አንዳንድ ልብ የማንላቸው ግን ለጤነታችን መጥፎ የሆኑ ነገሮች



ለጤንነታችን መጥፎ ወይም ጎጂ የሆኑ ነገሮችን በአብዛኛው ጊዜ እናውቃለን ብለን ልንገምት እንችላለን። ግን አንዳንዴ ያልጠበቅናቸው ነገሮች ለኛ መጥፎ ሆነው ሊገኙ ይችላሉ።

እናም ከነዚህ ውስጥ አንዳንዶቹን በሚከተለው እንመለከታለን።

1) ርካሽ የፀሓይ መነፅሮች:-

አንዳንድ ophthalmologists እንደሚያስረዱት ከሆነ ከ UVA እና ከ UVB ጨረሮች የመከላከል አቅም የሌለው የፀሓይ መነፅር ከሚያደርጉ ጭራሽ ባያደርጉት ይሻላል ነው የሚሉት ባለሙያዎቹ።

ባለሙያዎቹ ሲያስረዱ ለዚህ ምክንያቱ ሃይለኛ ብርሃን ወዳለው ነገር ስንመለከት በተፈጥሮ አይናችንን ጭምት አድርገን ቢያንስ የሚገባውን የጨረር ብዛት እንቀንሳለን። ግን የፀሓይ መነፅር ካደረግን የብርሃን ብዛት ስለማይኖር እንደዛ አናደርግም። ግን በአብዛኛው ሃይለኛ ብርሃን የሚያመነጩ ነገሮች በዛውም ለአይን ጤንነት ጥሩ ይስልሆንትን UVA እንስ UVB የሚባሉትን ጨረሮችንም እንደዚሁ በሃይል ያመነጫሉ። እና ብዙዎቹ የፀሓይ መነፅሮች ብርሃንን ይቀንሳሉ እንጂ እነዚህን UVA እና UVB የሚባሉትን ለአይን ጎጂ የሆኑትን ጨረሮች አይከላከሉም።

እናም ባዶአችንን ብንሆን አይናችንን ጭምት አድርገን ቢያንስ የነዚህን ጨረሮች መጠን ልንቀንስ እንችላለን። ግን እነዚህን የማይከላከሉ የፀሓይ መነፅሮች ካደረግን ግን አይናችን ብዙ ብርሃን ያለ ስለማይመስለው ጭምት አይልም። በዛውም እነዚህ ጎጂ ጨረሮች አይናችን ውስጥ አንዳለ እንዲገቡ እናደርጋለን ማለት ነው።

2) ብዙ ውሃ መጠጣት:-

ይሄ ነጥብ ምናልባት አንዳንድን ሰው ሊገርመው ይችላል። ለምን ቢባል ብዙ ጊዜ የጤና ምክር ሲሰጥ በዛ ያለ ውሃ ጠጡ ይባላል።

በቀን ውስጥ በአማካይ ከ 1.6 ሊትር እስከ 2 ሊትር ውሃ መጠጣት ለጤና ጥሩ ነው። ግን ከዛ በጣም የበለጠ ውሃ መጠጣት ለጤና ጥሩ ላይሆን ከመቻሉ አልፎ በጣም ከበዛ ሊገል ሁሉ ይችላል።

ይህ ሲሆን ደግሞ water intoxication (የውሃ ምርዛት) በመባል ይታወቃል።

ስፖርት ለማይሰራና ብዙ ለማያልበው ሰው ከ1.6 እስከ 2 ሊትር ውሃ እንዲየውም ብዙ ሆኖ ሊሰማ ይችላል። እናም አውቆ ካልሆነ በስተቀር ከዛ በጣም የሚበልጥ መጠን ውሃ የመጠጣቱ ዕድል ጭራሽ አይኖርም። ግን ከባድ ስፖርት የሚሰራና በጣም የሚያልበው ሰው በላቡ የወጣውን ውሃ ለመተካት ውሃ ይጠማዋል ይጠጣል።

እዚህ ላይ ችግሩ ምንድን ነው ውሃው ሲጠጣ ውሃው ቢተካም እንደ sodium(ሶዲዩም) አይነት ለሰውነት አስፈላጊ ንጥረ ነገሮች electrolytes ከውሃ ጋር አብረው ውጥተው ግን ከውሃ ጋር አብረው አልተተኩምና imbalace(አለመመጣጠን) ይፈጠራል።

ይህ ሰውነታችን ውስጥ የሚፈጠረው  electrolytes ከውሃ ጋር አለመጣጠን እስከሞት ድረስ ሊዳርግ የሚችል አለመመጣጠን ነው።

ስለዚህ ከባድ ስፖርት የሚሰሩ ሰዎች sport drinks (የስፖርት መጠጦች) ተብለው ተመጣጥነው የተዘጋጁ መጠጦች ቢጠጡ እና ደግሞ ብዙ ውሃ ከሰውነቱ በላብም ሆነ በሌላ ለወጣው ሰው ደግም(ለስፖርተኞችም ሊሆን ይችላል) ORS ወይም ለምለም በጥብጦ መጠጣት በጣም የተሻለ ነው።

