ላሞችን በስም መጥራት ማስለመድ የወተት ምርትን 3.5% ይጨምራል

በ Newcastle University ሳይንቲስቶች በተገኘው የምርምር ውጤት መሰረት ላሞችን ስም ሰይሞ በስማቸው መጥራት፣ እንዳይፈሩና እንዳይደነግጡ ማድረግ እና እንደግለሰብ ማየት የወተት ውጤትን በ 3.5% ይጨምራል።

የላሞችን ጠቅላላ ፍርሃታቸውን መቀነስ ዘር አተካካቸውን፣ እድገታቸውን እና የበሽታ መከላከል አቅማቸውን ያሻሽላል። ይህ ብቻ ሳይሆን ላሞቹ ሰው ካልፈሩ እና ከሰው ጋር ከተላመዱ ሊታለቡ ሲሉ ወተታቸውን አይከለክሉም ይላል በ Anthrozoos journal የተዘገበው ጥናታዊ ዘገባ።

ጥናቱ እንደሚያሳየው ከሆነ ላሞችን በስም የሚጠሩ  እና የማይጠሩ በሁለት ተመድበው ተመሳሳይ የላም ዘር ኖርዋቸው እራሱ በስም የሚጠሯቸው ከማይጠሯቸው እጅግ የበለጠ የወተት ውጤት እንደሚያገኙ ጥናቱ አይቷል።

ይሄ በሳይንሳዊ መረጃ እንዴት ሊደገፍ ይችላል ቢባል ብዙም የማይጨነቁ እና ፈታ ብለው የሚያድጉ ላሞች cortisol የሚባለውን የጭንቀት hormone ብዙም አያመነጩም። Cortisol ሰውም ሆነ እንስሳ ብዙ ሲጨነቅ ሰውነት እራሱ የሚያመነጨው hormone ነው። Cortisol የሚባለው የጭንቀት hormone ደግሞ በሰውም ሆነ በእንስሳ በሰውነት የሚካሄደውን የወተት ምርትን እንደሚቀንስ ብዙ ሳይንሳዊ ጥናቶች ያረጋግጣሉ።


0 comments:

Post a Comment