ነጭ ሽንኩርት እና ቀይ ሽንኩርት ምግብን በማጣፈጥና በተለይ ደግሞ ነጭ ሽንኩርት ምግብ ማጣፈጥ ብቻ ሳይሆን በተለያየ መንገድ ለጤንነታችንም በጣም ጠቃሚ እምደሆነ ይታወቃል።

ቢሆንም ግን ሁለቱም ነጭ እና ቀይ ሽንኩርት በተለይ በጥሬነታቸው ከተበሉ አንዳንድ እንደ ሆድን ማቃጠል አይነት ደስ የማይሉ ውጤቶች እንዳሏቸው ይታወቃሉ። ከነሱም አንደኛው መጥፎ የአፍ ጠረን ነው።

ነጭ ወይም ቀይ ሽንኩርት(በተለይ ነጭ ሽንኩርት) ሲሸረካከቱና ሲጨፈለቁ ከሌሎችም ነገሮች ጋራ allyl methyl sulfide የሚባል ንጥረ ነገር ከውስጣቸው ይለቃሉ። ይህ ንጥረ ነገር ደግሞ ሆዳችን ውስጥ ገብቶ ወደደማችን እንደሌሎች ነጥረ ነገሮች ተመጦ ይገባል። ከገባም በኋላ ላባችንና የአፍ ጠረናችን ለ አንድ ሙሉ ቀን ለሚያክል ጊዜ መጥፎ ሽታ እንዲይዝ ያደርጋል።

ከዚህ በታች የአፍ ጠረናችን በዚህ ንጥረ ነገር ምክንያት የያዘውን መጥፎ ጠረን እጅግ አድርገን እንዴት እንደምንቀንስ እንመለከታለን።

1) ሶስት የተቆላ የቡና ፍሬ አኝኮ አፍን መግሞጥሞጥ

2) እንደ ፖም ኮክ እና ወይን አይነት ፍራፍሬ መብላት:-

ፍራፍሬዎች ሲገመጡ ወይም ሲቆረጡ oxidize(ቀለማቸውን እንዲቀይሩ) እንዲሆኑ የሚያደርጋቸው ባህሪያቸው ከነጭ ሽንኩርት እና ሽንኩርት የሚመጣ መጥፎ የአፍ ጠረንንም የሚዋጋ ባህሪይ ነው።

3) እንደ ሰላጣ፣ ቆስጣ፣ ጎመን፣ ድንች አይነት አታክልቶችን መብላት:-

አንዳንድ አትክልቶች ከ ነጭ ሽንኩርት እና ቀይ ሽንኩርት የሚመጣን የአፍ ጠረን ለመቀነስ ጥሩ አስተዋጽኦ ያደርጋሉ

4) ወተት መጥጣት፡-

ወተት በተለይ ከ ነጭ ሽንኩርት የሚመጣ መጥፎ የአፍ ጠረንን እጅግ እንደሚቀንስ ይታወቃል

4) green tea መጠጣት

5) ዳቦ መብላት:-

የካርቦሃይድሬት እጥረት ከመጥፎ የአፍ ጠረን ጋር ተያያዥነት አለው። ዳቦ ደግሞ በ ካርቦሃይድሬት የበለጸገ ምግብ ነው

6) እንደ ሎሚ ጭማቂ እና ግሬፕ ፍሩት ጭማቂ አይነት አሲድ የበዛባቸው መጠጦችን መጠጣት

7) ማስቲካ ማኘክ

8) ጥርስ በጥርስ ሳሙና እና በጥርስ ብሩሽ መቦረሽ

9) በ mouth wash መግሞጥሞጥ

ሌላ ማወቅ ያለብን ነገር

- ነጭ እና ቀይ ሽንኩርት መብላት በአፍ ብቻ ሳይሆን መጥፎ ሽታ የሚያመጣው ንጥረነገር ደም ውስጥም ስለሚገባ ላባችንንም መጥፎ ጠረን እንዲያመጣ ሊያደርግ ይችላል። ስለዚህ እንደ ሽቶ አይነት ነገር ትንሽ መጠቀም ከላባችን ልብሳችን ላይ ለተጣበቀው ሽታ መቀነስ አስተዋጽኦ ያደርጋል።

- ከ ነጭ እና ቀይ ሽንኩርት የሚመጣ ሽታ በጊዜ እራሱ ይጠፋል።


አይ ኤስ(ISIS) የተባለው ቡድን እንደምናውቀው በዘመናችን ካሉ አሸባሪ ቡድኖች ከሁሉም አሸባሪ ቡድኖች በላይ በአስገራሚ ሁኔታ ብዙ ሰው፣ ብዙ ገንዘብ እና ብዙ መሬት ያለው ቡድን ነው።

እኚህ የ አይ ኤስ አሸባሪ ቡድን አባሎች እንደምናየው እና እንደምንሰማው እናም የአይን ምስክሮች እንደሚገልጹት ከሆነ ጥሩ እና መጥፎን የሚዳኝ እግዚአብሄር እንደሌለ ወይም እነሱ የሚከተሉት እግዚአብሄር አረመኔ እና ህሊና ቢስ ነው የሚል መልእክት ለማስተላለፍ እንደሚፈልጉ በሚመስል መንገድ የእስልምና ሃይማኖት ባይፈቅደው እራሱ በእስልምና ስም ወንድ ወይ ሴት፣ ልጅ ወይ አዋቂ ወይም ንጹህ ወይ ወንጀለኛ ሳይሉ ሰው እንደሚገድሉ፣ እንደሚያርዱ፣ ሴቶችን በመጥለፍ ከ 100 ዶላር ጀምረው እንደሚሸጡ፣ በእጃቸው የገቡ ሴቶችንም ደግሞ እንደፈለጉ እየተፈራረቁባቸው አስገድደው እንደሚደፍሩ እራሳቸው የሚለቁት የቪዲዮ ቀረጻ እና በነሱ ስር የሚኖሩ እና ከእነሱ እጅ ያመለጡ ሰዎች ይመሰክራሉ።

