስንመለከት በተፈጥሮ አይናችንን ጭምት አድርገን ቢያንስ የሚገባውን የጨረር ብዛት እንቀንሳለን። ግን የፀሓይ መነፅር ካደረግን የብርሃን ብዛት ስለማይኖር እንደዛ አናደርግም። ግን በአብዛኛው ሃይለኛ ብርሃን የሚያመነጩ ነገሮች በዛውም ለአይን ጤንነት ጥሩ ይስልሆንትን UVA እንስ UVB የሚባሉትን ጨረሮችንም እንደዚሁ በሃይል ያመነጫሉ። እና ብዙዎቹ የፀሓይ መነፅሮች ብርሃንን ይቀንሳሉ እንጂ እነዚህን UVA እና UVB የሚባሉትን ለአይን ጎጂ የሆኑትን ጨረሮች አይከላከሉም።

እናም ባዶአችንን ብንሆን አይናችንን ጭምት አድርገን ቢያንስ የነዚህን ጨረሮች መጠን ልንቀንስ እንችላለን። ግን እነዚህን የማይከላከሉ የፀሓይ መነፅሮች ካደረግን ግን አይናችን ብዙ ብርሃን ያለ ስለማይመስለው ጭምት አይልም። በዛውም እነዚህ ጎጂ ጨረሮች አይናችን ውስጥ አንዳለ እንዲገቡ እናደርጋለን ማለት ነው።

2) ብዙ ውሃ መጠጣት:-

ይሄ ነጥብ ምናልባት አንዳንድን ሰው ሊገርመው ይችላል። ለምን ቢባል ብዙ ጊዜ የጤና ምክር ሲሰጥ በዛ ያለ ውሃ ጠጡ ይባላል።

በቀን ውስጥ በአማካይ ከ 1.6 ሊትር እስከ 2 ሊትር ውሃ መጠጣት ለጤና ጥሩ ነው። ግን ከዛ በጣም የበለጠ ውሃ መጠጣት ለጤና ጥሩ ላይሆን ከመቻሉ አልፎ በጣም ከበዛ ሊገል ሁሉ ይችላል።

ይህ ሲሆን ደግሞ water intoxication (የውሃ ምርዛት) በመባል ይታወቃል።

ስፖርት ለማይሰራና ብዙ ለማያልበው ሰው ከ1.6 እስከ 2 ሊትር ውሃ እንዲየውም ብዙ ሆኖ ሊሰማ ይችላል። እናም አውቆ ካልሆነ በስተቀር ከዛ በጣም የሚበልጥ መጠን ውሃ የመጠጣቱ ዕድል ጭራሽ አይኖርም። ግን ከባድ ስፖርት የሚሰራና በጣም የሚያልበው ሰው በላቡ የወጣውን ውሃ ለመተካት ውሃ ይጠማዋል ይጠጣል።

እዚህ ላይ ችግሩ ምንድን ነው ውሃው ሲጠጣ ውሃው ቢተካም እንደ sodium(ሶዲዩም) አይነት ለሰውነት አስፈላጊ ንጥረ ነገሮች electrolytes ከውሃ ጋር አብረው ውጥተው ግን ከውሃ ጋር አብረው አልተተኩምና imbalace(አለመመጣጠን) ይፈጠራል።

ይህ ሰውነታችን ውስጥ የሚፈጠረው  electrolytes ከውሃ ጋር አለመጣጠን እስከሞት ድረስ ሊዳርግ የሚችል አለመመጣጠን ነው።

ስለዚህ ከባድ ስፖርት የሚሰሩ ሰዎች sport drinks (የስፖርት መጠጦች) ተብለው ተመጣጥነው የተዘጋጁ መጠጦች ቢጠጡ እና ደግሞ ብዙ ውሃ ከሰውነቱ በላብም ሆነ በሌላ ለወጣው ሰው ደግም(ለስፖርተኞችም ሊሆን ይችላል) ORS ወይም ለምለም በጥብጦ መጠጣት በጣም የተሻለ ነው።

3) ብዙ መሮጥ:-

በድጋሚ ይሄ ነጥብም ሰውን ሊያስገርም ይችላል። ምክንያቱም መሮጥ ከእንቅስቃሴ ወይም ስፖርት ጋር የተያያዘ ነው ስፖርትም ደግሞ ለጤነት ጥሩ ነው።

