አሸባሪው ቡድን አይ ኤስ (ISIS) ከምንም በላይ የሚፈሩት ነገር

አይ ኤስ(ISIS) የተባለው ቡድን እንደምናውቀው በዘመናችን ካሉ አሸባሪ ቡድኖች ከሁሉም አሸባሪ ቡድኖች በላይ በአስገራሚ ሁኔታ ብዙ ሰው፣ ብዙ ገንዘብ እና ብዙ መሬት ያለው ቡድን ነው።

እኚህ የ አይ ኤስ አሸባሪ ቡድን አባሎች እንደምናየው እና እንደምንሰማው እናም የአይን ምስክሮች እንደሚገልጹት ከሆነ ጥሩ እና መጥፎን የሚዳኝ እግዚአብሄር እንደሌለ ወይም እነሱ የሚከተሉት እግዚአብሄር አረመኔ እና ህሊና ቢስ ነው የሚል መልእክት ለማስተላለፍ እንደሚፈልጉ በሚመስል መንገድ የእስልምና ሃይማኖት ባይፈቅደው እራሱ በእስልምና ስም ወንድ ወይ ሴት፣ ልጅ ወይ አዋቂ ወይም ንጹህ ወይ ወንጀለኛ ሳይሉ ሰው እንደሚገድሉ፣ እንደሚያርዱ፣ ሴቶችን በመጥለፍ ከ 100 ዶላር ጀምረው እንደሚሸጡ፣ በእጃቸው የገቡ ሴቶችንም ደግሞ እንደፈለጉ እየተፈራረቁባቸው አስገድደው እንደሚደፍሩ እራሳቸው የሚለቁት የቪዲዮ ቀረጻ እና በነሱ ስር የሚኖሩ እና ከእነሱ እጅ ያመለጡ ሰዎች ይመሰክራሉ።

እኚህ የ አይ ኤስ ቡድን አባላት የሚያደርጉትን ነገር ሁሉ የሚያደርጉት በእስልምና ስም ነው። ይህም ሆኖ የሚያደርጉት ነገር ሁሉ ሰብአዊ ርህራሄ ፈጽሞ የሌለው፣ አረመኔያዊ እና የክፋት ነጸብራቅ እንጂ ለናሙና ያህል እንኳን አንድ ጥሩ ነገር አድርገው ታይቶም ወይም ተሰምቶም አይታወቅም።

እነዚህ የአይ ኤስ ቡድን አባላት ያደረጉትን ነገር አድርገው ሲሞቱ ገነት ገብተው 72 ድናግል ይጠብቁናል ብለው ያምናሉ። እንዲየውም የሚያደርጉት ነገር ሁሉ ለሱ ብለው እንደሆነ ይታወቃል።

በሚያደርጉት ተግባር አንድ ሰው እነኚህማ የሚፈሩት ነግር የለም ብሎ ሊያስብ ይችላል። ግን ይሄ ከእውነት የራቀ ነው። በእርግጥ ገነት ገብተን 72 ድንግሎች ይጠብቁናል ብለው ስለሚያምኑ ሞትን ላይፈሩ ይችላሉ። ተጨንቀው ከህንጻ ላይ ተፈጥፍጠው የሚሞቱ ሰዎችም እኮ ሞትን አልፈሩም። ሞት ደግሞ ፈራንም አልፈራንም ማንም አይቀርለትም እና የሚፈራ ነገርም መሆን የለበትም። ግን ሰው እንደመሆናቸው መጠን ከሞት ውጪ ማንም ሰው የሚያስፈራው ነገር ያስፈራቸዋል። እንዲየውም በቅርብ አንድ የ አይ ኤስ ቡድን አባል በ ኩርዶች ተይዞ እንደ ህጻን ልጅ ሲያለቅስ በ ቪዲዮ ተለቆ የአለም መሳሳቂያ ሆኗል።

ግን ከስቃይ እና ከውርደት በላይ ደግሞ የ አይ ኤስ ቡድኖች የሚፈሩት ነገር አለ። ይህም ደግሞ በሴት እጅ መገደልን ነው። እነሱ እንደሚያምኑት ከሆነ እራሳቸውን ቢያጠፉም ሆነ በጦርነት ላይ በወንድ ከተገደሉ ገነት ገብተው ከ 72 ድንግሎች ጋር አለማቸውን እንደሚቀጩ ነው። ግን እንደድንገት በሴት ከተገደሉ እኚህ ሁሉ ድንግሎች እና ገነት ቀርቶ ቀጥታ ገሃነም እንደሚሄዱ ነው።

Kurdish Peshmerga Forces የኩርዶች ፐሽመርጋ ሃይሎች አይ ኤስ ዋና ጦርነት የሚያካሄድበት አካባቢ ኢራቅ እና ሶርያ አካባቢ የሚገኙ የ ኩርዶች ወታደራዊ ሃይል ናቸው። እነሱ ወታደራዊ ሃይል ውስጥ ደግሞ ብዙ ሴቶች ይገኛሉ። እነዚህም ሴቶች በየቀኑ ከ አይ ኤስ ጋር ፍልሚያ መግጠም ከጀመሩ ሰንበትበት ብሏል። የሚያስቀው ነገር ግን የ አይ ኤስ ወታደሮች የ ኩርድ ሴት ወታደሮችን ሲያዩ ከሩቅ ሲሸሹ ሲታይ ነው። እንዲየውም እኚህ የኩርድ ሴት ወታደሮች ስለዚህ ጉዳይ ሲጠየቁ ሁሌም መልሳቸውን የሚመልሱት ከፈገግታና ከሳቅ ጋራ ነው። ግን ቢሸሹም የሚለቃቸው የለም። እነዚህ የኩርድ ሴት ወታደሮች እጅግ ብዙ የሆኑ የ አይ ኤስ ወታደሮችን ቀጥታ ወደ ገሃነም ልከዋል።


0 comments:

Post a Comment