እኚህ የ አይ ኤስ ቡድን አባላት የሚያደርጉትን ነገር ሁሉ የሚያደርጉት በእስልምና ስም ነው። ይህም ሆኖ የሚያደርጉት ነገር ሁሉ ሰብአዊ ርህራሄ ፈጽሞ የሌለው፣ አረመኔያዊ እና የክፋት ነጸብራቅ እንጂ ለናሙና ያህል እንኳን አንድ ጥሩ ነገር አድርገው ታይቶም ወይም ተሰምቶም አይታወቅም።

እነዚህ የአይ ኤስ ቡድን አባላት ያደረጉትን ነገር አድርገው ሲሞቱ ገነት ገብተው 72 ድናግል ይጠብቁናል ብለው ያምናሉ። እንዲየውም የሚያደርጉት ነገር ሁሉ ለሱ ብለው እንደሆነ ይታወቃል።

በሚያደርጉት ተግባር አንድ ሰው እነኚህማ የሚፈሩት ነግር የለም ብሎ ሊያስብ ይችላል። ግን ይሄ ከእውነት የራቀ ነው። በእርግጥ ገነት ገብተን 72 ድንግሎች ይጠብቁናል ብለው ስለሚያምኑ ሞትን ላይፈሩ ይችላሉ። ተጨንቀው ከህንጻ ላይ ተፈጥፍጠው የሚሞቱ ሰዎችም እኮ ሞትን አልፈሩም። ሞት ደግሞ ፈራንም አልፈራንም ማንም አይቀርለትም እና የሚፈራ ነገርም መሆን የለበትም። ግን ሰው እንደመሆናቸው መጠን ከሞት ውጪ ማንም ሰው የሚያስፈራው ነገር ያስፈራቸዋል። እንዲየውም በቅርብ አንድ የ አይ ኤስ ቡድን አባል በ ኩርዶች ተይዞ እንደ ህጻን ልጅ ሲያለቅስ በ ቪዲዮ ተለቆ የአለም መሳሳቂያ ሆኗል።

ግን ከስቃይ እና ከውርደት በላይ ደግሞ የ አይ ኤስ ቡድኖች የሚፈሩት ነገር አለ። ይህም ደግሞ በሴት እጅ መገደልን ነው። እነሱ እንደሚያምኑት ከሆነ እራሳቸውን ቢያጠፉም ሆነ በጦርነት ላይ በወንድ ከተገደሉ ገነት ገብተው ከ 72 ድንግሎች ጋር አለማቸውን እንደሚቀጩ ነው። ግን እንደድንገት በሴት ከተገደሉ እኚህ ሁሉ ድንግሎች እና ገነት ቀርቶ ቀጥታ ገሃነም እንደሚሄዱ ነው።

Kurdish Peshmerga Forces የኩርዶች ፐሽመርጋ ሃይሎች አይ ኤስ ዋና ጦርነት የሚያካሄድበት አካባቢ ኢራቅ እና ሶርያ አካባቢ የሚገኙ የ ኩርዶች ወታደራዊ ሃይል ናቸው። እነሱ ወታደራዊ ሃይል ውስጥ ደግሞ ብዙ ሴቶች ይገኛሉ። እነዚህም ሴቶች በየቀኑ ከ አይ ኤስ ጋር ፍልሚያ መግጠም ከጀመሩ ሰንበትበት ብሏል። የሚያስቀው ነገር ግን የ አይ ኤስ ወታደሮች የ ኩርድ ሴት ወታደሮችን ሲያዩ ከሩቅ ሲሸሹ ሲታይ ነው። እንዲየውም እኚህ የኩርድ ሴት ወታደሮች ስለዚህ ጉዳይ ሲጠየቁ ሁሌም መልሳቸውን የሚመልሱት ከፈገግታና ከሳቅ ጋራ ነው። ግን ቢሸሹም የሚለቃቸው የለም። እነዚህ የኩርድ ሴት ወታደሮች እጅግ ብዙ የሆኑ የ አይ ኤስ ወታደሮችን ቀጥታ ወደ ገሃነም ልከዋል።


1) ቡና በመጀመሪያ ጊዜ የተገኘው(የታወቀው) በኢትዮጵያ እረኞች በ 800 ዓ/ም አካባቢ ሲሆን እረኞቹም ያስተዋሉት ፍየሎቻቸው ቡናውን በልተው የመቅነዝነዝና የመደነስ ስሜት ሲታይባቸው ነው።

2) ቡና በምድር ላይ በብዛት ከሚሸጡ ነገሮች ሁለተኛውን ደረጃ ይይዛል። Global Exchange በዘገበው መሰረት ቡና ከ 50 በሚበልጡ ሀገራት ከ 25 ሚሊዮን በሚበልጡ ገበሬዎች ይመረታል።

3) የቡና ዘር አይነቶች ሁለት ናቸው። እነሱም Arabica እና Robusta ይባላሉ። 70% የሚያክሉ የቡና ዘሮች Arabica ናቸው። Robusta የቡና ዘር እንደ Arabica ብዙም ተወዳጅነት የሌለው ሲሆን ከ Arabica ትንሽ መረር የሚልና የ caffeine መጠኑም ከ Arabica እጥፍ ነው።

4) በቡና ምርት በአለም አንደኛ ብራዚል ስትሆን የአለማችንን የቡና ምርት 40% ትሸፍናለች። ሁለተኛና ሶስተኛ ደግሞ ኮሎምቢያና ቬትናም ናቸው።

ኢትዮጵያ በቡና ምርት በአለም ሰባተኛ ስትሆን በአፍሪካም ደግሞ አንደኛ ነች።

5) በአለም ውዱ ቡና Kopi luwak ሲባል ግማሹ ኪሎ ከ 100 - 600 ዶላር ያወጣል።
አመራረቱም Luwak የሚባል እንስሳ ቡናውን እስከነቅርፊቱ ከበላው በኋላ እንስሳውም በተፈጥሮው የቡና ፍሬውን ሆዱ መፍጨት ስለማይችል ፍሬው በአሩ እንዳለ ይወጣል። ከዛ ፍሬው ከአሩ ተለቅሞ ታጥቦ ለጥቅም ይውላል።