አዎ ትክክል ነው። ስፖርት ለጤንነት ጥሩ ነው።

ግን ብዙ መሮጥ ችግር ሊሆን የሚችልባቸው ጊዜያቶችና ሁኔታዎች አሉ።

እነሱም

ሀ) ረጅም ርቀት መሮጥ፡-

ረጅም ርቀት መሮጥ አንድ ሰው በ arthritis በሽታ የመያዙን እድል ይጨምራል። እሱም ብቻ ሳይሆን የጉልበት cartilage ን ያሳሳል ተብሎ ይገመታል።

ለ) በአፈርና በሳር ላይ ከመሮጥ ፋንታ በሲሚንቶና አስፋልት ላይ አዘውትሮ መሮጥ:-

ይህ እራሱ ቁርጭምጭሚት ላይ ችግር ያመጣል ተብሎ ይገመታል

ሐ) በጣም ወፍራም ሆኖ ብዙ ለመሮጥ መሞከር:-

አንድ ሰው በጣም ወፍራም ሆኖ አዘውትሮ ቢሮጥ ቁርጭምጭሚቱና ጉልበቱ ላይ ችግር ሊደርስ ይችላል። ስለዚህ ቀንሶ average ክብደት ላይ እስኪደርስ ድረስ ከመሮጥ ይልቅ መራመድ ይመከራል።

4) ኮምፕዩተር በብዛት መጠቀም:-

በመጀመሪያ አንዳንድ Environmental ቡድኖች የኮምፒዩተር መስኮት መርዛማ ባህሪይ ያለው አቧራ እንደሚይዝ ጠቁመዋል። ይህም ደግሞ neurological ችግር ሊፈጥር ይችላል ተብሎ ይገመታል።

ሁለተኛ ኮምፒዩተር በብዛት የሚጠቀም ሰው ብዙ መቀመጡ አይቀርም። ብዙ መቀመጥ ደግሞ ለጤነት መጥፎ ነው።

ሌላው ነገር ደግሞ ከኮምፒዩተር የሚመነጨው ደማቅ ብርሃን አይኖቻችንን ሊያደክመው ይችላል።

ለነዚህ መፍትሄ አንዳንድ ዶክተሮች የሚመክሩት ኮምፒዩተር ስንጠቀም በመሃል እረፍት ወስደን መንጠራራትና ትንሽ እንቅስቃሴ ማድረግ አይናችንን ደግሞ ከ 30 ደቂቃ እስከ 1 ሰዓት በመሃል ማሳረፍ ነው።

5) ብዙ መቀመጥ:-

ይሄ ነጥብ ብዙም ባያስገርምም ለእውቀቱ ያህል በቀን 3 ሰዓት ብቻ እራሱ መቀመጥ ከህይወታችን ከ 2 እስከ 3 አመት ድረስ ይቀንሳል ተብሎ በባለሙያዎች ይገመታል።

ሌላም ደግሞ በሳምንት 23 ሰዓት ብቻ እራሱ መቀመጥ የሰውን ልጅ ለሆነ አይነት የልብ በሽታ እጅጉኑ ተጋላጭ እንደሚያደርግ ተመራማሪዎች ይገልፃሉ።

6) ከመጠን በላይ ሻወር መውሰድ ወይም መታጠብ፡-

እሺ። እንደገና አስገራሚ ነጥብ ላይ መጣን። ብዙውን ጊዜ መፀዳዳት እና ንፅህናን መጠበቅ ለጤና ጥሩ ነው ይባላል። አዎ ነውም። ግን ሁሉም ነገር ሲበዛ ጥሩ አይደለም እንደሚባለው ሁሉ ይሄም ሲበዛ መጥፎ ሊሆን ይችላል።

ምክንያቶቹን በቀላሉ ስንመለከት

አንድኛ ከመጠን በላይ መታጠብ የሰውነታችንን natural oil ወይም ተፈጥሮእዊ ቅባት በማድረቅ ቆዳችን ደረቅ እንዲሆን ያደርጋል።

ሁለትኛ በተፈጥሮ ጎጂ የሆኑ ባክቴሪያዎች እንዳሉ ሁሉ በተፈጥሮ ጠቃሚ የሆኑ ባክቴሪያዎች እጆቻችንና ሰውነታችን ላይ ሁሌም ይገኛሉ። እናም ከመጠን በላይ በሳሙና መታጠብ እነዚህ ጠቃሚ ባክቴሪያዎችም እንዲጠፉ ያደርጋል።

