እርጅናን የሚዋጋ እና እስከ 120 አመት ድረስ በሙሉ ጤንነት ሊያስኖር የሚያስችል መድሃኒት metformin ሙከራ ላይ ነው



በአለማችን የመጀመሪያው እርጅናን የሚዋጋ መድሃኒት በአውሮፓዊያን ካላንደር መጪ አመት በሰዎች ላይ ሙከራ መደረጉን ይጀምራል። የዚህም ሙከራ ውጤት ደግሞ ሰዎች ከፈለጉ በጥሩ ጤንነት እስከ 120 አመት ድረስ እንዲኖሩ ሊያደርግ የሚችል ሊሆን ይችላል ይላል "The New Zealand Herald" ጋዜጣ።

ሳይንቲስቶች አሁን ሰዎች ቶሎ እንዳያርጁ መከላከል እንደሚቻልና Alzheimer's እና Parkinson's የሚባሉ በሽታዎችን ደግሞ ታሪክ ማድረግ እንደሚቻል ያምናሉ።

አሁን ባለንበት ጊዜ እውነት መስሎ ላይታይ ቢችልም ተመራማሪዎች metformin የሚባለው የስኳር በሽታ መድሃኒት የእንስሳቶችን እድሜ እንደሚያራዝም በማስረጃ አረጋግጠዋል። ስለዚህም የአሜሪካ ምግብ እና መድሃኒት ተቆጣጣሪ አካል "food and drug administration" ይህ መድሃኒት ሰው ላይም ተመሳሳይ ውጤት ያሳይ እንደሆን እንዲመረመር ሙከራው መጪ አመት እንዲጀምር ፈቃድ ሰጥቷል።

ይህ ውጤታማ ከሆነ የ 70 አመት ሰው በጤንነት እና በሰውነት ወጣትነት ከአሁኑ ከ50 አመት ሰው ጋር ተመሳሳይ ይሆናል ማለት ነው።

ሳይንቲስቶች እንደሚሉት ከሆነ ማርጀት ማምለጥ የማንችለው የህይወት ዱብዳ አይደለም። እንዲየውም አንዳንድ የባህር እንስሳቶች እንደማያረጁና በእድሜ ምክንያት ጭራሽ የሰውነት ድክመት እንደማያሳዩ ይገልጻሉ።

ይህ ሙከራ ውጤታማ ከሆነ እርጅናን ብቻ ሳይሆን ከእርጅና ጋር ተያይዘው የሚመጡ በሽታዎችንም አብሮ ይከላከላል ተብሎ ይገመታል። ስለዚህ አንድ ህጻን ልጅ አሁን ሲወለድ ይኖራል ተብሎ የሚጠበቀውን እድሜ 50 በመቶ ይጨምራል ተብሎ ይታመናል።



Posted via Blogaway


0 comments:

Post a Comment