6) በአለማችን ታሪክ ቡናን ህገወጥ ለማድረግ አምስት ጊዜ ተሞክሮ ነበር

1ኛ) በ 1511 AD በ Mecca 

2ኛ) በ 16ኛው ክፍለ ዘመን የጣልያን የካቶሊክ ቄሶች እና ዲያቆኖች ቡናን ስይጣናዊ ነው በማለት አስከልክለው ነበር። ቢሆንም ግን Pope Clement VII የሚባሉ የዚያን ጊዜ የካቶሊክ ዋና ጳጳስ ቡናን በጣም ይወዱ ስለነበር ቡናን አስጠምቀው ተመልሶ ህጋዊ እንዲሆን አድርገዋል።

3ኛ) በ 1623 AD Murad IV የሚባል የ Ottoman መሪ ለቡና መጠጥ የመጀመሪያውን ቅጣት ለዓለም አስተዋውቋል። ቡና ለጠጣ ሰው ቅጣቱም ግርፊያና ባህር ውስጥ መወርወር ነበር።

4ኛ) በ 1746 AD የ ስዊድን መንግስት እንደ ሲኒ ያሉ የቡና መጠጫ እቃዎች እራሱ ይዞ መገኘትን ህገወጥ አድርጎት ነበር።

5ኛ) 1777 AD የ የፕሩሺያው Frederick the Great ቡና ከቢራ መጠጥ ጋር እንዳይፎካከር ብሎ ህገወጥ አድርጎት ነበር።

7) ቡና ከልክ በላይ ከተጠጣ ሊገድል ይችላል። ግን ያንን መጠን ለመድረስ አንድ ሰው 100 ኩባያ መጠጣት አለበት።

8) ቡና Alzheimer's በሽታን፣  Parkinson's በሽታን፣ የተለያዩ የካንሰር በሽታዎችን እና የስኳር በሽታን የመከላከል አቅም አለው።

9) ቡና ላይ ክሬም ሲጨመር ቡናው ለበለጠ ጊዜ ትኩስ ሆኖ ይቆያል።

10) ቡና ላይ ወተት ሲጨመር የማነቃቃቱን ሃይል ይቀንሳል።

11) እስከአሁን ድረስ ከተፈሉት ትልልቅ ኩባያ ቡናዎች ከሁሉም ትልቁ በ ደቡብ ኮሪያ july 2014 ላይ የተፈላ ሲሆን እሱም 14 ሺህ ሊትር ነው።

12) ቡናን ማሽተቱ ብቻ ከእንቅልፍ ሊያነቃ ይችላል። ተመራማሪዎች እንደሚገልጹት ከሆነ ቡናን ማሽተቱ እራሱ አእምሮ ውስጥ ያሉትን የአንዳንድ genes እንቅስቃሴ በመቀየር የእንቅልፍ ስሜትን ሊቀንስ ይችላል። ያንን ያሸተቱትን ቡና ሲጠጡ ደግሞ ሳያሸቱ ከሚጠጡት ቡናው 10 ደቂቃ ቀድሞ ደም ውስጥ እንዲደርስ ያደርጋል።

13) በጣም ጠቁረው የተቆሉ የቡና ፍሬዎች ቀላ ካሉት በ caffeine መጠናቸው አነስ ይላሉ።

14) አሜሪካ ውስጥ ካሉት ከ 18 አመት በላይ የሆኑ ሰዎች 80% በየቀኑ ቡና ይጠጣሉ።


ይሄንን ፔጅ መደገፍና ማበረታታት ይቻላል።

Saving account number:- 1000072142474

Name:- Alazar Desta

Swift number:- CBETETAA

ኢትዮጵያ ንግድ ባንክ የሚጠቀሙ ከሆነ swift number አያስፈልግም




እስከቅርብ ጊዜ ድረስ ሳይኮሎጂ እና ፍልስፍና እንደ አንድ ጥናት ነበር የሚታዩት። እንዲየውም የሳይኮሎጂ ጥናት ከፍልስፍና ተለይቶና እራሱን ችሎ የወጣው በፈረንጆቹ ከ 1870 ዎቹ በኋላ ነው። ከዛ በኋላ በሳይኮሎጂ ጥናት ብዙ ግኝቶችና መሻሻሎች ቢኖሩም አሁንም ገና ያልተነካ ፊልድ እንደሆነ ባለሙያዎቹ ይናገራሉ።

ለማንኛውም በሳይኮሎጂ ጥናት የተኙትን እነዚህን የሚያስገርሙ ግኝቶችን እንመልከት።

1) እቅድዎትንና አላማዎትን ለሌሎች ከነገሩ ያንን እቅድ የማሳካትዎ እድል ይቀንሳል:-

በፈረንጆች አቆጣጠር ከ 1933 ዓ/ም ጀምሮ በተደረገው ጥናት መሰረት አንድ ሰው እቅዱን ለሌላ ሰው ከነገረ እቅዱን ስለነገረ የሚሰማው እርካታ ባይነግር ኖሮ የሚኖረውን ግፊት እና እልህ ይቀንስበታል ብሎ ጥናቱ ያሳያል። ስለዚህም እቅዱን የማሳካቱ እድልም የበለጠ ይቀንሳል።

2) ብዙ ሰዎች የሆነ ዘፈንን በጣም የሚወዱት ዘፈኑ የሆነ ያሳለፉትን ስሜታዊ ጊዜ ስለሚያስታውሳቸው ነው:-

ዘፈን ስሜት ላይ ተጽእኖ እንደሚያደርግ የታወቀ ነገር ነው። ግን አሁን ጥናቶች እንደሚያመለክቱት ከሆነ ተቃራኒውም እውነት ነው። ያ ማለት ስሜት ዘፈንን እንድንወደው ወይም እንዳንወደው ተጽእኖ ያደርጋል።