ስለዚህ ሁሉም ነገር ልክ እንዳለው መገንዘብ ይገባል።

Posted via Blogaway




አንዳንድ ጊዜ በተለይም በሃገራችን ላይ የሚያቃጥሉ ምግቦች መብላት የተለመደ ነው።

የሚያቃጥል ምግብ መብላት ወይም ቃሪያውን ወይ ሚጥሚጣውን ከምግብ ጎን አድርጎ እንዲሁ መብላት አፕታይት ሊከፍትና ምግብ ሊያባላ ይችላል።

አንዳንድ ጊዜ ግን ይሄ ቃጠሎ ሊበዛብን ይችላል። በዛን ጊዜ ቃጠሎውን ለማብረድ ያገኘነውን ነገር በተለይ ፈሳሽ ነገር እንዲያበርድልን ለመሞከር መውሰዳችን አይቀርም።

ከዚህ በታች የምላስ ቃጠሎን የሚያበርዱና የሚያብሱ ነገሮችን እናያለን


                ቃጠሎን የሚያበርዱ

1) እርጎ

2) ወተት

3) ጠንካራ አልኮሆል ይለባቸው መጠጦች(ዊስኪ፣ አረቄ ...)

4) ስኳር

5) ዳቦ

6) ጥሬ ቲማቲም

7) ሎሚና ብርቱካን

8) የወይራ ዘይት

                 ቃጠሎን የሚያባብሱ

1) ውሃ

2) ለስላሳ መጠጦች

3) ቢራ

4) ቡና



Posted via Blogaway


ጉንፋን በነገራችን ላይ እስከአሁን ድረስ መድሃኒት ያልተገኘለት በሽታ ነው።  immune system ወይም የሰውነታችን የመከላከያ አቅም ትክክል እና በቂ ከሆነ በራሱ ጊዜ የሚሄድ በሽታ ነው።

በአብዛኛው ጊዜ ለጤነኛ ሰው ጉንፋን ከ3 እስከ 7 ባሉት ቀናት ውስጥ እራሱ ይድናል። አንዳንድ ጊዜ ግን ከዛም በላይ ሊቆይ  ይችላል።

የሚከትሉት ነጥቦች ጉንፋን ከተቻለ ቶሎ እንዲለቅዎትና ብዙ ሳይጎዳዎት እንዲለቅ ይጠቅማሉ ተብሎ ይታሰባል።

1) የማርና የሎሚ ሻይ መጠጣት:-

1 1/2 የሾርባ ማንኪያ የሎሚ ጭማቂ ከ 2 የሻይ ማንኪያ ማር ጋር በአንድ ኩባያ የተቀዳ የፈላ ውሃ ውስጥ ጨምረው ይጠጡ

2) ፈሳሽ በደንብ መጠጣት:-

ማንኛውንም አይነት ፈሳሽ በደንብ መጠጣት። በተለይ ትኩስ ነገሮችን በደንብ በተደጋጋሚ መጠጣት

3) አዘውትረው እረፍት ከሚወስዱት በላይ እረፍት መውሰድ

4) ጨውና ለብ ያለ ውሃ በጥብጠው ጉሮሮዎትን በደንብ ይግሞጥሞጡበት

5) የሀኪም ትዕዛዝ ከማያስፈልጋቸው(over the counter) መድሃኒቶች አንዱን መውሰድ

6) ሲጋራ አለማጨስ ወይም ሲጋራ የሚጨስበት አካባቢ አለመሆን

7) የዶሮ ሾርባ መጠጣት:-

የዶሮ ሾርባ አንዳንድ የጉንፋንን ስሜት እንዲሰማን የሚያደርጉትን የነጭ ደም ሴል አይነቶች እንቅስቃሴያቸው እንዲቀንስ እምደሚያደርግ አንዳንድ የሳይንስ ጥናቶች ያሳያሉ። ስለዚህ የህመም ስሜቱ እንዲቀንስ ይረዳል።

የዶሮ ሾርባ ሲጠጡ የሚያቃጥል ነገር ጣል ቢያደርጉበት ይመረጣል።

8) በ zink የበለፀጉ ምግቦችን ወይም የ zink እንክብል መውሰድ:-

ጥናቶች እንደሚያመለክቱት ከሆነ የ zink እንክብል መውሰድ ጉንፋኑ እንክብሉ ሳይወሰድ ከሚድንበት አንድ ቀን አስቀድሞ እንደሚያድንና በታመሙበትም ጊዜ የህመም ስሜቱ አነስተኛ እንዲሆን እንደሚረዳ ነው።

