1) ሽንኩርት ሲከትፉ አይኖት እንዳያነባ

- የሽንኩቱን ጫፎች ቆርጠው ጣሉት
- ከዛ ሽንኩርቱን ለ 30 ሰኮንድ ያህል ቀዝቃዛ ውሃ ውስጥ ይዘፍዝፉት
- ሽንኩርቱን ሲከትፉ አይኖት አያነባም

2) የአፍዎትን ጠረን ማወቅ ከፈለጉ

- ከመዳፍዎት ዝቅ ብለው እጅዎትን ይላሱ
- ለ አስር ሰኮንድ ጠብቁ
- የላሱበትን ቦታ አሽትቱት
- የአፍዎት ጠረን እንደዛ ነው

3) እንቁላል ቀቅለው ሲልጡ እንዲቀልሎት ከፈለጉ እንቁላሉን ሲቀቅሉት 1 የሻይ ማንኪያ ቤኪንግ ሶዳ አብረው ውሃ ውስጥ ይጨምሩ

4) ስልኮትን ቶሎ ቻርጅ ማድረግ ከፈለጉ ቻርጅ ሲያደርጉት Airplane Mode ወይም በአንዳንድ ስልኮች Flight Mode ላይ አድርጉት