3) ዘፈን ስለ ማንኛውም ነገር ያለን አመለካከታችን ላይ ተጽእኖ ያደርጋል:-

በ Groningen University በተካሄደው ጥናት መሰረት ዘፈን አመለካከታችን ላይ ትልቅ አስተዋጽኦ ያደርጋል። በተለይ አሳዛኝ ዘፈን እና ይደስታ ዘፈን ስንሰማ ስለአለም ያለን አመለካከታችን ላይ በዛው መሰረት ተጽእኖ ያደርጋል።

4) ጥናቶች እንደሚያሳዩት ከሆነ ገንዘብን ለሌሎች ማዋል በራስ ከማዋል የበለጠ ደስታን ይሰጣል:-

በ Harvard buisness school በተደረገው ጥናት መሰረት ሰዎች ለሌሎች ሰዎች ገንዘብ ሲሰጡ ከማይሰጡ ይልቅ የበለጠ ደስተኞች ናቸው።

5) በጥናቶች መሰረት ገንዘብን ንብረት ማካበት ላይ ከማዋል ይልቅ በ experience(በተግባር ነገሮችን ማየት) ላይ ማጥፋት የበለጠ ደስተኛ ያደርጋል:-

6) ብዙ የዛሬ ልጆች(በተለይ ምዕራባዊያን) በ ፈረንጆች አቆጣጠር በ 1950 ዎቹ ከነበሩት የአእምሮ በሽተኞች ተመሳሳይ መጠን ያለው ጭንቀት አለባቸው:-

ጥናቶች እንደሚያመለክቱት ከሆነ የዛሬ ሰው ከድሮው ሰው እጅግ በበለጠ ሁኔታ ጭንቀት አለበት። ለዚህ ምክንያት ከሆኑት አንዳንዶቹ ሱሰኛ መሆን፣ ከህብረተሰቡ ጋር ብዙ ተቀራራቢነት አለመኖር፣ ስራ መቀያየር፣ የኑሮ ቦታ መቀያየር አንዳንዶቹ ናቸው።

7) አንዳንድ እንደፀሎት እና ቤተ ክርስቲያን መከታተል አይነት ሃይማኖታዊ ልምዶች የአእምሮን ጭንቀት ይቀንሳሉ:-

“The American Psychiatric Publishing Textbook of Mood Disorders” ባጠናው ጥናት መሰረት ሃይማኖታዊ ልማድን የሚያዘወትሩ ሰዎች ከማያዘወትሩት ሰዎች በጭንቀትና በሌሎች የአእምሮ ችግሮች ለመሰቃየት ያላቸው እድል በጣም ያነሰ ነው።

8) ገንዘብ ደስታን ሊገዛ ቢችልም ከተወሰነ የገንዘብ መጠን ካለን በኋላ ግን መጨመሩ ደስታችን ላይ ብዙም ለውጥ አያመጣም

9) በደስተኞች ሰዎች እራሳችንን መክበብ ወይም ከደስተኞች ጋር ብዙ ጊዜ አብሮ መሆን እራሳእንንም ደስተኛ እንድንሆን ያደርገናል:-

በ Psychoneuroendocrinology journal ላይ የታየ አዲስ ጥናት መሰረት ደስታም ሆነ ጭንቀት ተላላፊነት ባህሪይ አለው። እና ከየትኛውም አይነት ሰዎች ጋር መሆን የኛ ስሜት ላይ በዛው መሰረት ተጽዕኖ ያደርጋል።

10) ከ 18 እስከ 33 አመት ዕድሜ ያላቸው ሰዎች ከየትኛውም ዕድሜ ክልል ካሉ ሰዎች የበለጠ ጭንቀት አለባቸው። ከ 33 አመት በኋላ የጭንቀት መጠን እየቀነሰ ይሄዳል።

11) እራስን በቂ ተኝቻለሁ ብሎ ማሳመን በቂ ባይተኛ እራሱ ካለማሳመኑ ይልቅ በዕለት ተግባራችን ላይ የተሻለ ንቃት እንዲኖረን ያደርጋል:-

በ Journal of Experimental Psychology በታተመው ጥናት መሰረት ጥናት የተደረገባቸው ሰዎች በቂ ሳይተኙም ከበቂ በላይ ተኝታችኋል ተብለው ሲነገሩ ካልተነገሩት ይልቅ እጅግ የተሻለ ንቃትና የንቃት ተግባር አሳይተዋል።

12) አእምሮአቸው ብሩህ የሆኑ ሰዎች ስለራቸው ዝቅ አድርገው ነው የሚያስቡት። ብሩህ ያልሆኑና ብዙም የማያውቁ ሰዎች ግን በተጋነነ መልኩ ስለራሳቸው ከፍ ያለ ስሜት አላቸው።

13) ከአሁን በፊት የተደረገ ክስተትን ስናስታውስ በሚያስገርም ሁኔታ ድርጊቱን ሳይሆን የምናስታውሰው አሁን ካስታወስነው በፊት ስለሱ ያስታወስንበትን ጊዜ ነው።

14) አፍ ከፈቱበት ቋንቋ ውጪ ሌላ ቋንቋ ከቻሉ ውሳኔዎችን በሌላኛው ቋንቋ መወሰን ውሳኔው የበለጠ ምክንያታዊ እንዲሆን አስተዋጽኦ ያደርጋል።



