Immune System (የሰውነት በሽታ መከላከያ) አቅም የሚጎዱና የሚያጎለብቱ ነገሮች

የአኗኗር ዘይቤዎ ምን ያህል የሰውነትዎት የመከላከያ አቅም ከበሽታ ሊከላከልዎት እንደሚችል ይወስናል።

ለጤንነት መጥፎ የሆኑ የአኗኗር ዘይቤዎችን ጥሩ በሆኑት በመተካት የመከላከያ አቅምዎትን ጤነኛና ጠንካራ አድርገው ሊያቆዩት ይችላሉ።

የትኞቹ ዘይቤዎች ለ ሰውነት የበሽታ መከላከያ አቅም ጥሩ እንደሆኑና የትኞቹ ደግሞ መጥፎ እንደሆኑ እንይ።

1) በቂ እንቅልፍ መተኛት:-

በቂ እንቅልፍ መተኛት ለሰውነት መከላከያ አቅማችን እጅግ አስፈላጊ ነገር ነው። ጥናቶች እንደሚያመለክቱት ከሆነ በቂ እንቅልፍ የሚያገኙ ሰዎች ከማያገኙት ይልቅ በበሽታዎች(እንደጉንፋን አይነት ቀላል በሽታዎችም ቢሆን) የሚያዙበት ጊዜ ያነሰ ነው።

ተመራማሪዎች በትክክል እሄ የሚባል እንቅልፍንና የሰውነት የመከላከል አቅምን የሚያገናኝን ነገር ገና ባያውቁም በእርግጥ የሚታወቀው ነገር በቂ እንቅልፍ መተኛት ለሰውነት መከላከያ አቅም በጣም ጠቃሚ እንደሆነ እና በቂ እንቅልፍ አለመተኛት የጭንቀት hormones በጣም ሰውነታችን ውስጥ እንዲለቀቁ እንደሚያደርግ እና የጭንቀት hormones ደግሞ ለሰውነት መከላከያ አቅም ጎጂ እንደሆኑ ነው።

2) ስፖርት መስራት:-

ስፖርት መስራት ለ በሽታ መከላከያ አቅም ብቻ ሳይሆን ለብዙ ነገር ይጠቅማል። ስፖርት መስራት ደግሞ እንቅልፍም በደንብ እንድንተኛ ይረዳል። በቀን ውስጥ 30 ደቂቃ ብቻ እራሱ መራመድ ትልቅ የጤና ጥቅም አለው።

3) የአመጋገብ ዘይቤ:-

ስኳር የበዛበት ምግብ መብላት ወይም ስኳር የበዛበት መጠጥ መጠጣት ባክቴሪያን የሚዋጉ የሰውነት ተከላካይ ሴሎችን ከተጠጣ በኋላ ለትንሽ ሰአታት ይቀንሳል። ስለዚህ ስኳር የበዛበት ነገር መብላት ብዙም አይመከርም።

ምግባችን አትክልትና ፍራፍሬ በርከት ያለበት፣ በ ቫይታሚን C ፣ በ ቫይታሚን E በ beta caroten እና zink የበለጸጉ ምግቦችን መብላት የሰውነታችንን  immune system ወይም መከላከያ አቅም ያዳብራል።

4) ጭንቀት:-

ብዙ መጨነቅ ሰውነታችን cortisol የሚባሉትን የጭንቀት hormomes ከልክ በላይ እንዲለቅ ያደርጋል። እኚህ hormones ደግሞ ለ immune system ወይም የመከላከያ አቅማችን መጥፎ ናቸው።

5) ከሰዎች ጋር ቅርርብነት:-

ለሰው መድሃኒቱ ሰው ነው ሲባል ሰምተን ልናውቅ እንችላለን። እውነትም ጥናቶች እንደሚደግፉት ከሆነ ሌሎች ነገሮችም አብረው ሚና ቢጫወቱም ከሰዎች መቀራረብ እና ማህራዊ ኑሮ ማዳበር የበሽታ ተጋላጭነትን ሊቀንስ ይችላል።

6) መሳቅ:-

መሳቅ ለሰውነታችንም ሆነ ለ ሰውነታችን immune system(የመከላከያ አቅም) ጥሩ ነው። መሳቅ የተወሰኑ የነጭ የደም ሴል አይነቶች በይበልጥ እንዲመረቱም ሊያደርግ ይችላል። ነጭ ደም ሴሎች ደግሞ በሽታን የሚዋጉልን ሰውነታችን ውስጥ ያሉ ወታደሮች ናቸው።


0 comments:

Post a Comment