9) ነጭ ሽንኩርት መብላት:-

ነጭ ሽንኩርት anti oxidents ስልስሉት የሰውነት የመከላከል ዓቅማችንን ከፍ ያደርጋል።

10) ጥሬ ማር መብላት:-

ጥሬ ማር ልክ እንደ ነጭ ሽንኩርት የሰውነት የመከላከያ አቅማችንን ይጨምራል። ከዛም በላይ ደግሞ ጉሮሮእችንን ከሚበላን ስሜት ነፃ ለማድረግ ይረዳል።

11) ቫይታሚን ሲ በደንብ ያላቸውን ምግቦች መብላት ወይም የቫይታሚን ሲ እንክብል መውሰድ:-

ቫይታሚን ሲ ያላቸው ምግቦች እንደ ብርቱካን፣ ሎሚ፣ ስትሮቤሪ የመሳሰሉት ናቸው።

አብዛኞቹ ፍራፍሬዎች ቫይታሚን ሲ አላቸው ግን ሎሚ፣ ብርቱካን እና ስትሮቤሪ የመሳሰሉት በተፈጥሮአቸው ኮምጠጥ የሚሉ ፍራፍሬዎች ከሌሎች በላቀ ሁኔታ ቫይታሚን ሲ ይገኝባቸዋል




1) የስልኩን ስክሪን ታይም አውት(Screen Timeout) አስተካክሉ:-

ስክሪን ታይም አውት ማለት ስልኩን ተጠቅመው አብቅተው የስልኩ ስክሪን(መረጃዎችን የሚያሳየው መስኮት) እንደበራ የሚቆይበት የሚቆይበት የጊዜ መጠን ማለት ነው።
ስክሪኑ በርቶ በቆየበት ሰዕስት ቁጥር ባትሪዎትን እየጨረሰብዎት ነው ማለት ነው። ስለዚህ ይህንን ስክሪን ታይም አውት ለእጭር ጊዜ እንዲሆን ማስተካኪል ባትሪዎት እንዲቆጠብ ይረዳል።

2) የስልክዎት ባትሪ ከብረት ጋራ እንዳይገናኝ መጠንቀቅ:-

የስልክዎት ባትሪ ከብረት ጋራ በተገናኘ ቁጥር አገልግሎት ሰጪነቱ የመቀነስ እድል የበለጠ ይሆናል

3) ባትሪዎትን ከቀጥተኛ ፀሃይ ወይም ከፍተኛ ሙቀት ያርቁ:-

ባትሪዎት በተለይም 100% ቻርጅ ተቀብሎ ለቀጥተኛ ፀሃይ ወይም ለከፍተኛ ሙቀት ከተጋለጠ የመበላሸቱና አገልግሎቱን የመቀነሱ እድል እጅግ ከፍተኛ ይሆናል

4) Drain and refill(አሟጦ እንደገና መሙላት)

በወር አንዴ ቻርጅዎት ባዶ እስኪሆን ስልክዎትን ተጠቀሙና እንደገና full(ሙሉ) እስኪሆን ቻርጅ ያድርጉት

5) እየተጠቀሙት ካልሆነ የኢንተርኔት ኮኔክሽን አጥፉት:-

ኢንተርኔት እየተጠቀሙ ካልሆነ ኢንተርኔት ኮኔክሽንና ዋይፋይን off ያድርጉት



Posted via Blogaway


የዕለት ተግባሮቻችንን ስንፈፅም ወይም ልንፈፅም ስናስብ ድካም ትልቅ መሰናክል ሊሆንብን ይችላል።

ግን ችግር የለውም። አይጨነቁ። ለአብዛኞቹ የድካም መንስኤዎች መፍትሄ አላቸው።

ስለዚህ አሁን የድካም መንስኤዎችንና መፍትሄዎቻቸውን እንመልከት

1) በሽታ:-

ለድካሞት አንደኛው መንስኤ በሽታ ሊሆን ይችላል። የሆነ በሽታ ይዞዎት ወይም ሊይዞት እየሞከረ ሊሆን ይችላል።
ድካሞት ብርቱ ከሆነ ሀኪም ቤት ሄደው ይመርመሩ።

2) እንቅልፍ:-

ለድካሞት ሌላው መንስኤ ሌሊት በቂ እንቅልፍ ሳያገኙ ቀርተውም ሊሆን ይችላል። የእንቅልፍ እጦት ድካም ብቻ ሳይሆን የምንሰራቸውን ሥራዎች ሁሉ በስነስርዓት እንዳንሰራ ይከለክላል።
ሌሊት እንቅልፍዎትን በስነስርአት ካልተኙ አደጋ ካላቸው ስራዎች በተለይ እንደ መንዳትና ኮንስትራክሽን ይቆጠቡ።
ለእቅልፍ መፍትሄው ያው መተኛት ነው።
እንቅልፍ ሁሌ የሚያስቸግርዎት ከሆነ ሀኪም ያማክሩ።