Posted via Blogaway


ከሺ በኋላ መቶ ሺ፣ ከ መቶ ሺ በኋላ ሚሊዮን፣ ከሚሊዮን በኋላ ቢሊዮን እንደሚባል አብዛኞቻችን እናውቃለን።

ከቢሊዮን በኋላ ግን ምን እንደሚባል ብዙ ሰው አያውቅም።

እስቲ ከ ቢሊዮን በኋላ ያሉት ቁጥሮች ምን እንደሚባሉ እንይ።

- Trillion (ትሪሊዮን):- 1,000,000,000,000

- Quadrillion (ኳድሪሊዮን) :- 1,000,000,000,000,000

- Quintillion (ኩዊንቲሊዮን):- 1,000,000,000,000,000,000

- Sextillion (ሴክስቲሊዮን) :- 1,000,000,000,000,000,000,000

- Septillion (ሴፕቲሊዮን) :- 1,000,000,000,000,000,000,000,000

- Octillion (ኦክቲሊዮን):- 1,000,000,000,000,000,000,000,000,000

- Nonillion (ኖኒሊዮን):- 1,000,000,000,000,000,000,000,000,
000,000

- Decillion (ዴሲሊዮን):- 1,000,000,000,000,000,000,000,000,000,000,000

- Undecillion (አንዴሲሊዮን):- 1,000,000,000,000,000,000,000,000,000,000,000,000

- Duodecillion(ዱዎዴሲሊዮን):- 1,000,000,000,000,000,000,000,000,000,000,000,000,000

- Tredecillion (ትሬዴሲሊዮን):- 1,000,000,000,000,000,000,000,000,000,000,000,000,000,000

- Quatttuor-decillion(ኳቶር ዴሲሊዮን):-
1,000,000,000,000,000,000,000,000,000,000,000,000,000,000,000

- Quindecillion (ኩዊንዴሲሊዮን):-
1,000,000,000,000,000,000,000,000,000,000,000,000,000,000,000,000

- Sexdecillion (ሴክስዴሲሊዮን):- 1,000,000,000,000,000,000,000,000,000,000,000,000,000,000,000,000,000

- Septen-decillion (ሴፕተን ዴሲሊዮን):- 1,000,000,000,000,000,000,000,000,000,000,000,000,000,000,000,000,000,000

- Octodecillion (ኦክቶዴሲሊዮን):- 1,000,000,000,000,000,000,000,000,000,000,000,000,000,000,000,000,000,000,000

- Novemdecillion (ኖቬምዴሲሊዮን):- 1,000,000,000,000,000,000,000,000,000,000,000,000,000,000,000,000,000,000,000,000

- Vigintillion (ቪጂንቴሊዮን):- 1,000,000,000,000,000,000,000,000,000,000,000,000,000,000,000,000,000,000,000,000,000

- Centillion (ሴንቲሊዮን):- 1,000,000,000,000,000,000,000,000,000,000,000,000,000,000,000,000,000,000,000,000,000,000,000,000,000,000,000,000,000,000,000,000,000,000,000,000,000,000,000,000,000,000,000,000,000,000,000,000,000,000,000,000,000,000,000,000,000,000,000,000,000,000,000,000,000,000,000,000,000,000,000,000,000,000,000,000,000,000,000,000,000,000,000,000,000,000,000,000,000,000,000,000,000,000,000,000,000,000,000,000,000




ምርምር እንደሚያሳየውና በጉዳዩ ጥልቅ እውቀት ያላቸው ባለሙያዎች እንደሚነግሩን ከሆነ ስኳርን ክብደት በመቀነስ እና የአኗኗር ዘይቤን በመቀየር ለመከላከልና ለመቆጣጠር ይቻላል።

የአኗኗር ዘይቤን መቀየር በቂ እንቅስቃሴ ማድረግና የሚበሉትን ምግብ መርጦ መብላት ዋና ዋናዎቹ ናቸው።

ምክንያቱም እንደምናውቀው ስኳር ከሰውነት ክብደትና ከምንበላው የምግብ አይነት ጋር በጣም ተያያዥነት አለው።

በተለይ ስኳር በሽታ ላለባቸው ሰዎች የሚበሉት ምግብ በጤና የመቆየታቸውንና በበሽታ መታወካቸውን ውሳኔ ይወስናል።

አንዳንድ ምግቦች ስኳር ላለባቸው ሰዎች ምርጥ እና እንዲየውም ከአንዳንድ የአኗኗር ዘይቤ ለውጥ ጋር ሰውነት እራሱ ደም ውስጥ ይለውን የስኳር መጠን እንዲቆጣጠር ይረዳል ተብሎ ይታሰባል።

እነሱም ምግቦች የሚከተሉት ናቸው።

1) ፖም:-

ፖም በጣም ብዙ የጤና ጥቅሞች አሉት ተብሎ ከተበየነለት ቆይቷል። ፖም በተፈጥሮው ዝቅተኛ ካሎሪ እና ከፍተኛ ፋይበር አለው። ፋይበር ደግሞ እንዳይርብ፣ መጥፎ ኮለስተሮልን ለመዋጋት እና ደም ውስጥ ያለው ስኳር ወደ ሁለቱ ጫፎች እንዳይወላውል ይረዳል።

በዛ ላይ ደግሞ ፖም ብዙ በሽታዎችን እንድንዋጋ የሚረዳንንና ለሰውነታችን በብዙ መልኩ የሚጠቅመንን anti oxident በበለጸገ መልኩ ይዟል።

2) አቮካዶ:-

አቮካዶ በ monounsaturated fat የበለጸገ ስለሆነ digestion ቀስ ብሎ እንዲካሄድና ከምግብ በኋላ ደም ውስጥ ያለው የስኳር መጠን ጣሪያ እንዳይመታ ይቆጣጠራል።

እንዲየውም እንደ አቮካዶ አይነት ጥሩ fats ያሏቸው ምግቦች የደም የስኳር መጠን ጭራሽ ተመልሶ በተፈጥሮ ጤነኛ እንዲሆን ትልቅ አስተዋጽኦ ያደርጋሉ ተብሎ ይታሰባል።