3) ብዙ መሮጥ:-

በድጋሚ ይሄ ነጥብም ሰውን ሊያስገርም ይችላል። ምክንያቱም መሮጥ ከእንቅስቃሴ ወይም ስፖርት ጋር የተያያዘ ነው ስፖርትም ደግሞ ለጤነት ጥሩ ነው።

አዎ ትክክል ነው። ስፖርት ለጤንነት ጥሩ ነው።

ግን ብዙ መሮጥ ችግር ሊሆን የሚችልባቸው ጊዜያቶችና ሁኔታዎች አሉ።

እነሱም

ሀ) ረጅም ርቀት መሮጥ፡-

ረጅም ርቀት መሮጥ አንድ ሰው በ arthritis በሽታ የመያዙን እድል ይጨምራል። እሱም ብቻ ሳይሆን የጉልበት cartilage ን ያሳሳል ተብሎ ይገመታል።

ለ) በአፈርና በሳር ላይ ከመሮጥ ፋንታ በሲሚንቶና አስፋልት ላይ አዘውትሮ መሮጥ:-

ይህ እራሱ ቁርጭምጭሚት ላይ ችግር ያመጣል ተብሎ ይገመታል

ሐ) በጣም ወፍራም ሆኖ ብዙ ለመሮጥ መሞከር:-

አንድ ሰው በጣም ወፍራም ሆኖ አዘውትሮ ቢሮጥ ቁርጭምጭሚቱና ጉልበቱ ላይ ችግር ሊደርስ ይችላል። ስለዚህ ቀንሶ average ክብደት ላይ እስኪደርስ ድረስ ከመሮጥ ይልቅ መራመድ ይመከራል።

4) ኮምፕዩተር በብዛት መጠቀም:-

በመጀመሪያ አንዳንድ Environmental ቡድኖች የኮምፒዩተር መስኮት መርዛማ ባህሪይ ያለው አቧራ እንደሚይዝ ጠቁመዋል። ይህም ደግሞ neurological ችግር ሊፈጥር ይችላል ተብሎ ይገመታል።

ሁለተኛ ኮምፒዩተር በብዛት የሚጠቀም ሰው ብዙ መቀመጡ አይቀርም። ብዙ መቀመጥ ደግሞ ለጤነት መጥፎ ነው።

ሌላው ነገር ደግሞ ከኮምፒዩተር የሚመነጨው ደማቅ ብርሃን አይኖቻችንን ሊያደክመው ይችላል።

ለነዚህ መፍትሄ አንዳንድ ዶክተሮች የሚመክሩት ኮምፒዩተር ስንጠቀም በመሃል እረፍት ወስደን መንጠራራትና ትንሽ እንቅስቃሴ ማድረግ አይናችንን ደግሞ ከ 30 ደቂቃ እስከ 1 ሰዓት በመሃል ማሳረፍ ነው።

5) ብዙ መቀመጥ:-

ይሄ ነጥብ ብዙም ባያስገርምም ለእውቀቱ ያህል በቀን 3 ሰዓት ብቻ እራሱ መቀመጥ ከህይወታችን ከ 2 እስከ 3 አመት ድረስ ይቀንሳል ተብሎ በባለሙያዎች ይገመታል።

ሌላም ደግሞ በሳምንት 23 ሰዓት ብቻ እራሱ መቀመጥ የሰውን ልጅ ለሆነ አይነት የልብ በሽታ እጅጉኑ ተጋላጭ እንደሚያደርግ ተመራማሪዎች ይገልፃሉ።

6) ከመጠን በላይ ሻወር መውሰድ ወይም መታጠብ፡-

እሺ። እንደገና አስገራሚ ነጥብ ላይ መጣን። ብዙውን ጊዜ መፀዳዳት እና ንፅህናን መጠበቅ ለጤና ጥሩ ነው ይባላል። አዎ ነውም። ግን ሁሉም ነገር ሲበዛ ጥሩ አይደለም እንደሚባለው ሁሉ ይሄም ሲበዛ መጥፎ ሊሆን ይችላል።

ምክንያቶቹን በቀላሉ ስንመለከት

አንድኛ ከመጠን በላይ መታጠብ የሰውነታችንን natural oil ወይም ተፈጥሮእዊ ቅባት በማድረቅ ቆዳችን ደረቅ እንዲሆን ያደርጋል።

ሁለትኛ በተፈጥሮ ጎጂ የሆኑ ባክቴሪያዎች እንዳሉ ሁሉ በተፈጥሮ ጠቃሚ የሆኑ ባክቴሪያዎች እጆቻችንና ሰውነታችን ላይ ሁሌም ይገኛሉ። እናም ከመጠን በላይ በሳሙና መታጠብ እነዚህ ጠቃሚ ባክቴሪያዎችም እንዲጠፉ ያደርጋል።

ስለዚህ ሁሉም ነገር ልክ እንዳለው መገንዘብ ይገባል።

Posted via Blogaway


0 comments:

Post a Comment