3)dehidration(የሰውነት ውሃ መጠን ማነስ):-

የሰውነታችን የውሃ መጠን ሊሆን ከሚገባው 1.5% እንኳን ከጎደለ የድካም ስሜት፣ የስሜት መቀያየር፣ ጉልበት ማጣት  ይሰማናል። በዛው እየቀነሰ ከሄደ እስከሞት ድረስ ሊዳርገን ይችላል።
በቀን ውስጥ በሞላ ጎደል ከ 1.6 እስከ 2 ሊትር ውሃ ለሰውነታችን ያስፈልጋል።
ስራችን ከባድ ከሆነ ወይም ከባድ ሥራ ከሰራን፣ ተቅማጥ ከያዘን፣ ብዙ ጨው ያለበት መግብ ከበላን እና ውሃ በየትኛውም መንገድ በላብም ሆነ በሌላ በፍጥነት የሚወጣን ከሆነ ከዛ በላይ መጠጣት ይኖርብናል።
ስለዚህ በዚህ መሰረት ውሃችንን በየቀኑ መጠጣት ያስፈልገናል።

4) Alcohol(የሚያሰክሩ መጠጦች):-

እሄ ቀልድ ሊመስልዎት ይችላል ግን የሚያሰክሩ መጠጦች የእንቅልፍዎትን ጥራት እንደሚቀንስብዎት የተረጋገጠ ነገር ነው።

5) አንዳንድ መድሃኒቶች:-

አንዳንድ መድሃኒቶች ድካም ሊለቁብን ይችላሉ። የድካም ስሜትዎት በሚወስዱት መድሃኒት ነው ብለው የሚጠረጥሩ ከሆነ እና ደግሞ ድካሙ ከባድ ከሆነብዎት ሃኪምዎትን ያማክሩ

6) የሰውነት የብረት መጠን መቀነስ:-

ብረት ደማችን አኦክስጅን ወደ መላ ሰውነታችን እንዲደርስ የሚረዳ ንጥረ ነገር ነው። ሰውነታችን በቂ ብረት ካጣ ደግሞ አኦክስጅን ለሰውነታችን በብቁ ሁኔታ አይደርስም ማለት ነው። ይህ ደግሞ አእምሮእችንን ያካትታል። በዚህ ምክንያት ድካም እና የማዞር ስሜት ሊሰማን ይችላል።
እንደ እንጀራ፣ ቅጠላቅጠሎች እና እህሎች ብረት የያዙ ምግቦች ናቸው።
እነሱን እየበሉም የብረት መጠን ማነስ በራስዎት ላይ ከጠረጠሩ ሃኪምዎትን ያማክሩ።

7) ቡና:-

ቡና ልክ ሲጠጣ ያነቃቃል። ግን ከሰውነታችን ባለቀ ጊዜ ድካም ሊያሰማ ይችላል።
በተለይ ሱስ ካለብን በተለመደው ሰዓት ከባድ ድካም ሊሰማን ይችላል።

8) በቂ እንቅስቃሴ አለማድረግ:-

በቂ እንቅስቃሴ አለማድረግ ለድካም አንዱ መንስኤ  ነው። ጥናቶች እንደሚያመለክቱት ከሆነ በሳምንት ሶስቴ ለሃያ ደቂቃ ስፖርት የሚሰሩ ሰዎች ምንም ስፖርት ከማይሰሩ ሰዎች የላቀ የሃይል መጠን ያላቸውና ድካማቸውም ስፖርት ከማይሰሩት ሰዎች ያነሰ እንደሆነ ታይቷል።

9) ከመጠን በላይ መሥራት:-

ሁሉም ነገር ሲበዛ ወይም ሲይስንስ ጥሩ አይደለም። ሥራ ጥሩ ቢሆንም ከመጠን በላይ መሥራት በተለይ የጉልበት ሥራ ከመጠን በላይ መሥራት ሰውነታችን "cortisol" የሚባል የጭንቀት ሆርሞንን በጣም እንደሚለቅና በዛም ምክንያት እንቅልፍ መተኛት  እንኳን በጣም እንደሚከብድ ጥናቶች ያመለክታሉ።
ስለዚህ ሁሉንም ነገር ስናደርግ በመጠኑ እናድርግ።