3) ገብስ:-

ለምሳሌ ያህል በነጭ ሩዝ ፋንታ ገብስ መብላት ደም ውስጥ ያለውን ስኳር 70% ይቀንሳል። እሱ ብቻ ሳይሆን ገብስ በ ፋይበር የበለጸገ ስለሆነ የደም ስኳር መጠን ለሰዓታት ወይም ለረጅም ጊዜ ዝቅ ብሎ እንዲቆይ ይረዳል። ስለዚህ ገብስ ስኳር ላለበት እጅግ ምርጥ ምግብ ነው ተብሎ ይታወቃል።

4) ባቄላ እና ዘሮቹ:-

ባቄላ፣ አተር እና ሽምብራ አይነት ጥራጥሬዎች አንደኛ በፋይበር የበለጸጉ ናቸው። ሁለተኛ ደግሞ በ ፕሮቲንም የበለጸጉ ስለሆኑ የደም ስኳር መጠንን ዝቅ አድርጎ ለመጠበቅና እንዳይርብ አስተዋጽኦ ያደርጋሉ።

5) እንቁላል(በመጠኑ):-

እንቁላል በፕሮቲን የበለጸገ ምግብ ከመሆኑም በላይ እንቁላል የፕሮቲኖች ወርቅ ተብሎ ተሰይሟል። በቀን አንድ ወይም ሁለት እንቁላል  መብላት ኮለስትሮልንም ከፍ አያደርግም። ስለዚህ እንቁላል በፕሮቲን የበለጸገ ስለሆነ ቶሎ እንዳንራብ ይረዳል።

6) አሳ:-

የስኳር በሽታ ዋነኛው መዘዝ የሚባለው የልብ በሽታ ነው። አሳ ደግሞ በሳምንት አንዴ ብቻ እንኳን መብላት ሰው በየትኛውም አይነት የልብ በሽታ የመያዙን እድል 40% ይቀንሳል።

7) የአበሻ አይብ:-

የአበሻ አይብ ከአብዛኞቹ አይቦች የሚለየው ቅቤው የውጣለት መሆኑ ነው። አይብ በካልሲዩምና በፕሮቲን የበለጸገ ነው። እንደ አይብ አይነት የወተት ምርቶችን በበቂ መጠቀም insulin resistance (የስኳር በሽታ ዋነኛው ችግር) ይዋጋል።

8) ለውዝ አና የለውዝ ዘሮች

ለውዝ በ monounsaturated fats የበለጸገና ከሰውነት ቶሎ የማያልቅ ምግብ ነው። እና እነዚህ ያሉት ባህሪይዎች ለስኳር እጅግ ተስማሚ ናቸው

9) የወይራ ዘይት:-

በአንዳንድ የጤና አኳያ ሲታይ የወይራ ዘይት ፈሳሽ ወርቅ ነው ተብሎ በብዙዎች ተሰይሟል። የወይራ  ዘይት ከፍተኛ  anti inflamatory ባህሪይ አለው። ይህ ደግሞ ስኳርን እና የልብ በሽታን የሚዋጋ ባህሪይ አለው ማለት ነው።

10) ስኳር ድንች:-

ለምሳሌ ያህል በድንች ፋንታ ስኳር ድንች መብላት ደም ውስጥ ያለው ስኳር 30% ያህል ከፍ እንዳይል ያግዛል። ስኳር ድንች በበሽታ ተከላካይ ፋይበር የበለጸገ ነው። ከዛ ውስጥ 40% የሚሟሟና ኮለስተሮልን የሚቀንሱና digestion በፍጥነት እንዳይካሄድ የሚረዱ ናቸው። ሌላ ደግሞ በ ኦሬንጅና ቢጫ carotenoids የበለጸጉ ሲሆኑ እነሱም ሰውነታችን ለ insulin respond እንዲያደርግ ይረዳሉ። ከዛ በተረፈ በ chlorogenic acid የበለጸጉ ሲሆኑ እነሱም የስኳር በሽታ መንስኤ የሆነውን  insulin resistance ይዋጋሉ።

11) ቀይ ስጋ በመጠኑ:-

ቀይ ስጋ በ ፕሮቲን የበለጸገ እና ሰውነታችን ጮማ ከሚሆን በቂ የአካል እንቅስቃሴ ካደረግን በጡንቻ እንዲተካ ይረዳል።



Posted via Blogaway


የስኳር በሽታ ምልክቶች ዋና ዋናዎቹ

- ቶሎ ቶሎ ሽንት መሽናት(polyuria)


- ከፍተኛ የውሃ ጥም(polydipsia)

- የድካም ስሜት ሲሆኑ

ሌሎች ዋና ዋና የሆኑ የስኳር በሽታ ምልክቶች የሚከተሉት ናቸው

የ type 1 ስኳር በሽታ ምልክቶች

1) ሽንት ቶሎ ቶሎ መሽናት(አንዳንዴ በየሰአቱ) በተለይ ማታ ማታ

2) ከፍተኛ የሆነ የውሃ ጥም

3) ከፍተኛ የርሃብ ስሜት(ከበሉ በኋላ እራሱ)

4) የድካም ስሜት

5) ብዥታ

6) ያልተጠበቀ ክብደት መቀነስ

7) ማቅለሽለሽ አንዳንዴ ማስታወክ

8) በሴቶች ተደጋጋሚ የብልት infection

9) አፍ መድረቅ

10) ማሳከክ በተለይ ብልት አካባቢ

ሲሆኑ

የ type 2 የስኳር በሽታ ምልክቶች

1) ሽንት ቶሎ ቶሎ መሽናት(አንዳንዴ በየሰአቱ) በተለይ ማታ ማታ

2) ከፍተኛ የሆነ የውሃ ጥም

3) ከፍተኛ የርሃብ ስሜት(ከበሉ በኋላ እራሱ)

4) የድካም ስሜት

5) ብዥታ

6) ያልተጠበቀ ክብደት መቀነስ

7) ማቅለሽለሽ አንዳንዴ ማስታወክ

8) በሴቶች ተደጋጋሚ የብልት infection

9) አፍ መድረቅ

10) ማሳከክ በተለይ ብልት አካባቢ

ናቸው


ፎሮፎር እንደምናውቀው አሳፋሪና ነዝናዥ ነገር ሊሆን የሚችል ነገር ነው። አንደኛ በጣም ያሳክካል ሁለተኛ በሰው ፊት ነጭ ሆኖ ሊያጋልጠንና ሊያሳፍረን ይችላል።

ፎሮፎር ላለባችሁ ሰዎች ጥሩ ዜናው አንዳንድ ሊያጠፉላችሁ የሚችሉ ዘዴዎች አሉ።

ከነሱም አንዳንዶቹ የሚከተሉት ናቸው

1) ለፎሮፎር ተብለው የተሰሩ ሻምፑዎችን መጠቀም:-

እነሱም

- zinc pyrithione shampoo

- coal tar base የሚል ያለበት ሻምፑ

- selenium sulfide ያለበት ሻምፑ

- salisylic acid ያለበት ሻምፑ

- ketoconazole ያለበት ሻምፑ

አንዳንዶቹ ናቸው

የየሰዉ የቆዳ አይነት የተለያየ ስለሆነ አንዱ የሻምፑ አይነት ካልሰራ ሌላ በመቀየር መሞከር ጠቃሚ ነው።

2) coconut oil ወይም baby oil ራስን መቀባት:-

Coconut oil ወይም baby oil ራስዎትን ከተቀቡ በኋላ የተወሰነ ያህል ጊዜ ቆይተው ይታጠቡት። ይህንን በሳምንት እስከ ሶስቴ ያድርጉ።

3) ራስዎትን እርጎ መቀባት:-

እርጎ ራስዎትን ተቀብተው ከ 10 - 15 ደቂቃ ይቆዩ። ከዛ በኋላ በትንሽ ሻምፑ ይታጠቡ።

4) ራስዎትን የሎሚ ጭማቂ መቀባት:-

የሎሚ ጭማቂ ራስዎትን ተቀብተው ለትንሽ ጊዜ ያህል ቆይተው ራስዎትን በደንብ ይታጠቡ

5) ራስዎትን vinegar/አቼቶ መቀባት:-

ሁለት የሾርባ ማንኪያ አቼቶ ራስዎትን ተቀብተው ትንሽ ጊዜ ይቆዩና በደንብ ይታጠቡት

6) ራስዎት በቂ የጸሃይ ብርሃን በየቀኑ እንዲያገኝ ማድረግ።(እንዳያበዙት ይጠንቀቁ)

7) በ zinc እና በ vitamin b የበለጸጉ ምግቦችን መብላት:-

በ zinc ከበለጸጉ ምግቦች ከዋናዎቹ

ቀይ ስጋ፣ ዶሮ፣ እንቁላል፣ የአሳማ ስጋ፣ የወተት ውጤቶች አንዳንዶቹ ናቸው።

በ vitamin b ከበለጸጉ ምግቦች ከዋናዎቹ

አሳ፣ ጉበት፣ ቀይ ስጋ፣ cheese(አይብ ከተቻለ የፈረንጅ) እና እንቁላል አንዳንዶቹ ናቸው።

8) እንደ ጄል እና ጸጉር ላይ የሙነፉ ስፕሬይዎች የመሳሰሉትን ኬሚካል ያላቸው ነገሮች መጠቀም መቀነስ

9) ጭንቀት መቀነስ

10) በሃኪም ታይቶ ጠንከር ያሉ ፎሮፎርን የሚያጠፉ ሻምፑዎችና ቅባቶች እንዲታዘዝሎት ማድረግና መጠቀም

11) steroid lotion መጠቀም:-

Steroid lotion የሚባሉት በአብዛኛው corticosteroid የሚባል ንጥረ ነገር ያለባቸው ቅባቶች ናቸው።


ብጉርን ለማጥፋት ከሚከተሉት ዘዴዎች አንዱን ወይም የተወሰኑትን በድርርብ መጠቀም ይቻላል።(ግን አለማብዛት ይመከራል)

1) dermitologists የሚያዙትን ቅባቶች መቀባት:-
ከነዚህ መካከል
- salicylic acid
- retinal product
- benozoll peroxide

አንዳንዶቹ ናቸው።

2) asprin ኪኒን ወቅጦ ትንሽ ውሃ ተጨምሮበት በማደባለቅ ብጉሩ ላይ መቀባት። ከተወሰነ ጊዜ በኋላ ፊትን መታጠብ

3) በረዶ ብጉሩ ላይ ከ20 - 30 ደቂቃ የሚያክል ጊዜ መያዝ

4) ብጉሩ እስኪጠፋ በየቀኑ ተለቅ ባለ ዕቃ የፈላ ውሃ አድርጎ እንፋሎቱ ለተውሰነ ያህል ጊዜ ፊትን እንዲመታ ማድረግ

5) ነጭ ሽንኩርት በደንብ ከትፎ ወይም ለሁለት ሰብሮ ብጉሩ ላይ መቀባት ወይም መያዝ። ከዛ መታጠብ

6) ማር ብጉሩ ላይ ቀብቶ ለሚችሉት ያህል ጊዜ ማቆየት። ከዛ ለብ ባለ ውሃ መታጠብ

7) ፓፓያ ጨፍልቆ ብጉሩ ላይ ተቀብቶ የሚቻለውን ያህል ጊዜ ማኖር። ከዛ በቀዝቃዛ ውሃ መታጠብ

8) የሙዝ ልጣጭ(የውስጡን በኩል) ፊትን ቀብቶ የተወሰነ ያህል ጊዜ ቆይቶ መታጠብ።

9) toothpaste(የጥርስ ሳሙና) (ጄል ባይሆን ይመረጣል) ብጉሩ ላይ(ብጉሩ ላይ ብቻ) በመቀባት ለተወሰነ ጊዜ ማቆየት። ከተወሰነ ጊዜ በኋላ መታጠብ

ከዋና ዘዴዎች አንዳንዶቹ ናቸው

ብጉር እንዳይነሳብዎት በቀላሉ ማድረግ የሚችሏቸው ነገሮች

1) ፊትን በየቀኑ በመታጠብ ንጽህናውን መጠበቅ

2) ፊት ደረቅ እንዳይሆን moisturizers መጠቀም

3) አለመጨነቅ

4) የትራስ ልብስ ንጽህናን መጠበቅ

5) ውሃ በቂ መጠጣት

6) makeup የሚጠቀሙ ከሆን
"noncomedogenic" የሚል ምልክት ያለበት ፈልጎ መቀባት። noncomedogenic የሆኑ makeup ብጉር አይቀሰቅሱም

7) የተፈበረኩና ቅባት በተለይ ዘይት የበዛባቸው ምግቦች አለማዘውተር

ከዋናዎቹ አንዳንዶቹ ናቸው።



Posted via Blogaway


አብዛኛውን ሰው ቀለም ያለው ልብስ ይወዳል። ግን ልብሱ ቀለሙን ሲለቅ ደስ የማይል መልክ ሊያመጣና የማንፈልገው አይነት ልብስ ሊሆንብን ይችላል።

ስለዚህ ልብሶት ቀለሙን እንዳይለቅብዎት አንዳንድ መጠቀም የሚችሏቸው ዘዴዎች አሉ። እነሱም የሚከተሉት ናቸው።

1) ልብሱ ላይ ያለውን label በደንብ ማንበብ:-

Label ልብሱ የት እንደተሰራ፣ ከምን እንደተሰራ፣ እንዴት መታጠብ እንዳለበትና እንዴት መጨመቅ እንዳለበት ይነግረናል።

2) ልብስዎትን ሲያጥቡ በቀለም መለያየት:-

አንድ አይነት ቀለም ያላቸው ልብሶች አንድ ላይ ቢታጠቡ ተመራጭ ነው።

3) ልብስዎትን ሲያጥቡ መጀመሪያ ይገልብጡት:-

ልብስዎት ሲታጠብም ሆነ ሲሰጣ ተገልብጦ ቢሆን የልብስ ቀለም እንዳይለቅ ይረዳል። በተለይ ፀሃይ የልብስ ቀለምን ሊያደበዝዝ ስለሚችል ተገልብጦ ቢሰጣ ተመራጭ ነው።

4) ቀለም ያላቸውን ልብሶች በቀዝቃዛ ውሃ ማጠብ:-

ቀለም ያላቸው ልብሶች በሙቅ ውሃ ከሚታጠቡ ይልቅ በቀዝቃዛ ቢታጠቡ ቀለማቸውን ይጠብቃሉ።

5) vinigar(አቼቶ) በማጠቢያው ውሃ ውስጥ መደባለቅ:-

ልብስዎትን ሲያጥቡ በመጀመሪያ አንድ ኩባያ vinigar(አቼቶ) አድርገው ቢያደባልቁ አቼቶው የልብሱ ቀለም እንዳይለቅ ትልቅ አስተዋጽኦ ያደርጋል። የአቼቶውም ሽታ ልብሱ ከታጠበ በኋላ ይለቃል።

6) ጨው መጠቀም:-

አቼቶ የማይጠቀሙ ከሆነ ልብሶትን የሚያጥቡበት ውሃ ውስጥ ትንሽ ጨው በመካከለኛ ቁንጥጫ ጨምረው አሟምተው ልብሶትን ቢያጥቡ ጨዉ የልብስዎት ቀለም እንዳይለቅ ትልቅ አስተዋጽኦ ያደርጋል።


1) ምድር ከተፈጠረ ጀምሮ እስከአሁን ድረስ ከተወለዱት ሰዎች ሁሉ 10% አሁን በህይወት አሉ

2) በዓመት ከ አንድ ሚሊዬን በላይ መብረቅ ምድር ላይ ይጥላል

3) በየሴኮንዱ ከ 100 በላይ መብረቅ ምድር ላይ ይጥላል

4) female black widow የሚባሉ ሴት የሸረሪት ዝርያዎች ከወንድ አጋሮቻቸው ጋር ግንኙነት ካደረጉ በኋላ ግንኙነት ያደረጉትን ወንድ ወዲያው ይበሉታል

5) እስካሁን ድረስ በሬኮርድ ረጅም የሚባለው ዛፍ ባህር ዛፍ ሲሆን በ 1972 ዓ/ም(የፈረንጆች አቆጣጠር)  በአውስትራልያ ሀገር በ 435 feet ነው ሬኮርዱን የያዘው

6) electric eel የአሳ ዝርያ በአንዴ 650 ቮልት የኤሌክትሪክ ሃይል ሊያመነጭ ይችላል

7) ኢቦላ ቫይረስ ከሚይዛቸው 5 ሰዎች መካከል 4 ቱን ይገላል

8) ከ 5 ቢሊዮን ዓመት በኋላ ፀሃይ ነዳጇ ያልቃል

9) ቀጭኔዎች በአብዛኛው ጊዜ በ 24 ሰዓታት ውስጥ ለ 20 ደቂቃ ብቻ ነው የሚተኙት

10) ህይወት ካላቸው ነገሮች ውስጥ ትልቅ ዓይን ያለው giant sqid የሚባል የባህር ውስጥ እንስሳ ሲሆን ዓይኑ 15 inch ነው

11) በ universe ውስጥ ከ 100 ቢሉዬን በላይ galaxy ዎች ይገኛሉ

12) ከመሳሳም ይልቅ እጅ በመጨባበጥ ጀርም ከአንድ ሰው ወደ ሌላ ሰው ሊተላለፍ ይችላል

13) አንድ ከባድ ነገር ከሁሉም ስምጥ የተባለ ውቅያኖስ ውስጥ ቢጣል ያ እቃ የውቅያኖሱን መሬት ሊደርስ አንድ ሰዓት ይፈጅበታል

14) በየሰዓቱ ዩኒቨርሳችን በየአቅጣጫው ከ አንድ ቢሊዮን miles በላይ ይስፋፋል